African Leadership Excellence Academy
2.14K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን እምርታ በማረጋገጥ ላይ መሆኗ ተመለከተ::

#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን እምርታ በማምጣት ላይ መሆኗን ክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ #ተመስገን_ጥሩነህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ በሚሰጠው ስልጠና ላይ አመላከቱ።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ የፀጥታ እና የደህንነት ተቋማትን በመገንባት ረገድ የረጅም ጊዜ ባለ ታሪክ መሆኗንም ገልፀዋል።

የዛሬው የሥልጠና ርዕሰ ጉዳይ "የፀጥታና ደህንነት እመርታ" የሚል ሲሆን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የጽህፈት ቤቶች አመራሮች የሥልጠናው ገለፃ በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ውስጥ ቀርቧል።

ክቡር ም/ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ባቀረቡት ገለፃ ሀገራችን የፀጥታና የደህንነት ተቋማትን በመገንባት ረጅም አመታትን ማስቆጠር ብቻ ሳይሆን እነዚህ ተቋማት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ አልፈው እንደ ኮሪያ፣ ኮንጎ እና በሌሎች ሀገራት በመሰማራት ሰላም የማስከበር ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት የቻሉ ናቸው ብለዋል።

ተቋማቱ የየራሳቸው ጥንካሬ ቢኖራቸውም የነበረባቸው ክፍተት ሊያርም በሚችል መልኩ አሁን ላይ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ አነሳሽነት ወቅቱን በሚመጥን ደረጃ የሪፎርም ሥራ በመሠራቱ ከፍተኛ አቅም ለመፍጠር ተችሏል ሲሉ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ተናግረዋል።