African Leadership Excellence Academy
2.14K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ ይህን የገለፁት "እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ተሟላ ብልፅግና" በሚል ርዕስ የፕላንና ልማት ሚንስትር በሆኑት በክብርት #ፍፁም_አሰፋ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች አመራሮች የቀረበ ገለጻን አስመልክቶ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ ከተሳታፊዎች ለቀረቡት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት መድረክ ላይ ነው።
ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ከኢኮኖሚ ዕድገቱ፣ ከዋጋ ግሽበትና ከኑሮ ውድነት እንዲሁም ከንግድ ሥርዓቱ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ ከለውጥ ወዲህ ባሉት ስድስት አመታት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳየቷ ጥርጥር የሌለው፣ የሚታይና የሚጨበጥ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
ይህን የኢኮኖሚ ዕድገት የአለም ባንክና የገንዘብ ተቋማት ሁሉ የመሰከሩለት ነው ያሉት ክቡር ዶ/ር ካሣሁን፤ የዕድገቱ መነሻዎች የለውጡ መንግሥት ያሳየው ቁርጠኝነት እና የፖሊሲ ለውጦች መሆናቸውን በዋናነት ጠቅሰዋል።
አያይዘውም አሁን ላይ የተጀመሩ የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት በተለይ በስንዴ፣ በሩዝና ሌሎች ምርቶች ከፍተኛ የማምረት አቅም፣ የመደበኛና ትይዩ ንግድ ላይ የነበረውን ሰፊ ልዩነት በማጥበብ እና የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎች በመንግሥት ማድረግ በመቻሉ በአጭር ጊዜ በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ እያሳዩት ያለው ውጤት እጅግ ከፍተኛ በመሆኑ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በ2025 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በዓለም ኢኮኖሚያቸው በከፍተኛ ደረጃ ካደጉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ትገባለች፤ ከአፍሪካ ደግሞ በቀዳሚነት ተርታ ትሰለፋለች ሲሉ አብራርተዋል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ዜጎች የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ተፅእኖ እንዳለባቸው ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጠቁመው፤ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ደሞዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች ያለውን ጫና በመረዳት የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ እና በሌሎች ልዩ ልዩ ድጎማዎች እንዲሁም እንደአጠቃላይ የሕዝብን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ምርትን በከፍተኛ ደረጃ በማምረት የገበያውን ሁኔታ በማስተካከል ኑሮን ለማቃለል መንግሥት እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
በቀጣይም መንግሥት ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዜጎች በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ እየቀየሰ እንደሚሰራም ነው የገለፁት።
ከንግድ ሥርዓቱ ጋር በተያያዘ በርካታ ማነቆዎች መኖራቸውን ጠቁመው፤ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት መንግሥት ነፃ የንግድ ቀጠናን ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን እያደረገ መሆኑንም ክቡር ዶ/ር ካሣሁን አመላክተዋል።