African Leadership Excellence Academy
2.14K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ በመጪዎቹ ዓመታት #የኢኮኖሚ_እመርታ እንደምታስመዘግብ ተገለፀ።
(ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 11ቀን ፣2017 ዓ.ም፤ ሱሉልታ፤ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አራት አስርተ አመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ እመርታ እንደምታስመዘግብ የፕላንና ልማት ሚንስትር ክብርት ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ በሚሰጠው ስልጠና ላይ ገለፁ።
የትንበያ ጥናቱ ከሀገራችን የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ባሻገር የውጭ ሀገራት ባለሙያዎችም ያረጋገጡት ነው ብለዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም ይህን የተናገሩት "እመርታ ከሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ተሟላ ብልፅግና" በሚል ርዕስ #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራርና አባላት እንዲሁም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤቶች አመራሮች እየተሰጠ ባለው ሥልጠና ላይ ባቀረቡት ገለፃ ነው።
ሀገራት ባላቸው የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ ከሚያመርቱት ምርትና ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ አንፃር ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ተብለው በሶስት እንደሚከፈሉ አብራርተዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም ሀገራችን አሁን ላይ በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካስመዘገቡ ሀገራት በ5ኛ ደረጃ፣ ከሰሃራ በታች ካሉት ሀገራት በ3ኛ እና ከምስራቅ አፍሪካ ደግም ቀዳሚውን ደረጃ መያዟን አስገንዝበዋል።
በአለም ባንክ በተደረጉ ጥናቶች ኢትዮጵያ በ2021 እና በ2022 ዓ.ም. በአፍሪካ ሀገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት 2ኛ ደረጃን እንደምትይዝ መጠቆሙን አብራርተዋል።
ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ሀብት፣ የሰው ሀይል፣ ይሄንን ማስፈፀም የሚችል መንግስት አኳያ ህልሟን እውን የማታደርግበት አንዳች ምክንያት እንደማይኖርም ነው ያስረዱት።
ስልጠናው ዛሬም #በአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ለ5ኛ ቀን ቀጥሏል።