African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ጋር ተወያዩ።

አካዳሚውና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ በሚሰሩባቸው የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ላይ ምክክር ተደርጓል።

የአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ አካዳሚው በቀጣይ ሶስት ዓመታት ሊሰራቸው ያቀዳቸውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለአምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ ገልጸዋል።

አካዳሚው በአፍሪካናይዜሽን ፕሮጀክቱ ሊሰራቸው ያቀዳቸውን ተግባራት ከግብ ለማድረስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር እንደሚያስፈልገው የጠቀሱት አቶ ዛዲግ፤ በተለይም በአፍሪካውያን ለሚደራጀው የምክትል ፕሬዚደንት ዘርፍ፤ ለሚከፈቱ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች፤ ከአፍሪካውያን ለሚመረጡ የቦርድ አባላት፤ የአመራር ልማት ማዕከሉ አፍሪካዊ ቅርጽና ይዘት እንዲኖረው በሚደረጉ ስራዎች ውስጥ አፍሪካውያንን በማስተባበር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጎላ ሚና እንዲጫወት ጥሪ አቅርበዋል።

ተቋሙን ዓለምአቀፍ የጉባኤ ማዕከል ለማድረግም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለመስራት ማቀዳቸውን የጠቆሙት አቶ ዛዲግ፤ አካዳሚው ሱሉልታን እንደ ዳቮስ የሚል ፕሮጀክት መንደፉንና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለምአቀፍ ተቋማት ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ታዋቂ አፍሪካውያን እና ዓለምአቀፍ ሙሁራንን በማፈላለግ በአካዳሚው ውስጥ አስተማሪ ንግግሮችንና ክርክሮችን እንዲደረጉ የሚያስችል አቅም እንዳለው የጠቀሱት አቶ ዛዲግ ለአፍሪካውያን አመራር የልህቀት ሽልማትም በጋራ መስራት የሚቻልበት ዕድል እንዳለ ጠቁመዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ በበኩላቸው ስለ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለውጥ፤ ሽግግር እና ማስፋት ስራዎች የተደረገላቸውን ገለጻ አድንቀው፤ ተቋማዊ ትብብርና ትስስር ፈጥሮ ወደ ስራ መግባት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደር ታየ አያይዘውም አካዳሚው የሀሳብ ማፍለቂያ ማዕከል ለመሆን የሰነቀው ራዕይ የሀገራችንንም ሆነ የአህጉራችንን ችግር ለመፍታት የሚያግዝ በመሆኑ ቅድሚያ ተሰጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ ጠቁመው፤ ለክፍለ ዘመኑ የሚመጥን አመራር ለማፍራትም የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት የሚኖራቸው ሚና ቀላል ግምት የማይሰጠው በመሆኑ ከአካዳሚው ጋር በትብብር መስራት እንደሚቻል ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ተጠቅማ አፍሪካውያንን በማስተባበር ደረጃ ያለውን ውስንነት የጠቀሱት አምባሳደር ታየ፤ አካዳሚው ያቀደውን ወደ ተግባር እንዲለውጥ በተቋማቸውም ሆነ በግላቸው እንደሚያግዙ ተናግረዋል።
እኛ #የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር #600_ሚሊዮን_ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን ልናኖር ተዘጋጅተናል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!

አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚን ወክለው በጫካ ፕሮጀክት የችግኝ ተከላ ላይ የተሳተፉ አመራሮች እና ሰራተኞች ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም አረንጓዴ ዓሻራቸውን አኑረዋል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አካዳሚውን ወክለው ከሸገር ሲቲ መና አብቹ ክፍለ ከተማ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም አረንጓዴ ዓሻራቸውን አኑረዋል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
👍2
#የአፍሪካ_አመራር_ልህቀት_አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በተገኙበት ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም አረንጓዴ ዓሻራቸውን አኑረዋል::

በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!
👍3