African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
AFLEX and Clingendael Institute Explore Potential Partnership Opportunities
African Leadership Excellence Academy president Zadig Abreha met with Clingendael Institute Academy Fellow, Gijs Van Loon to discuss potential partnership opportunities.
The meeting at the Academy's Addis Ababa head office aimed to explore collaboration between AFLEX and Clingendael Institute on various research, training, and initiatives.
Mr. Zadig Abreha and Mr. Gijs Van Loon discussed a range of potential partnership areas, including research collaborations, training and education programs, staff exchange, and experience sharing.
Mr. Zadig Abreha expressed excitement about potential collaboration between organizations, stating that the Academy is committed to advancing leadership excellence through leadership development, education, and research.
Both parties express hopefulness about the potential benefits of a partnership and plan to continue exploring these opportunities in the coming weeks.
Clingendael, the Netherlands Institute of International Relations, is an independent think tank and academy on international affairs that aims to contribute to a secure, sustainable, and just world.
AFLEX President and US Embassy's Cultural Affairs Officer Discuss the Future of the Leadership Development Program and Partnership
The President of the African Leadership Excellence Academy, Mr. Zadig Abreha, and the Cultural Affairs Officer at the US Embassy, Ryan Bradeen, met today to discuss the latest developments in the leadership development program and potential partnership opportunities between the parites.
The meeting focused on the importance of the Leadership Development Program, women's leadership, and emerging leadership in today's complex global landscape. Mr. Zadig emphasized the need for leaders to possess these skills to navigate high-pressure situations and build strong relationships with international partners.
"We believe that leadership development is key to achieving this goal," said Mr. Zadig. "That's why we're excited to explore potential partnership opportunities with the US Embassy."
"We're particularly interested in exploring ways to integrate our expertise in leadership development program and experience sharing into the US Embassy's diplomatic training programs," said Mr. Zadig.
Mr. Ryan Bradeen noted that the US Embassy promotes cross-cultural dialogue and exchange programs to build bridges between the US and other countries.
The parties discussed several potential collaboration initiatives, including joint research projects, workshops, and training programs.
The initiative aims to enhance leadership skills among senior leaders, business leaders, and community members in the US and the Academy's international network.
The meeting concluded with a commitment from both parties to explore further partnership opportunities and establish a framework for collaboration.
Day #1 With 30 participants, 15 from Ethiopia and 15 from Sudan, and in collaboration with Stanford University; CIPE Africa organized its Leadership Academy for Development #LAD program @AFLEX #African_leadership_excellence_academy , in Addis Ababa, Ethiopia.
Day #2 of the Strategic Management of Policy Reform intensive five-day training workshop which is taking place from June 24 to June 28 @AFLEX #African_leadership_excellence_academy, in Addis Ababa, Ethiopia facilitated by Center for International Private Enterprise and Stanford University’s Leadership Academy for Development. This training program was designed by LAD to stimulate decision-makers in difficult environments as they tackle their countries' most complex economic problems. Participants from Ethiopia and Sudan will work in small groups to analyze policy scenarios and learn about evidence-based decision-making. The training program is provided by Professors Kent Weaver and Ken Opalo .
Day #3 of the Strategic Management of Policy Reform intensive five-day training workshop which is taking place from June 24 to June 28 @AFLEX #African_leadership_excellence_academy, in Addis Ababa, Ethiopia facilitated by Center for International Private Enterprise and Stanford University’s Leadership Academy for Development. Ethiopian and Sudanese students working in groups are presenting interim deliverables of their policy-reform projects. The training program is provided by Professors Kent Weaver and Ken Opalo. Day #4 of the Strategic Management of Policy Reform intensive five-day training workshop which is taking place from June 24 to June 28 @AFLEX #African_leadership_excellence_academy , in Addis Ababa, Ethiopia facilitated by Center for International Private Enterprise and Stanford University’s Leadership Academy for Development. The program case studies are designed in a way to address the Ethiopian Sudanese current contexts. The training program is provided by Professors Kent Weaver and Ken Opalo.
Women participation has been exceptional in the Strategic Management of Policy Reform intensive five-day training workshop which is taking place from June 24 to June 28 @AFLEX #African_leadership_excellence_academy, in Addis Ababa, Ethiopia facilitated by Center for International Private Enterprise and Stanford University’s Leadership Academy for Development
የጠ/ሚ ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት በሲዳማና በትግራይ ክልሎች የበጎ ፈቃድ ፕሮጀክቶችን አስጀመሩ

ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት በዘንድሮው መርኃ ግብር በሲዳማና በትግራይ ክልሎች የሚያከናውኗቸው የበጎ ፈቃድ ፕሮጀክቶች ዛሬ ተጀምረዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ጨምሮ 11 ተጠሪ ተቋማት የተሳተፉበት የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ሥራ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተጀምሯል።

በዚህ መርኃ ግብር ተጠሪ ተቋማቱን በማስተባበር በክልሉ የ20 አቅመ ደካሞችን ቤት ለመገንባት፣ ከ2ሺሕ 500 በላይ ችግኞችን ለመትከል፣ በፅዱ ኢትዮጵያ መርኃ ግብር ደረጃውን የጠበቀ መፀዳጃ ቤት ግንባታ እና ለ1 ሺሕ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ለማበርከት እንድታቀደ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራዎች ካላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ባሻገር ለሃገርና ለዜጎቿ የሚቆረቆር ትውልድን ለመገንባት፤ ጊዜውን፣ ጉልበቱንና ገንዘቡን በበጎ ፍቃድ ለዜጎች የሚለግስ፤ የሃገር ፍቅርና ሃላፊነት የሚሰማው ትውልድን ለመፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል እየተተገበረ ሲሆን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በትግራይ ክልል መቐለ ተገኝተዋል::
👍3
ለኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች‼️

በመጪው በጀት አመት ትልቅ ፈተና ሆኖ ያለወን የኑሮ ውድነትን ለመፍታት ምን ታስቧል፤

የአገሪቷ ኢኮኖሚን በተመለከተ በተለያዩ አካላት የተለያዩ መረጃዎች እየወጡ ነውና ኢኮኖሚው ያለበት ደረጃ እንዴት ይገለጻል፤

የአገሪቷን ሀብት አሟጥጦ ለመጠቀም መንግስት ምን እየሰራ ነው

በኢንዱስትሪ መስከ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ፤

ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ መንግስታዊ አገልገሎትን ማግኘት ያለሙስና የማይቻል እየሆነ ነው። ይህንን ችግር ስር የሰደደ ሙስና ለመፍታት ምን ታስቧል፤ በተደጋጋሚ ቃል ከመግባት ባለፈ ህዝብ ምን ይጠብቅ ፤

የቀጣይ በጀት አመት የዋጋ ግሽበት እንዳይፈጥር ምን ታቅዷል፤

የመንግስት ገቢን ለማሳደግ ምን ታቅዷል፤

ከሀገራዊ ምክክሩ በፊት መቅደም ያለበት መተማመን መፍጠር ነው። በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል፤ የታሰሩ ዜጎችም አሉ። በዚህ ዙሪያ ምላሽ ቢሰጡን፤ ይሄ ባለበት ሁኔታ እንዴት ስለ ምክክር ኮሚሽን ልናወራ እንችላለን፤ መጀመሪያ እመነት መገንባት መቅደም አለበትና መ ንግስት በዚህ ዙሪያ ምን የወሰነው ጉዳይ አለ፤

አገራችን ከውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች በጋራ የከፈቱብንን ጥቃት በመመከት አገራችን አንጸባራቂ ድሎችን እያስመዘገበች ቀጥላላች። ለዚህ ደግሞ የእርስዎ አመራር ትልቅ ድርሻ አለው። ከሰላም አንጻር ምን ለመስራት ታስቧል፤
👍1
የሙስና ችግርን ለመፍታት ምን ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ታስቦዋል፣ በሀገሪቱ የታጠቁ ሀይሎችን ወደ ሰላም ለመመለስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥበት፤

በበጀት እጥረት ምክንያት በአዲስ የተዋቀሩ ክልሎች ለሰራተኞቻቸው ደሞዝ ለመክፈል እየተቸገሩ ነው እነዚህን ክልሎች መንግስት በቋሚነት ለመደገፍ ምን እየተሰራ ነው፣
ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ብሏል - ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው በ2016 በጀት ዓመት በእያንዳንዱ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል፡

የኢትዮጵያ ያለባት የውጭ እዳ ወደ 17 ነጥብ 5 በመቶ ዝቅ ማለቱንም ነው የገለጹት፡፡

በቀጣይ ዓመታት በሚደጉ ርብርቦች ከ10 በመቶ በታች ማውረድ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ላለፉት ስድስት ዓመታት ምንም አይነት ኮሜርሺያል ብድር እንዳልተወሰደም አንስተዋል፡፡
"ከፈተናዎች ውስጥ ዕድልን ፈልቅቆ የማውጣት እና የመጠቀም አካሄድ በመከተል፣ በተቀየረ አመለካከት እና የአሰራር ስርዓት እጅግ ስኬታማ ዓመት አሳልፈናል!"- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ስንዴን ጨምሮ በተኪ ምርቶች ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ስንዴን ጨምሮ በተኪ ምርቶች ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 36ኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት ተችሏል ብለዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ከምርትና አገልግሎት ወጪ ንግድ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም አንስተዋል፡፡

ከሐዋላ አገልግሎትም 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ገቢ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ አሁንም በምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሳቢ አገር መሆኗን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበጀት ዓመቱም 3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መሳብ እንደቻለች ገልጸዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የገቢ ዕቅድ 529 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን በ11 ወራት ውስጥ 466 ቢሊዮን ብር (96 በመቶ) ቢሊዮን ብር ሰብስበናል ሲሉም ገልጸዋል። ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነጻጸር ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቱን አንስተዋል።

ወጭን በተመለከተ 730 ቢሊዮን ብር ወጭ የታቀደ ሲሆን 716 ቢሊዮን ብር (98 በመቶ) በ11 ወራት ውስጥ ተመዝግቧል።
👍2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያና ምላሽ ላይ ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡-

👉እንደ ሀገር ከፍተኛ የእዳ ቀንበር ትከሻዋን ያጎበጣትን ሀገር ነው የተረከብነው፤

👉በቅርብና በሩቅ ያሉ አደጋዎችና ጦሶች ወደ እኛ ሲመጡ የእኛን ኢኮኖሚና ጉዞ ሊገዳደር በሚያስችለው ሁኔታ አደጋ ገጥሞን ነበር፤

👉 የውጭ ጦርነት ብቻ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ያጋጠመን የእርስ በርስ ግጭትና ሌሎች ተደማምረው ለኢኮኖሚ ጉዞው በጣም ፈታኝ፣ ያለሙትን የፈለጉትን ለመጨበጥ በእጅጉ መትጋት የሚጠይቅ ዘመን ሆኗል፤

👉ችግሩን ከዓለም ጋር የምንቋደሰውና የምንወርሰው፣ የምንጋራው ቢሆንም በተለይ የለውጡ መንግስት የገጠመው ተግዳሮት ነበር፤ እንደ ሀገር ከፍተኛ የእዳ ቀንበር ትከሻዋን ያጎበጣትን ሀገር ነው የተረከብነው፣

👉ባለፈው አመትና ቀድሞ በነበረው አመት አጠቃላይ ዓለማችን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ በተከታታይ አንዱ ያመጣውን ጦስ ማብረድ ሳንችል ሌላ ጦስና ሌላ አደጋ፣ ችግር እያስከተለ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ነው ያለነው፤

👉ወረርሽኝ፣ ጦርነቶች፣ በቅርቡ በኛ ቀጠና የገጠመው የቀይ ባህር አካባቢ የገጠመው የዓለም ኢኮኖሚን፣ አጠቃላይ የዓለምን የንግድ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ያወከ ነው፤

ሁከቱም በተሟላ መንገድ ያልረገበ፣ የዓለምን ኢኮኖሚ እየፈተነ ያለበት ሁኔታ ይታያል፤

👉የውጭ እዳ፣ የሀገር ውስጥ እዳ በርካታ ፕሮጀክቶች በምክር ቤት አባላትም ሲገለጹ የነበሩት፣ ብዙ ቃል የተገቡ ግን ፈቀቅ ማለት ያልቻሉ ሰፋፊ ስራዎች የቆሙበት ሁኔታ አለ፤
የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************

የኑሮ ውድነቱ ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሸ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ መንግስት የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ በተለይም የሌማት ትሩፋት ምርሃ ግብር የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

መንግስት የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ባከናወናቸው ስራዎች የዋጋ ንረቱ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እያመጣ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሌማት ትሩፋት ከተጀመረ ሁለት አመት እንኳ ያልሞላው ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከም/ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡
"ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ከውጭ ሀገራት የምትፈልገው የስንዴ እርዳታ ሳይሆን ማሽን፣ ፓምፕ እና እውቀት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ማድረግ ከቻልን የድህነት ምሳሌ የሆነችውን ኢትዮጵያን ስሟን ቀይረን፣ ብልፅግናን አረጋግጠን፣ ለብልፅግና መሰረት ጣልን ማለት ነው፡፡ ደግሞም እናሳካዋለን!!"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አያቶቻችን ቅድመ አያቶቻችን ባቆዩት ጸብ ሲዋጉ ኖሩ አባቶቻችን አያቶቻችን ባቆዩት ጸብ ሲዋጉ ኖሩ እኛ ደግሞ አባቶቻችን ባቆዩት ጸብ እየተዋጋን ጦርነትን አንውረስ