African Leadership Excellence Academy
2.34K subscribers
2.55K photos
96 videos
6 files
119 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በመንግሥት የ2016 ዓ.ም 10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ::

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመንግሥት የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ሰፊ ገለፃ አድርገዋል::

ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ስለ አለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ አዝማሚያ እና ሀገራዊ አፈፃፀም ላይ ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጮች አፈፃፀም ላይም መንግሥት ያከናወናቸውን አበይት ተግባራትን አብራርተዋል::

ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አያይዘውም የመሰረተ ልማት እና የፕሮጀክት አፈፃፀምን በተመለከተ በ10 ወራት ውስጥ መንግሥት የሰራቸውን ስራዎች ጠቅሰው መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት መንግሥት በስፋት እየሰራ እንደሆነና ፕሮጀክቶችም በተያዘላቸው በጀት እና ጊዜ እየተጠናቀቁ በመሆናቸው የመንግስትን አቅዶ የመፈፀም አቅም በጉልህ የሚያሳዩ እንደሆኑ ተናግረዋል::

የማህበራዊ እና የአስተዳደር ዘርፎች አፈፃፀም ላይም መንግሥት ውጤታማ ስራዎችን እንደሰራ የገለፁት ምክትል ርዕሰ አካዳሚው የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍም ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ገልጸዋል::

በውይይቱ ላይ የ2017 ዓ.ም የመንግስት ዋና ዋና አቅጣጫዎች በምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) የተገለፁ ሲሆን የአካዳሚው አመራሮችና ባለሙያዎች ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል::
👍1
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን የለውጥ: የማስፋት እና የሽግግር ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ::

የአፍሌክስ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለአካዳሚው አመራር እና ባለሙያዎች ሲሰጥ በነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት
ባለፉት ስምንት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ለተቋሙ የወደፊት ጉዞ እርሾ የሚሆኑ ስራዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል::

አቶ ዛዲግ እንደተናገሩት ባለፉት ስምንት ወራት የአካዳሚውን መዋቅር እንደ አዲስ በመስራት በሚመለከታቸው አካላት በማስተቸት እና በማስገምገም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስፀድቀው ለድልድል ዝግጁ እንዲሆን ማድረጋቸውን ገልጸዋል::

ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም የአፍሌክስን ግብ እና መዳረሻ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ በርካታ ስራዎች እንደተከናወኑ አስታውሰው የተገኘው ድጋፍም የተቋሙን የገንዘብ እና የሰው ሀይል ችግር የሚፈታ ነው ብለዋል::

የተቋሙን የመሰረተ ልማት ችግር ለመፍታትም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ተቋማት ድጋፍ ባሻገር በመንግሥት ልዩ ውሳኔ የኮንቬንሽን ማዕከል ለመገንባት መታቀዱንም አቶ ዛዲግ ተናግረዋል::

በአፍሌክስ ውስጥ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችንና ህገወጥ ግዥዎችን በመመርመርና ተገቢውን የማስተካከያ ርምጃ በመውሰድ አላስፈላጊ ወጭዎችን በመቀነስ የመንግስት ገንዘብ ለተመደበለት ዓላማ እንዲውል መደረጉንም ፕሬዝዳንቱ አስታውሰዋል::

መላው የአካዳሚው ማህበረሰብም የተቋሙን የለውጥ: የማስፋት እና የሽግግር ፕሮግራሞች በመደገፍ የድርሻውን እንዲወጣም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል::

ከአመራሮች እና ሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችም አቶ ዛዲግ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል::
AFLEX President and Ben Leibowitz, First Secretary, Political British Embassy in Ethiopia, Forge Paths for Transformative Partnership
The African Leadership Excellence Academy president, Mr. Zadig Abreha, recently discussed with Ben Leibowitz, the First Secretary of the Political British Embassy in Ethiopia.
The purpose of their meeting was to explore potential areas of partnership.
During the meeting, Mr. Zadig Abreha provided detailed insights into AFLEX Academy’s reform, scaling up, and transformation plans.
The discussion point was the leadership development projects that AFLEX plans to execute over the next three years.
Mr. Zadig mentioned that the African Leadership Excellence Academy has designed four General and thirty-eight specialized leadership development programs.
He explained that a detailed strategy, consisting of over 2,500 pages, has been prepared for the implementation of these programs.
He also highlighted AFLEX ‘s collaboration with local and foreign stakeholders and expressed the desire to work in cooperation with the UK to achieve their plans.
He emphasized the academy’s mission of bridging the gap between academic rigor and practical worldliness, to unlock the best potential in Ethiopia and Africa.
Mr. Zadig also highlighted the importance of leveraging Ethiopia’s strategic position within the African continent, expressing aspirations for AFLEX to become a community-based organization.
Furthermore, Mr. Zadig Abreha shared information about AFLEX’s initiatives, including the African Davos project in Sululta.
This project envisions Ethiopia as the African capital, reimagining the Davos model for fostering dialogue, dreams, and development on the African continent.
Ben Leibowitz, First Secretary of of the Political British Embassy in Ethiopia, responded positively to the presentation, expressing his appreciation for the insights shared.
Ben Leibowitz also emphasized the importance of women and emerging leader's capacity building and the exchange of experts and encouraged AFLEX to provide detailed research programs.
The First Secretary appreciated AFLEX’s reform, scaling-up, and transformation projects and expressed willingness to support the exchange of experts. Additionally,
He requested that AFLEX provide detailed leadership development program documents to further enhance their initiatives.
Ben Leibowitz also expressed his desire to establish a solid partnership with the African Women and Emerging Leadership Development programs.
In a show of interest and support, Mr. Zadig Abreha and Ben Leibowitz visited the facilities of AFLEX Academy, further solidifying their commitment to exploring potential collaboration between their respective organizations.