የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ሰራተኞች በአካዳሚው ሪፎርም: ማስፋት እና ሽግግር ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ ነው:: ስልጠናውን የሰጡት እሸቴ አበበ (ዶ/ር) ሲሆኑ በአፍሌክስ ውስጥ ሊሰሩ ስለታቀዱ ፕሮጀክቶች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል::
የተቋም እና የግል ልማት በሚል ርዕስም በሞገስ ሎጋው (ዶ/ር) ስልጠና ተስጥቷል::

የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ የአካዳሚውን የአገልግሎት አፈፃፀም ልህቀት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ::
ይህ የተገለጸው ለአካዳሚው አመራሮችና ባለሙያዎች ስለ ተገልጋዮች አገልግሎት አሰጣጥ (Customer Service Delivery, Etiquette and Protocol) ስልጠና በተሰጠበት መድረክ ነው::
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ሲሳይ ዘሪሁን እንደጠቀሱት የአካዳሚውን የአገልግሎት አሰጣጥና የእንግዳ አቀባበል በማሳደግና ዘመናዊ በማድረግ የተገልጋዮችን እርካታ ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልጸዋል::
የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በእቅድ: ክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም የአፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውን የሰጡት አቶ ምትኩ ጫኔ ናቸው::
በስልጠናው ላይም ስለ እቅድ እና ሪፖርት ምንነት እና አዘገጃጀት: ስለ ክትትል እና ግምገማ ስርዓት በሰፊው የቀረበ ሲሆን ስለ ተቋማዊ መዋቅርም ማብራሪያ ቀርቦበታል::

የአካዳሚውን የለውጥ: የማስፋት እና የሽግግር ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ ለውጥን የሚረዳ: የሚያግዝና የሚያስተዳድር የተቋም ማህብረሰብ ለመፍጠር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ተገለጸ::
ለአካዳሚው አመራር እና ሰራተኞች በተዘጋጀው የለውጥ አስተዳደር (Change Management) ስልጠና ላይ እንደተጠቀሰው የአፍሌክስ አመራር እና ሰራተኞች የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ከጫፍ ለማድረስ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ስልጠናውን የሰጡት አቶ ጥላሁን አረጋ ተናግረዋል::
አፍሌክስ የሰነቀው ራዕይ ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ ምድር ሚና እንዲኖረው የሚያስችለው በመሆኑ የተቋሙ ማህበረሰብ ለተልዕኮው መሳካት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ከመድረኩ ተገልጿል::
የአካዳሚው አመራር እና ሰራተኞች በፐብሊክ ሰርቪስ ስነ ምግባር እና ፕሮፌሽናሊዝም (Public Service Ethics and Professionalism) ላይም ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በተቋሙ የሚያጋጥሙ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል የአካዳሚውን ግብ እንዲያሳኩ ጥሪ ቀርቧል:: ስልጠናውን የሰጡት አቶ መስፍን በሃይሉ እንደጠቀሱት ለሙያዊ ስነ ምግባር እና ለህግ ተገዥ በመሆን የተቋሙን ተልእኮ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል::

በመንግሥት የ2016 ዓ.ም 10 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዋና ዋና አፈፃፀም እና የ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮች እና ባለሙያዎች በመንግሥት የ10 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና በ2017 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ሰፊ ገለፃ አድርገዋል::
ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ስለ አለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ አዝማሚያ እና ሀገራዊ አፈፃፀም ላይ ሰፊ ማብራሪያ ያቀረቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ዕድገት ምንጮች አፈፃፀም ላይም መንግሥት ያከናወናቸውን አበይት ተግባራትን አብራርተዋል::
ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) አያይዘውም የመሰረተ ልማት እና የፕሮጀክት አፈፃፀምን በተመለከተ በ10 ወራት ውስጥ መንግሥት የሰራቸውን ስራዎች ጠቅሰው መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት መንግሥት በስፋት እየሰራ እንደሆነና ፕሮጀክቶችም በተያዘላቸው በጀት እና ጊዜ እየተጠናቀቁ በመሆናቸው የመንግስትን አቅዶ የመፈፀም አቅም በጉልህ የሚያሳዩ እንደሆኑ ተናግረዋል::
የማህበራዊ እና የአስተዳደር ዘርፎች አፈፃፀም ላይም መንግሥት ውጤታማ ስራዎችን እንደሰራ የገለፁት ምክትል ርዕሰ አካዳሚው የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍም ሰፋፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ገልጸዋል::
በውይይቱ ላይ የ2017 ዓ.ም የመንግስት ዋና ዋና አቅጣጫዎች በምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) የተገለፁ ሲሆን የአካዳሚው አመራሮችና ባለሙያዎች ላነሷቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል::

👍1