African Leadership Excellence Academy
2.35K subscribers
2.56K photos
96 videos
6 files
120 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
GOAL
To generate world class leaders.
To create premium innovation, learning, research, and collaboration experience
vision of the academy
To be the best African center of excellence in leadership
To raise elite leaders who realize African prosperity.
Contribute to global integration and unity though global partnership.

AFLEX GOAL
👍2
#Upcoming #Event #MoU #Signing
#partnership #AFLEX & #AIBO (Academy for Business Officials)
April 26,2024
#newlogo
👍2
የከተማ አመራሮችን ለማብቃት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
*********

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተማ አመራሮችን ለማበቃት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

በስምምነቱ ወቅት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሀ እንደተናገሩት የከተሞችን እድገት ዘላቂና ውጤታማ ለማድረግ ብቃት ያላቸው ከንቲባዎችና አመራሮች ከማስቀመጥ ባለፈ በየወቅቱ በስልጠናና ትምህርት መደገፍ ይጠበቃል። ይህም በየወቅቱ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅና ከግዜ ጋር ለመራመድ የሚያስችላቸው ይሆናል።

በኢትዮጵያ በቀጥታ ከከንቲባነት ጋር የተያያዘ ስልጠናም ሆነ ትምህርት አልነበረም። አሁን አካዳሚው ያቀረበውና ሁሉንም የሀገሪቱ ከተማ አመራሮች ተደራሽ ለማድረግ የሚሞክረው ይህንን እወቀት ነው ብለዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው እንደተናገሩት ለከተሞች ማደግና መለወጥ ብቁ አመራር ወሳኝ ነው። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን በመረዳት ከሲቪል ሠርቪስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከመጀመሪያ እስከ ሶስተኛ ድግሪ ሲያስተምር ቆይቷል።

ወቅቱን እየተከተለ የሚሠራ አመራር ለመፍጠር ከአጫጭር ስልጠናዎች እስከ ከፍተኛ ደረጃ መስጠት ይጠይቃል። ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር ያደረግነው ስምምነትም ይህንን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችለን ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የከተማ አመራሮች አቅም መጎልበት ሁሉን አቀፍ የከተማ እድገት እንዲኖር ከማስቻል ባለፈ እንደሀገር የተመጣጠነና ተቀራራቢ የከተሞች እድገት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
👍1
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከቻይናው ዓለም አቀፍ የቢዝነስ አካዳሚ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ሥምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ እና የቻይናው ዓለም አቀፍ የቢዝነስ አካዳሚ(AIBO) ፕሬዝዳንት ሱን ዞን ጊህ ፈርመውታል።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በአመራር አቅም ግንባታ ላይ በጋራ ለመሥራት እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት አቶ ዛዲግ አብርሃ በዚሁ ጊዜ አካዳሚው በኢትዮጵያ የአመራር አቅም ለማጎልበት ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ብቁ አመራሮችን ለማፍራት ያግዛል ነው ያሉት።

ቻይናው ዓለም አቀፍ የቢዝነስ አካዳሚ(AIBO) በቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ የንግድ ሚኒስቴር ሥር የሚገኝ የትምህርት እና የሥልጠና ተቋም ነው::
👍1
#AFLEX and the #EmbassyofSwitzerlandindEthiopia Join Forces to #EmpowerAfricanLeaders.
Breaking Boundaries: AFLEX and the Embassy of Switzerland in Ethiopia Unite to Transform African Leadership Development.
AFLEX, in #partnership with various organizations, The Embassy of Switzerland in Ethiopia, is working to empower African leaders through leadership development programs.
In a recent meeting, AFLEX president, #ZadigAbreha, discussed plans for expansion and collaboration with @TamaraMona, Ambassador to Ethiopia and #SouthSudan.
The academy aims to connect African leaders and promote collaboration through its programs. They have already implemented initiatives to empower leaders and set agendas.
Additionally, AFLEX plans to establish an #internationalconferencecenter called #Sululutalike #DAVOS to facilitate connections with leaders from other continents.
During the meeting, Mr. #Zadig asked Ambassador #TamaraMona to explore programmatic cooperation regarding professional experts and infrastructure planning concerning #Davos in Switzerland and its sister city, Sululuta Davos in Ethiopia.
Ambassador Tamara Mona expressed gratitude for the presentation and the support for AFLEX projects and leadership development programs.
Mr. #Zadig presented comprehensive explanations to address questions and ensure clarity on the discussed issues.
👍2
አፍሪካዊያን የሚያስተሳስራቸውን ድልድይ ሊገነቡ ይገባል - ዛዲግ አብርሃ

ለአፍሪካ መጻይ እድል አፍሪካዊያን የሚያስተሳስራቸውን ድልድይ ሊገነቡ እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንትዛዲግ አብርሃ ገለጹ።

የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና ተወካዮች ስለ አካዳሚው ገለጻ አድርገዋል።

በገለጻቸውም የአፍሪካ ልህቀት አመራር አካዳሚ ብቁ አፍሪካዊ መሪዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጸው አፍሪካዊያን በጋራ ሊሰሩ የሚገባበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

አፍሪካዊያን በጋራ የሚሰሩብት እና እርስ በእርስ የሚተሳሰሩበትን መንገድ መፈለግ አለባቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለዚህም አካዳሚው አንደኛው መንገድ መሆኑን አንስተዋል።

አፍሪካዊያን የሚጋሯቸው በርካታ ተመሳሳይ ነገሮች በመኖራቸው ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ አካዳሚውን መጠቀም ይችላሉ ብለዋል።

አካዳሚው አፍሪካዊ ተቋም እንዲሆን ተድርጎ መገንባቱንና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ካሉ የምርምር ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
👍2
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት አድርጓል።
በውይይት መድረኩ ላይ ገለፃ ያደረጉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (አፍሌክስ)ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ፤ አካዳሚው በኢትዮጵያ ብቻ ሳይወሰን በአፍሪካ አህጉር ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በአፍሪካ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማረጋገጥና ብቁ አመራር ለማፍራት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሚና ከጥንት እስካሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ አፍሌክስም ይህንኑ ለማገዝ እየሰራ ነው ብለዋል::
ኢትዮጵያ የቀድሞውን የኬንያ መሪ ጆሞ ኬንያታ እና የነፃነት ታጋዩን ኔልሰን ማንዴላ ማሰልጠኗን አስታውሰው፤ አፍሌክስ ይህንኑ በማስቀጠል በዘመናዊ የአመራር ልማት ማዕከል ውስጥ በርካታ አፍሪካውያን እየሰለጠኑ መሆኑን ተናግረዋል።
አካዳሚው የአፍሪካን ችግር የሚፈታ ብቁ አመራር ለማፍራት በሚያስችል መልኩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት በዘመናዊ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ ሥልጠና ለመውሰድ ከተለያዪ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ገልጸው፤ ይህንን ፍላጎት ተግባራዊ መልስ ለመስጠትም በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
አካዳሚው በአህጉሪቱ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ተናግረው፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ ከ120 በላይ የአፍሪካ አገራት አመራሮች ሥልጠና መውሰዳቸውን ጠቅሰዋል።
👍2
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በተሟላና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የተገነባው አካዳሚው ዓላማውም የሚደነቅ በመሆኑ የሁላችንም ድጋፍና እገዛ ያስፈልገዋል ብለዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ እያደረገች ላለው የላቀ አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን በማቅረብ ሌሎች አገራትም ይህንን መልካም አርዓያ ሊከተሉ ይገባል ብለዋል።