African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
" የአመራር ልህቀት አካዳሚው የኢትዮጵያን ብሎም የአህጉሩን ችግር በዕውቀት ለመፍታት የተመሰረተ ነው" ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)
የኢፌዴሪ ጠ/ሚ/ር
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሴኔት ሐምሌ 09 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ የአንድ ተመራቂ ተማሪን ምረቃን አፅድቋል፡፡
ተመራቂ ተማሪው በህመም ምክንያት ትምህርቱን አቋርጦ እንደነበርና ህክምና አግኝቶ ወደ ትምህርት ተመልሶ አስፈላጊውን የመመረቂያ የሟሟያ ፅሁፍ በጥሩ ውጤት በማጠናቀቁ እንዲመረቅ ከአዳሚክ ዘርፍ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳባ ሴኔቱ ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል፡፡
ሰበር ዜና‼️
የሁለተኛው አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ ጀመረ
**********
ዛሬ ሀምሌ 12ቀን 2013 ዓ.ም የሁለተኛውን አመት የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተገባዶ ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፈሰስ መጀመሩን የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ አሁን በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ ጀምሯል።
"ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም እንኩዋን ደስ አላችሁ። ይህ ውጤት ማለት 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና
ይዘናል ማለት ነው" ሲሉም ነው ሚኒስትሩ ያስታወቁት።
በዘንድሮው አመት እየዘነበ ያለው ውሃ መጠን እጅግ ከፍተኛ ነው፤ ይህም ከፈጣሪ የተሰጠን ፀጋ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነና እንዴት እያገዘን እንደሆነ መረዳት እንችላለን:: ለዚሁም ምስጋና ይግባው።" ብለዋል ሚኒስትሩ።
እዚህ ደረጃ ለመድረስ በዘንድሮው አመት መጠነ ሰፊ ስራ ሰርተናል ያሉት ኢንጅነር ስለሺ፤ በቀጣይ ሁለቱ ተርባይኖች እንዲያመነጩ ብርቱ ስራዎች እየተሰሩ ነው እናም ያንን በቅርብ ወራት በማጠናቀቅ ልፋታችንን ውጤት ላይ እናደርሳለን ብለዋል👍👍👍👍👍👍👍🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች 10ሺ ሜትር ፍጻሜ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ በሰለሞን በረጋ አማካኝነት አገኘች: እንኳን ደስ አለን በአስር ሺ ሜትር ሩጫ ኢትዮጵያ በሰለሞን ባረጋ ወርቅ እንዲሁም በበሪሁን 4ኛ ደረጃን በማግኘታችን በጀግኖቻችን ኮርተናል🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ደንብ ቁጥር 484/2013

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዲሚን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሠላም፣ ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንዴፈ-ኃሳብ የተደገፈ ተግባር ተኮር የአመራር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ብሎም ችግር ፈቺ ምርምር በማካሄድ ሳይንሳዊ የለውጥ ሀሳቦችን በማመንጨት የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ሁለንተናዊ ብልጽግና እና መልካም አስተዳደር ማረጋገጥ የሚያስችል የአመራር ልህቀት አካዲሚ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የልማትና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ በማዋል ተቋማዊና ሀገራዊ ለውጥ በቀጣይነት ማረጋገጥ የሚችል፣ የአሁንና የመጪውን ጊዜ ፈተናና ለውጥ በመምራት የአፍሪካን ዘላቂ ልማትና ትስስር በማምጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ አመራር ማፍራት የሚችል ተቋም አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌደራሊዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 34 መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከጀርመን ኬሄል ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ውይይት አደረገ፡፡
የጋራ ስምምነቱ በአጭር ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በመማር ማስተማር ላይ ያተኮረ መሆኑን የአካዳሚው የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ዘርፍ ም/ፕሬዚደንት ተወካይ ዶ/ር ሰሜነህ ቤሴ አብራርተዋል፡፡
የጀርመን ሀገር ኬሄል ዩኒቨርሲቲን በመወከል በውይይቱ ላይ የተገኙት የዬኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ዶ/ር ኢንድሪያስ ፓተር በተደረገላቸው ገለፃና አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ የጋራ ስምምነቱ ለመምህራን እና ለአመራሩ የልምድ ልውውጥና የአቅም ግንባታ እድል በመፍጠር መልካም አጋጣሚ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
የውይይት ተሳታፊዎችና የጀርመን ኬሄል የዩኒቨርስቲ ተወካዮች የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሱልሉታ ካምፓስ ጉብኝትም አድርገዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነት ፊርማ ስነ-ስርዓቱም በቀጣይ በተያዘለት ጊዜ የሚደረግ መሆኑም ተገልጿል፡፡