African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም፤ ተጠቃሚዎች እና መሰረተ ልማቱን በማስፋት ወደ ሽግግር ለማምራት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተገለጸ።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎች ላይ አስራ ሶስት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ለይቶ ለስምንቱ ቅድሚያ በመስጠት ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የስራ ሀላፊዎች ገልጸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው እንደገለጹት አፍሌክስን ሪፎርም ለማድረግ፤ ለማስፋትና ለማሸጋገር አስራ ሶስት የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን በሶስት ዓመት ውስጥ ለመተግበር የሚረዳ ከ2500 በላይ ገጽ ያለው የስትራቴጂ ሰነድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው ለስምንቱ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ቅድሚያ በመስጠት ወደ ስራ እንደገቡ እና የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም፤ ተጠቃሚዎች እና መሰረተ ልማቱን በማስፋት ወደ ሽግግር ለማምራት በሚደረገው ሂደት ውስጥ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አዎንታዊ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ በበኩላቸው አፍሌክስ ያቀዳቸውን የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት ተቋማቸው ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም አፍሌክስን የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ በሚሰራው ስራ ውስጥ ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ እና የአፍሪካ የፀረ-ሙስና ኤጀንሲ አባል በመሆኗ በቀጣይ የአስተናጋጅነት ሚናውን ስትወስድ በአፍሌክስ ውስጥ ሊሆን የሚችልበት ሰፊ ዕድል አለ ብለዋል።
የንግዱን ዘርፍ በብቃት ለመምራት ልዩ የንግድ አመራር ልማት ፕሮግራም መቀረጹ ለዘርፉ አመራር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል ግምት የሚሰጠው እንዳልሆነ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ክቡር ሚኒስትሩ ገብረ መስቀል ጫላ ገለጹ።
ክቡር ሚኒስትሩ ይሕን የተናገሩት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎቹ ላይ ያቀዳቸው ስራዎች ገለጻ በተደረጉላቸው ወቅት ነው።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ለንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ስለ አካዳሚው የሶስት ዓመት ስትራቴጂ እና ፕሮግራም ገለጻ አድርገዋል። አቶ ዛዲግ እንደጠቀሱት አፍሌክስ የአህጉሪቱን እና የሀገራችንን አመራሮች ለማብቃት ስልጠና ብቻውን በቂ እንዳልሆነ በማመኑ አራት ጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ነድፎ ወደ ስራ እየገባ እንደሆነ ተናግረዋል። በእነዚህ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎች ውስጥም ከፍተኛ አመራሮች አቅማቸውን እንደሚገነቡ እና ሀሳብ እያፈለቁ የምርምር ስራዎችን እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ በበኩላቸው አፍሌክስ ይዞ የተነሳው የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፍ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የሚኖረውን ጥቅም አስታውሰው፤ በተለይም ውድድር የበዛበትን የንግዱን ዘርፍ ለሚመሩ የተቋሙ አመራሮች ልዩ የንግድ አመራር ልማት ፕሮግራም መቀረጹ ከፍተኛ ግብዓት እንደሚሆን ተናግረዋል። ተቋማቸውም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት በቴክኒክ እና በባለሙያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።