African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.5K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከልን በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ለመገንባት መወሰኑን አስታወቀ።
አፍሌክስ እና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረጉት ውይይት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከልን ሱሉሉታ በሚገኘው የአፍሌክስ የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕከል ውስጥ በቅንጅት ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (አፍሌክስ) ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ እንደገለጹት በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ የሚገነባው የፖሊስ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከል (Police Peace Keeping Mission Center) ለሠላም ማስከበር ተግባራት መጠናከርና ለቀጠናው የሚኖረው ሚና ጉልህ መሆኑን ጠቅሰው ግንባታውን ለማስጀመር የሚያስችል ዝርዝር የአፈጻጸም ዕቅድም ከፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን እንዲዘጋጅ ሀሳብ አቅርበዋል።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት የኢትዮጵያ ፌደራል ፓሊስ የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመደገፍ የወሰነውን ውሳኔ አድንቀው በሚገነባው የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከል ውስጥ ለሀገራችን እና ለአህጉሪቷ ሰላም መስፈን አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ሀሳቦች እንደሚመነጩ ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ ማዕከሉ በአፍሌክስ ውስጥ መገንባቱም ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ውስጥ ያላትን የሰላም ማስከበር ሚና እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።
የማዕከሉ ግንባታ በቅርቡ እንዲጀመርም የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአመራር ልማት ፕሮግራም ላይ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚሆን ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን የቀረጸ መሆኑን ገልጸው፤ የዘርፉን አመራርና ባለሙያዎች በአመራር ልማት ፕሮግራም ለማብቃት ከአገልግሎቱ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ የአፍሌክስን የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ማብራሪያ ከተከታተሉ በሁዋላ በሰጡት አስተያየት ተቋማቸው ከአፍሌክስ ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገልጸው በተለይም ከተቋሙ ተልዕኮ አንጻር በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የሀሳብ ማመንጫ ማዕከል ምስረታ ላይ ለመሳተፍ እንደሚፈልጉ እና ለዚህም ስራውን የሚከታተልና የሚመራ የሰው ሀይል መድበዋል።
በአፍሌክስ ጠቅላላ እና ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞች ውስጥም የአገልግሎቱን አመራርና ባለሙያ ለማብቃት እንደሚሰሩ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም በአመራር ልማት ፕሮግራም ሽልማት ላይም ከአፍሌክስ ጋር አብረው በመስራት በዘርፉ ያለውን የአመራር ሀይል ለማብቃትና ለሌላውም ሞዴል የሚሆኑ አመራሮችን ለማፍራት የአፍሌክስ የሽልማት ፕሮጀክት ላይ መሳተፍ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እና በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ በአመራር ልማት ፕሮግራም እና በስትራቴጂያዊ ትብብር ላይ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ የአካዳሚውን የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች በተመለከተ ባቀረቡት ገለጻ ላይ እንደጠቀሱት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያውያንን እና አፍሪካውያንን በአመራር ልማት ፕሮግራም ለማብቃት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በጋራ በትብብር መስራት ተገቢ በመሆኑም የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግም አቶ ዛዲግ ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የደቡብ ኮሪያ ኤምባሲ ቆንስል ጄኔራል ጆ ሱንግ ዉክ JO Sung Wook በበኩላቸው አፍሌክስ ስምንት የአመራር ልማት ፕሮግራም ማዕቀፎችን ቀርጾ ወደ ስራ ለመግባት ዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን ማነጋገሩ እና ድጋፍ መጠየቁን አድንቀው ኤምባሲያቸው የኮርያን ልምድ እና አሰራር በማካፈል በኩል አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
በሀሳብ ማመንጫ ማእከሉ ላይ ሊሰሩ የሚችሉ ባለሙያዎችን እና ሙሁራንን በማነጋገርም የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም ለመደገፍ እነደሚሰራ የገለጹት ቆንስል ጄኔራሉ በፕሮግራም ቀረጻው እና ዲዛይን ላይ አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል። በመሰረተ ልማት ስራ ላይ ለመሳተፍም ተጨማሪ ውይይቶችን ለማድረግ እንደሚፈልጉም ተናግረዋል። አካዳሚውንም ጎብኝተዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ ከተባበሩት መንግስታት ረዳት ጄኔራል ሴክሬታሪ ጋር ተወያዩ።
የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ከዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭ Dr. Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General and UN Resident and Humanitarian Coordinator ጋር በአፍሌክስ ሪፎርም፤ ሽግግር እና ማስፋት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን የአካዳሚው የሪፎርም (Reform)፤ የማስፋት (Scaling Up) እና የሽግግር (Transformation) ስራዎች ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ርዕሰ አካዳሚው አቶ ዛዲግ በገለጻቸው ላይ እንዳብራሩት አካዳሚው ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካውያን የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየሰራ እንደሆነ እና ይህንን ዓላማውን ለማሳካትም አራት የጠቅላላ እና ሰላሳ ሰባት ልዩ የአመራር ልማት ፕሮግራሞችን ቀርጾ በሶሰት ዓመት ውስጥ ለመፈጸም እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።
አፍሌክስን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የልማት ድርጅቶች እንዲያውቁት እና አብረውን እንዲሰሩ እንፈልጋለን ያሉት አቶ ዛዲግ፤ ለዚህም የአፍሌክስን የአመራር ልማት ፕሮግራም በሰፊው በማስተዋወቅ በሀገር ውስጥ ሀብት ብቻ ሊሰሩ የማይችሉ የመሰረተ ልማቶች እና የፕሮግራም ቀረጻዎች ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ዶክተር ራሚዝ በበኩላቸው የአፍሌክስን መሰረተ ልማትና የተቀረጸውን የአመራር ልማት ፕሮግራም አድንቀው ለዚሁ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ እና ሽግግር ዕውን መሆን አብረው ሊሰሩ የሚችሉ ተቋማትን በማፈላለግና ከአፍሌክስ ጋር አብረው እንዲሰሩ ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በሪፎርም (Reform)፤ በማስፋት (Scaling Up) እና በሽግግር (Transformation) ዘርፎቹ ላይ ያቀዳቸውን ስራዎች ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ አመራሮች ገለጻ አደረገ።
ሰንዳፋ በሚገኘው የፖሊስ ዩኒቨርስቲ በመገኘት ገለጻውን ያደረጉት የአፍሌክስ ርዕሰ አካዳሚ አቶ ዛዲግ አብርሃ ሲሆኑ ከከፍተኛ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አመራሮች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም ፌዴራል የፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከሉን በአፍሌክስ ውስጥ ለመገንባት በመወሰኑ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው በማዕከሉ ውስጥም ለሀገራችን እና ለአፍሪካ ሰላም የሚሰሩ ሀሳቦችን በማመንጨት በኩል ሰፊ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ሪፎርም (Reform)፤ ማስፋት (Scaling Up) እና ሽግግር (Transformation) ስትራቴጂ ከሀገር አልፎ ለአፍሪካውያን የአመራር ልማት ፕሮግራም እና የምርምር ማዕከል ለመሆን በሚያስችል መልኩ የተነደፈ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው ከአፍሌክስ ጋር በመስራት ዓላማው እንዲሳካ ያደርጋል ብለዋል።
ፕሬዚደንቱ አያይዘውም የፖሊስ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ማዕከሉም በአፍሌክስ ውስጥ እንዲሆን መወሰኑ ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ ሰላም እና ደህንነት ያበረከቱትን አስተዋጽኦ ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን ለማሳየት ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥር እና አስራ ሁለት የሀሳብ ማመንጫ ማዕከላት ባሉበት ስፍራ ላይ መሆኑ ሰፊ ምርምርና ጥናት ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
ሌሎች የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮችም በሰጡት ሀሳብ ማዕከሉ መገንባቱ ለፖሊስ ሙያ የምርምር ስራ ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።