African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በአፍሪካ እሴቶች የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በአፍሪካ እሴቶች የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አካዳሚው አስታወቀ።
አካዳሚው ስሙን የሚመጥን በፓን-አፍሪካኒዝም የተቃኘ አህጉራዊ ተቋም መሆን የሚያስችል አዲስ ተቋማዊ የማስተር ፕላን ንድፈ ሃሳብ ይፋ አድርጓል።
በአካዳሚው ማስተር ፕላን ንድፈ ሃሳብን ለማቅረብ ከተወዳደሩ 14 የኪነ-ሕንፃ ባለሙያዎች መካከል ለአሸናፊው እና ለተሳታፊዎቹ ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የአካዳሚው ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ዶክተር ወንድዬ ለገሰ፤ አካዳሚው በፓን አፍሪካኒዝም ይዘት ለትውልድ ተሻጋሪ ተቋም የመሆን ግብ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አዲሱ መሪ ፕላን ተቋማዊ ገጽታውን መገንባት እንደሚያስችለው ነው የጠቆሙት።
አካዳሚው ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ለውጥ የሚበጁ አመራሮች የሚፈልቁበት የሀሳብ ልዕልና ማዕከል በመሆኑ፤ የአካዳሚው ገጽታ የአፍሪካን እሴቶች ያንፀበረቀ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
ማስተር ፕላኑ አካባቢያዊ ሁኔታውን ታሳቢ ያደረገ፣ የመሬት ሀብቱን በቅጡ የተጠቀመ፣ አፍሪካዊ ገፅታ ያለው ዘመን ተሻጋሪ ሕንፃ ለመገንባት እንደታቀደም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ማስተር ፕላኑ የአካዳሚውን አህጉራዊ የልህቀት ተቋም የመሆን እንቅስቃሴን ለማሳካት የራሱ ድርሻ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የማስተር ፕላን ሀሳቡ በውድድር መደረጉ በምህንድስና መስፈርቶችን ያሟሉ ግንባታዎችን ለማካሔድ ብሎም ተቋማዊ ገፅታ በመገንባት ሁነኛ ፋይዳ እንደሚኖረው በመጠቆም። (ኢዜአ)
አሁን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች የሳይንስ ሙዝየምን እየጎበኙ ነው
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የአካዳሚውን የልህቀት ጉዞ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ::
በአገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜን አንድ ቀን እንዲከበር የተወሰነውን "የአገልግሎት ቀን" የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች በውይይት አክብረዋል::
በተቋሙ ውስጥ ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ በሚያድግበት እና በሚጎለብትበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የተቋሙን የልህቀት ጉዞ ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ የአካዳሚው የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ገልጸዋል::
ለተገልጋዮችና ደንበኞች የሚሰጠው አገልግሎት ከቅሬታ የፀዳና የመልካም አስተዳደር መርህን የተከተለ መሆን አለበት ያሉት ምክትል ርዕሰ አካዳሚው ተቋሙ ያሉትን ፀጋዎች በማጎልበት በውስንነቶቹ ላይ መስራትና ውጤታማ መሆን ይገባል ብለዋል::
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች በበኩላቸው በተቋሙ ውስጥ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን የጠቆሙ ሲሆን የሚፈቱበትን መንገድም አመላክተዋል::
አገርንና ዜጋን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል ለትውልድ መስራት እንደሆነም በውይይቱ ላይ ተጠቅሷል::
እንኳን አደረሳችሁ!!
መልካም አዲስ ዓመት!!
#2016 ዓ.ም
እንኳን አደረሳችሁ!!
መልካም አዲስ ዓመት!!
#2016 ዓ.ም
Second-round capacity-building training for women
The African Leadership Excellence Academy provided second-round capacity-building training for women in the public sector and government enterprises, middle-level, aspiring, and low-level leaders of different organizations on September 18, 2023, at the academy hall in Sululuta town.
At the opening ceremony of the training, AFLEX Chief of Staff, Mrs. Hanna Atnafu, enlightened that it was a training designed to increase the capacity of the women middle-level leaders of institutions and urged the trainees to turn the knowledge they gained into action when they return to their institution.
Mrs. Hanna stressed that the trainees should work as a team to achieve the vision and mission of their organization and try to make a difference in the lessons they acquire.
They should not only wait for the training to come to them, but they should go and take it, Hana stated.
All through the training, there was a productive discussion between the participants, and it was stated that the group debate and the training were valuable.
In the training, group work was presented by the participants. It is indicated that the training will last from September 18 to September 21, 2016.