African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#AFLEX Positioning
AFLEX is a premier #pan-African leadership institute with a reputation for
#excellence, #integrity, #merit, and #character development
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሕዝብ ጥያቄ መፍትሔን የሚያመነጭ አመራርን መፍጠር ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል - የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

አዲስ አበባ መጋቢት 18/2015 (ኢዜአ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት ለህዝብ ጥያቄ መፍትሔን የሚያመነጭ አመራርን መፍጠር ላይ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ።
በምክር ቤቱ የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአካዳሚውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ገምግሟል።
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የእቅድ፣ በጀትና ሪፎርም ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ጫኔ የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።
በዚህም በግማሽ ዓመቱ ማዕከሉ በአዲስ መልክ መቋቋሙን ተከትሎ ተልዕኮውን በማሳካት ረገድ በርካታ ሥራዎችን አከናውኗል።
በተለይም አጫጭር ሥልጠናዎችን መስጠት፣ የውጪ የትምህርት እድሎችን ማመቻቸት፣ የፖሊሲ ምርምሮችን ማካሄድና ተተኪ አመራሮችን ማብቃት ተጠቃሽ ናቸው።
የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንን ጨምሮ ሥልጠናዎችን በበይነ-መረብ ለማካሄድ የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረጉም እንዲሁ።
ይሁን አንጂ ተቋሙ ከሚጠበቅበት ውጤት አኳያ በቂ ሥራዎች ተሰርተዋል ተብሎ እንደማይታመን አቶ ምትኩ አብራርተዋል።
የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ጥያቄና አስተያየት ሰንዝረዋል።
በተለይም ከተቋሙ ስያሜ አኳያ ፓናፍሪካኒዝምን አጉልቶ በማሳየትና ተደራሽነቱን በማስፋት ረገድ ውስንነቶች እንዳሉ አንስተዋል።
በፌዴራል፣ በክልልና የከተማ አስተዳደር አመራሮችን አቅም ከማሳደግ አኳያ ጎልተው የሚታዩ ሥራዎች አለመከናወናቸውንም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል።
https://www.ena.et/web/amh/w/amh_2632960
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የስድስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሲያቀርብ ኢቢኤስ ቲቪ ተገኝቶ ኹነቱን እንዲህ ዘግቦታል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=8MTdWL9t7us
Special thanks & appreciation to #የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ #African Leadership Excellence Academy for making our 3 weeks conference a success. We leave the academy with #renewed mind & commitment to represent #Ethiopia more. Much appreciation to the coordinators, speakers, staff & coach for the warm welcome, hospitality, ambiance, sports, conducive atmosphere to think & more.
#LOGO MARK
AFLEX logo mark, our symbol, and our message convey several facets of our brand and define who we are. The #butterfly icon represents a #transformation and #infusion of youthful ambition or content tradition, in addition to the icon “X,” which represents #excellence, the attribute of being exceptional and outstanding.
#AFLEX Objective
Ensure a state and nation building processes by providing #leadership trainings and #consultancy services by generating leaders that ensure successful #state and institution building efforts.
ብዙ ጊዜ መሪ የምንለው የፖለቲካና የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ነው፡፡ ነገር ግን በግል ኩባንያዎች፤በፋይናንስ፤በሚዲያ፤በበጎ አድራጎት፤ በሰብዓዊና በዴሞክራሲያዊ መብቶች፤ በህዝባዊ አገልግሎት ዘርፍም መሪዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ በአንድም በሌላም መንገድ አገርን ይመራሉ፡፡
Environmentally friendly Academy
#AFLEX determined to keep environment #smart and #friendly. We have established a #treatment plant and recycled the water for our nursery garden and for the neighborhood community as a way of Corporate Social Responsibility.
This is my second time attending training here at the Academy. Based on my observations, this academy has several good things… they all indicate that it will soon be an #African Center of Excellence. I am sure it will be keep enhancing the service it offers. The facilities and instructors are globally competence. In addition, the sport facilities are refreshing the soul.
Negash Wagesho Dr/Eng
South West Ethiopian Peoples regional state President.
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ወቅታዊና ታሪካዊ የአመራር ተልዕኮ በሚል ርዕስ ለመንግስት ሰራተኞች የተዘጋጀውን የመወያያ ፅሑፉን ያቀረቡት የአካዳሚው የስራ አመራር ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ናቸው፡፡
ም/ል ርዕሰ አካዳሚው የውይይቱን ዓላማ ሲገልፁ የመንግስት ሰራተኞች የለውጡን ስኬት በተገቢው መንገድ በመገንዘብ ውስጣዊና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በብቃት በመሻገር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እንዲተጉ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሀገርን ከመበታተን ያዳነና በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገበው ሀገራዊ ለውጥ የፖለቲካ ምህዳርን ያሰፋ፤ኢኮኖሚውን ከውድቀት የታደገ፤የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ያስቀጠለና ለፈተናዎች ሳይንበረከክ ችግሮችን በብልሀት ተሻግሮ ዛሬ ላይ የደረሰ መሆኑን ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
ሀገራዊ ለውጡ ያጋጠመውን ፈተናዎችና ተግዳሮቶችም በውይይቱ ላይ ተነስተዋል፡፡ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን የሚያሳድጉ ትርክቶች ላይ በበቂ ደረጃ አለመስራት፤የዲሲፕሊን መጓደልና የተጠያቂነት፤ ማነስ፤ከመርህ ማፈንገጥ፤የፅንፈኝነትን አመለካከቶችን ማራመድ፤ የምክንያታዊነት መጓደል፤በወቅታዊ ስሜቶች መነዳት፤ብልሹ አሰራሮችን ለቅሞ አለማረም፤ተገልጋይን ማንገላታት እና እንደ ሀገር የተቀናጀና የተናበበ የኮሙዩኒኬሽን ስርዓት አለመተግበር፤ አንዱ በሌላው ላይ የሚዲያ ዘመቻ መክፈት፤የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት ከሀገራዊ ለውጡ ተግዳሮቶች ውስጥ የሚጠቀሱ መሆናቸውን ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) ጠቅሰዋል፡፡
በቀረበው የውይይት ፅሑፍ ላይ የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ላቀረቧቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶችም ከመድረኩ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡