African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
ውይይቱን የመሩት የአካዳሚው ርዕሰ አካዳሚ ዶ/ር ምህረት ደበበ እንደተናገሩት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት የሚደረገው በሁሉም የመንግስትቋማት ውስጥ መሆኑን ገልፀው ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከሀይማኖት አባቶች የሚተላለፉ መልእክቶች በመንግስት ስራ ውስጥ ክፍተት እንዳይፈጥሩ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ችግሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሁሉም የአካዳሚው አመራርና ሰራተኛ የበኩሉን ሚና እንዲጫወትም ጠይቀዋል፡፡
የስራ አመራር ዘርፍ ም/ል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው በሀይማኖት አባቶች መካከል የተፈጠረውን ችግር ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው የሚሰሩ ሀይሎች እንዳሉ ጠቅሰው የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ በሰከነ መንገድ ሰላም እንዲሰፍን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞችም የተፈጠረው ችግር በሰላም እንዲፈታ መንግስት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
Public Lecture on The African Diaspora and Africa’s Development
Date Feb. 22, 2023
Time 4 pm -5:30 pm
Venue A.A.U Mekonnen Hall
Prof. Hakim Adi
organized by :-
African Leadership Excellence Academy
in Collaboration with Addis Ababa University
የፓን አፍሪካዊነት እሳቤ ዳግም እንዲያንሰራራ ኢትዮጵያ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተካሄደ በሚገኘው የፓን አፍሪካዊነት ፎረም ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ነው።
ኢትዮጵያ የገነባችው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአፍሪካ ወጣት መሪዎችን ለማፍራት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለፓን አፍሪካ መጠናከር የነበራትን ታሪካዊ የመሪነት ሚና አሁንም አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ አረጋግጠዋል።
የፓን አፍሪካ ፎረምን በ2063 የአፍሪካ የልማት አጀንዳ 10 ዓመት እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረት ምስረታ ለ60ኛ ዓመት ክብረ በዓል ወቅት ማዘጋጀቷም ለጉዳዩ ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ፎረሙ ለፓን አፍሪካዊነት መንፈስ እና የአፍሪካ አንድነት እንደ አዲስ ትንሳዔውን እንደሚያበስር ተናገረዋል። የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴውን ዕውን ለማድረግ አዲስ አስተሳሰብ፣ አካሄድ እና ጥበብ እንደሚጠይቅም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ሀገራት ከሰው ሰራሽ መልክዓ ምድራዊ የወሰን ሃሳብ መስመሮች እና ከርዕዮተ ዓለም አጥሮች ወጥተው የተባበረች እና የበገለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ መስራት አለባቸውም ነው ያሉት። በተለይም መሪዎች አጀንዳ የሚቀርጽ፣ ተሻጋሪ ሃሳብ የሚያፈልቅ ችግር ፈች አፍሪካዊ ትውልድ ለመገንባት በአርዓያነት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ የፓን አፍሪካዊነት ዳግም ትንሳኤ እንዲያብብ በቁርጠኝነት እንደምትሰራም አረጋግጠዋል።
የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካዊነት ፎረም በአካዳሚው ተከናውኗል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ትውልዱ በስፋት ሊያስቀጥለው እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ።
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተካሄደው የመጀመሪያው የፓን አፍሪካኒዝም ፎረም ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ፓንአፍሪካኒዝም በ21ኛው ክፍለዘመን ትርጉሙ የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ማስቀረት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በምግብ እራሷን ለመቻልና የበለፀገች አገር እንድትሆን በርትታ እየሰራች መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፤ ባለፉት ዓመታት ለአረንጓዴ አሻራ ትኩረት ሰጥታ መስራቷን ገልፀዋል።
እንደ አቶ ደመቀ ገለፃ፤ የአረንጓዴ አሻራ መርሀግብር አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ አለው፡፡
አፍሪካ የመሬት መሸርሸር እንዲሁም ድርቅና ርሀብ የጋራ ችግሮቿ ናቸው ያሉት አቶ ደመቀ፤ ለዚህም ትውልዱ የአረንጓዴ አሻራን ጥቅም ተገንዝቦ በስፋት ሊያስቀጥለው እንደሚገባ መክረዋል።
በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡት የኢትዮጵያ የደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር አደፍርስ ወርቁ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የካርቦን ልቀትን በመቀነስ የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ትልቅ ሚና እንደሚኖረውም ጠቅሰዋል።
መርሃ ግብሩ ጎረቤት ሀገራት ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ እንዲሰሩ ለማድረግ አስፈላጊ ነው ያሉት ዶክተር አደፍርስ፤ የግጦሽ መሬት፣ የውሃና የደን ሃብት እጥረት ችግሮችን ለመፍታት አስችሏል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በተካሄደው የፓን አፍሪካኒዝም ፎርም የተሳተፉ የሀገራት መሪዎች፤እንዲሁም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራው ልኡክ በአካዳሚው ችግኞችን ተክሏል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በአረንጓዴ አሻራ ላይ የተሳተፉ የአፍሪካ አገራት መሪዎችና አምባሳደሮች