African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
AFLEX Females Staff. (አንበሲት) (ጀግኒት)
አዲስ አበባ ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም (አአልአ)፡- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (AFLEX) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) በጋራ ለመስራት የውል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ሁለቱ ተቋማት በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት እንደተገለፀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የካውንተር ኢንተለጀንስ አገልግሎት (Counter Intelligence Service) የሚሰጥ ሲሆን፤ አካዳሚውም ለሚያገኘው አገልግሎት ለአስተዳደሩ ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል፡፡ የውል ስምምነቱ ለሁለት አመት የሚቆይ ሲሆን በዚህም የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና አጠቃላይ የአካዳሚውን የሥራ ቦታ ከየትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ጥቃት ሊያጋልጡ የሚችሉ ክፍተቶችንና ተጋላጭነቶችን ለመከላከል የሚያስችል የካውንተር ኢንተለጀንስ ቴክኒካል አገልግሎት (Proactive and event based counter espionage service) በኢመደአ በኩል የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ስምምነቱን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እና የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ፈርመዋል፡፡
በስምምነቱ ላይ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ ሕይወት አለማየሁ እንደተናገሩት አካዳሚው ከኢትዮጵያ አልፎ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችን የሚያሰለጥን ተቋም በመሆኑ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችም ይሁኑ አጠቃላይ የአካዳሚው ቅጥረ ግቢ ከየትኛውም አይነት የኤሌክትሮኒክስ ጥቃት ስጋት ነጻ መሆኑን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የአስተዳደሩ ዋና ተልዕኮ የተቋማትን የኢንፎርሜሽን ደህንነት ማረጋገጥ ሲሆን ይህንንም መነሻ በማድረግ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ከኢንፎርሜሽን ጥቃት ለመከላከልና ደህንነቱን ለማስጠበቅ የሚያስችል የካውንተር ኢንተለጀንስ ቴክኒካል አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የቴክኖሎጂ አቅምም ይሁን ብቃት ያለው የሰው ሃይል ኢመደአ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የአፍሌክስ አመራሮችና ሰራተኞች ኢንሳን ሲጎበኙ
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራርና ሰራተኞች በመቂ የስንዴ የኩታ ገጠም ማሳን ሲጎበኙ