African Leadership Excellence Academy
2.29K subscribers
2.47K photos
96 videos
6 files
114 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
መስና በሃገር አቀፍ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ያለበትን ሁኔታ እና የሚያስከትለውን ጉዳት በአሃዛዊ መረጃዎች አስደግፈው በማብራራት ስልጠናውን የጀመሩት ዶክተር ተስፋዬ ሙስና የሃገር ኩራት የሆኑ ተቋማት ሳይቀሩ እንዲጠፉ እስከማድረግ የሚደርስ በሃገር እና በህዝብ ላይ የተጋረጠ አደጋ መሆኑን አመላክተዋል።

በቅድሚያ በሁሉም ዘንድ ግልጽ የሆነ የጋራ አመለካከት ከተያዘ ይህንን ጎጂ ተግባር ለመከላከል ይበልጥ አመቺ እንደሆነ ተናግረው "ይህ ስልጠና የአመራር ልማት ላይ የሚሰራው አፍሌክስ የጸረ ሙስና ተግባርን ከስራው ጋር በማስተሳሰር ሙስናና ብልሹ አሰራርን የሚታገል አመራር ማፍራት እንዲችል ክህሎት ማስጨበጥ ነው!" ብለዋል።

ስልጠናው ሁሉም ተሳታፊ የተለያዩ ሃሳቦችን እንዲያነሳና እንዲወያይ በሚያስችል መልኩ አሳታፊ ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አፍሌክስ አፍሪካዊ ተቋም መሆኑን በተግባር ያስመሰከረበት ዕለት



የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታን በመዘከር የአህጉሪቷን ችግሮች እና የመፍትሄ ሀሳቦች የተመላከተበት



አፍሪካውያን ወጣቶች ስለ መፃኢ እድሎቻቸው የመከሩበት ልዩ ኮንፈረንስ



አፍሪካውያን እህትማማቾችና ወንድማማቾች በአፍሪካዊቷ ዳቮስ ሱሉልታ በጋራ የመከሩበትን ጉባኤ ሙሉ



ቪዲዮ በአፍሌክስ ፌስቡክ ገፅ እና ዩቱዩብ ቻናል በቅርቡ ይጠብቁ!!
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ ለ1446ኛው የአረፋ (ዒድ አል አድሃ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
እንኳን ለ1446ኛው የአረፋ(ዒድ አል አድሃ) በዓል አደረሳችሁ
#የኢትዮጵያ_ወደብ_አልባነትን_አምኖ_የተቀበለ_ትውልድ_ወደ_ወደብ_ያስፈልገናል_የሚል_እምነት በአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ
👉 ግዛቶች የሚወድቁትም የሚነሱትም በመሬት በባህር እና በጎረቤት ሃገራት አማካይነት ነው
👉 የሰው ልጅ አዲስ አለም እየፈጠረ ነው
👉 የባህር በርን የበለጠ አስፈላጊ የሚያደርገው ለቀውስ የማይበገር መሆኑ ነው
👉 የባህር በር ሲኖር የሰብአዊ እርዳታ በፍጥነት እንዲደርስ ያደርጋል
👉 ስትራቴጂክ ወደብ የተፅእኖ ማዕከል ነው
👉 ወደብ አልባ መሆናችን ሊያስቆጣን ብቻ
ሳይሆን መልሰን ስለማግኘት ማሰብ አለብን
👉 የባህር በር አልባ ሀገራት ማደግ እና መበልፀግ ይችላሉ?
ዛሬ ማታ 1፡00 ላይ በአካዳሚው ፌስቡክ ገጽ እና ዩቱዩብ ቻናል ላይ https://www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca ይጠብቁን!!
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የአፍሌክስ ሕንጻዎችን የሪኖቬሽን እና የማዘመን ሥራን ለመስራት ተስማማ
****

አዲስ አበባ ሰኔ 04/2017 (አፍሌክስ):- የፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን ሕንጻዎችን የማስዋብ እና የማዘመን ሥራ ለመስራት ስምምነት ፈጽሟል፡፡

የማስዋብ እና የማዘመን ሥራው አፍሌክስ የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ምቹና ዘመናዊ ለማድረግ እንደሚያስችለው ተገልጿል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ፡- አፍሌክስ በመጠን ከፍተኛ ለሆነው የሪኖቬሽን ሥራ ኮርፖሬሽኑን መምረጡ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሚታወቅበት ውጤታማ የፕሮጀክት አፈጻጸም በውሉ በተቀመጠው የማጠናቀቂያ ጊዜ አጠናቆ እንደሚያስረክብም ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በዚህ ፕሮጀክት ትርፍን ሳይሆን ለጥራት እና ለጊዜ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥም ተናገረዋል፡፡
ስምምነቱ የሰልጠኞች ማደሪያ ሕንጻ እድሳት ፣ የመመሪያ ክፍሎች ሕንጻ እድሳት እና የምድረ ግቢ ማስዋብ ሥራን የሚያካትት ግዙፍ የማስዋብ እና የማዘመን ሥራ እንደሆነ ተገለጿል፡፡

በዘርፉ ያካበተውን ልምድና ብቃት መሰረት አድርገው ኮርፖሬሽኑን እንዲሰራ ተቋማቸው መወሰኑን ዶ/ር ወንድዬ ለገሠ የአፍሌክስ ምክትል ፕሬዜዳንት ተናግረዋል፡፡

የማስዋብና የማዘመን ሥራውን በጥራት እና በጊዜ አጠናቆ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለማስረከብ ለያዘው እቅድ ከአፍሌክስ በኩል አስፈለጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ምክትል ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የበርካታ የመንግስት ተቋማትን የሪኖቬሽንና የማዘመን ሥራዎች በብቃት በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን ለመግስት ተቋማት በጥራት እና በጊዜ የማዘመን ሥራዎችን ከመሰራት ባሻገር የሪኖቬሽን ሥራ የተቋሙን ገቢ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
The president of the Somali region, Mr. Mustafe Muxummed Cumar has closed a four-day training of the leadership of the party and the regional government held by the office of the Prosperity Party in the Somali region with the support of the African Leadership Training Institute (African Leadership Excellence Academy).

The president advised the leadership to come up with determination and hard work, to strengthen the jobs and service of the society— the party and the government will continue their role in developing the knowledge of leadership.

The president said that the plans of the government will focus on: strengthening security, completing the ongoing projects, quality of education, revenue, justice, rehabilitation of cities and resting places etc.