African Leadership Excellence Academy
2.15K subscribers
2.38K photos
90 videos
6 files
105 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ በበኩላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዋና ተልዕኳቸው ከመማር ማስተማር ፣ከምርምር እና ከማሕበረሰብ አገልግሎት በተጨማሪ ወቅታዊ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ ውይይቶች ፣ስልጠናዎችና ዓውደ ጥናቶች ማካሄዳቸው አስፈላጊ መሆኑን አውስተው ዲላ ዩኒቨርሲቲም ክቡር አቶ ዛዲግን በመጋበዝ በወቅታዊ ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሰፊና ጥልቅ ስልጠና መስጠቱን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ ክቡር አቶ ዛዲግ ዩኒቨርስቲው ባቀረበላቸው ጥያቄ ከፍተኛ የስራ መደራረብ ቢኖራቸውም ቅድሚያ በመስጠት የዳበረ እውቀትና ልምዳቸውን ተጠቅመው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች በትጋትና በቅንነት ለሰጡት ስልጠና ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ክቡር አቶ ዛዲግ በዛሬው የስልጠና ውሎ ትምህርትና መፃኢ ዕጣ ፈንታ ፣ከፍተኛ ትምህርትና መፃኢ ዕጣፈንታ፣ ትምህርትና የመምህራን ሚና፣ የልዕለ ሃያልነት ጂኦፖለቲካና መፃኢ የዓለም ዕጣ ፈንታ እንዲሁም ለልዕለ ሃያልነት የሚያበቁ ሁኔታዎች በሚል ርእሰ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት የተያዘው የስልጠና መርሐግብር በስኬት ተጠናቋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ ሰልጣኛች መካከል መምህር አሸናፊ አስራት በሰጡን አስተያየት ስልጠናው በወቅታዊ ሁኔታዎች በተለይም በቴክኖሎጂ ዕድገት፣ በትምህርት መፃኢ እድልና የባህር በርን በተመለከተ ጥሩ ግንዛቤ የተገኘበት መድረክ እንደነበር ተናግረዋል።

ስልጠናው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ካውንስል አባላት፣ አንጋፋ መምህራንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም የተከበሩ አቶ ዛዲግ አብረሃ ባለፉት ስድስት ቀናት በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች በሰጡት ስልጠና እና ገለጻ ባበረከቱት አስተዋጽኦ የባህል አልባሳት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ሰራተኞች በአፍሌክስ ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው።

ሚያዝያ 28/2017 (አፍሌክስ) -
ለ300 አዲስ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች በተለያዩ ሀገራዊና ተቋማዊ ርዕሰ ጉዳዮች በአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።

ስልጠናው ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 2/2017 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ስለተቋሙ ገለጻ አድርገዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በመክፈቻው ላይ የስራ መመሪያ ሲሰጡ፣ ተቋማችን ከያዘው ግብ አንዱ ለማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሀገር ደህንነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል። ይህም ወደ አገር የሚገባውና ከአገር የሚወጣው ሰው ትክክለኛነትን በማረጋገጥ፣ አገርን ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም ተቋምን መገንባት የመንግስት ስርዓት ግንባታ አካል በመሆኑ ሰልጣኞች በ’እንችላለን’ መንፈስ መስራት ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የተቋሙ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና የዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ፣ በየዘርፋቸው ያሉትን ተግባራትና ተጨማሪ የስራ መመሪያ ለሰልጣኞች ሰጥተዋል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአመራር ስልጠና ለሀገር ጉልበት ሆነናል- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ(አፍሌክስ) ምክትል ፕሬዝዳንት መሰረት ደስታ @EthiopianNewsAgency
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ለመሪዎቹ ''የመሪነት ጥበብ'' ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሥልጠናው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ ይህን ስልጠና ያዘጋጀነው ሚዲያው እና መሪዎቹ ሕዝብ እና መንግሥት የሰጣቸውን ኀላፊነት በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ አርበኞች ሀገራቸውን ከወራሪዎች የተከላከሉበትን ጀግንነት እና ጽናት አንስተዋል። በዚህም ኢትዮጵያን ማስከበራቸውን ጠቅሰው ዘመኑ የሚጠይቀው አርበኝነት ደግሞ ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ኀላፊነቱን መወጣት እንደኾነ ገልጸዋል።

የዘመኑ ጠላታችን ድህነት እና ልመና ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን እንደ ቀደምት አርበኞች ሁሉ በአሸናፊነት ለመወጣት ጠንክሮ መታገል እንደሚገባ ነው የተናገሩት። የሚዲያ ሠራተኞችም በዚሁ ቅኝት እንዲሠሩ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭት ተፈትቶ ክልሉ ወደ ቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ ሚዲያው ለሠራው ሥራ እውቅና ሰጥተው በቀጣይም ድህነትን ለማሸነፍ ለሚደረገው ጥረት የሚዲያውን አቅም የመጠቀምን አስፈላጊነት አንስተዋል።

ዶክተር ዘሪሁን የሕዝብ ዐይን እና ጆሮ የኾነውን አሚኮን በመጠቀም ልማትን በማፋጠን ድህነትን ለማሸነፍ እንሠራለንም ነው ያሉት።
#የጀመሩትን_የመጨረስ_ሳይንስ_ጥበብ_መሰረታዊ_እና_ሁሉን_አቀፍ_ለውጥ_የማስመዝገብ_ሃይል - ከግለሰብ እስከ ሃገር- በዛዲግ አብርሃ

The science and the art of finishing - from individual to national endeavors

❗️አለም ባልተጠናቀቁ ጅምሮች የተሞላች ናት።

❗️ታሪክ የሚሸልመው ጀማሪዎችን ሳይሆን የጀመሩትን የሚጨርሱትን ነው!

ዛሬ ማታ በአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል እና ፌስቡክ ገጽ ይጠብቁን
አፍሌክስን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለማግኘት ከታች ያሉ ሊንኮችን ይጠቀሙ

https://shorturl.at/1Pirn
https://www.tiktok.com/@aflex_academy?_t=ZM-8t1gJsnIFgT&_r=1
https://x.com/Afleexacademy?s=09
https://t.me/afleexac
https://web.facebook.com/@aflexacademy.gov.et
https://aflexacademy.gov.et
http://www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca
Africa Day 2025: Investing in Our Future - Coming Soon!

The future of Africa is education!

Be part of a pivotal moment at the #Africa_Day_2025 commemoration, hosted for the second time by AFLEX in the dynamic town of Sululta, Ethiopia. On May 24th.

Occasion: 62nd anniversary of the OAU/AU

Event: Africa Day 2025 Commemoration

Theme: 'Education for All: Empowering Africa's Future'

📆 May 24, 2025

Location: AFLEX, Sululta, Ethiopia

Key Attendees: AU Commissioners,
Ministers, University Presidents, Scholars, Youth Leaders

Prepare to engage with a diverse and influential audience of 300 participants, including high-profile guests and panelists from across the continent.

And, we have a surprise guest lined up to make this event even more special!

Keynote addresses, dynamic panel discussions, youth-led policy dialogues and Networking opportunities await you on this significant day!

Ready to shape Africa's future through education Be there on May 24th at AFLEX in Sululta❗️
"አሚኮን መለወጥ እና ማሻሻል ክልሉን በሁለንተናዊ መንገድ ማሻሻል ነው" አቶ ዛዲግ አብርሃ

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር "የመሪነት ጥበብ" በሚል መሪ ሃሳብ ለኮርፖሬሽኑ መሪዎች ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና አጠናቅቋል፡፡ ሥልጠናው የዕውቀት፣ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ክፍተትን ከመሙላት ባሻገር ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡