African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
#የሀሳብ_ኃይል_እና_ዕጣ_ፈንታችን_ከግለሰብ_እስከ_ሀገር

👍 በአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ ዛሬ #በፌስቡክ_ገጻችን https://web.facebook.com/aflexacademy.gov.et እና #በዩቱዩብ_ቻናላችን www.youtube.com/@AfricanLeadershipExcellenceAca ይጠብቁን!!

👍 አንድ ሀሳብ ተቀባይነት ካገኘ ሌሎች ሀሳቦችን ያዋልዳል

👍 ሀሳብ ያለው ሰው ዋጋ ይከፍላል

👍 አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች መሪን እና ተከታይን የመለየት አቅም አላቸው

👍 ሀሳብ ከፈጣሪው በላይ ተሻግሮ ለዘላለም ይኖራል

👍 ሀሳብ ሰዎችን ያገናኛል። በሀሳብ የተገናኘ እና የተዋሀደ ሰው የሚፈጥረው ግንኙነት የማይበጠስ ነው

👍 ሀሳብ ድንበር አልባ ነው። ገደብም የለውም። በብሔር፤ በሀይማኖት እና በዘር አይታጠርም።

👍 ሀሳብ ምንም በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ተዓምር የመፍጠር ኃይል አለው

👍 ሀሳብ ሰዎችን ያነሳሳል፤ ተስፋን ይፈጥራል፤ ችግርን የመፍታት አቅም ስላለው ተዓምራዊ ነው።
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት ዛዲግ አብርሃ #የሀሳብ_ኃይል_እና_ዕጣ_ፈንታችን_ከግለሰብ_እስከ_ሀገር በሚል ርዕስ ለአመራሮች የሰጡትን የአመራር ልማት ስልጠና ከአካዳሚው ዩቱዩብ ቻናል እና የፌስቡክ ገጽ ይከታተሉ። በዩቱዩብ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

https://www.youtube.com/watch?v=PcP5ZeCCOl4

ፕሬዚደንቱ ስለ ሀሳብ ኃያልነት እና ስለ ዕጣ ፈንታችን ካነሷቸው ቁም ነገሮች ውስጥ በጥቂቱ፡-

👍 አንድ ሀሳብ ተቀባይነት ካገኘ ሌሎች ሀሳቦችን ያዋልዳል

👍 ሀሳብ ያለው ሰው ዋጋ ይከፍላል

👍 አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች መሪን እና ተከታይን የመለየት አቅም አላቸው

👍 ሀሳብ ከፈጣሪው በላይ ተሻግሮ ለዘላለም ይኖራል

👍 ሀሳብ ሰዎችን ያገናኛል። በሀሳብ የተገናኘ እና የተዋሀደ ሰው የሚፈጥረው ግንኙነት የማይበጠስ ነው

👍 ሀሳብ ድንበር አልባ ነው። ገደብም የለውም። በብሔር፤ በሀይማኖት እና በዘር አይታጠርም።

👍 ሀሳብ ምንም በሌለበት ሁኔታ ውስጥ ተዓምር የመፍጠር ኃይል አለው

👍 ሀሳብ ሰዎችን ያነሳሳል፤ ተስፋን ይፈጥራል፤ ችግርን የመፍታት አቅም ስላለው ተዓምራዊ ነው

👍 ሀሳብ ዘር ነው ፣ ፍሬ ነው፤ ውሀ ቢጠጣ ያድጋል፤ የሁሉም ፈጠራዎች እና ስልጣኔዎች መነሻቸው ሃሳብ ነው

👍 ሀሳብ የማፍረስም የመገንባትም አቅም ያለው ነው

👍 አንድ ሰው መሪ የሚሆነው በሀሳብ የላቀ ሲሆን ነው
"የባህር በር ያላት ሀገር የምትነካው ውሃ ብቻ ሳይሆን የዓለምን የልብ ትርታ ነው"

አቶ ዛዲግ አብረሃ

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብረሃ በወቅታዊ ሀገራዊ እና አለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እየተሰጠ ያለው በዛሬ ትኩረቱን በውሃ እና በባህር በር ጥቅሞች ዙሪያ አድርጎ ውሏል።

የተከበሩ አቶ ዛዲግ አብረሃ፣ የባህር በር ያላት ሀገር የምትነካው ውሃ ብቻ ሳይሆን የዓለምን የልብ ትርታ መሆኑን አውስተው የባህር በር የንግድ ስርዓትን የሚቆጣጠር በመሆኑ የንግድ ስርዓትን መቆጣጠር ደግሞ እድገት እና ብልፅግናን እውን ያደረጋል፤ የበለፀገ ሀገር ደግሞ በዓለም ከፍተኛ ተሰሚነት ይኖረዋል።

አቶ ዛዲግ አያይዘውም የምድራችንን 70 በመቶ የሚሸፍነው ውሃ የጥንታዊ ስልጣኔዎች መነሻ፣ የብዝሀ ህይወት መገኛ፣ 90 ከመቶ የዓለም ንግድ መንቀሳቀሻ እና የጂኦፖለቲካዊ ኃያልነት መወሰኛ በመሆኑ የባህር በር ባለቤት የሆነች ሀገር የአለምዓቀፍ ንግድ ስበት ማዕከል ያላት፣ ብሄራዊ ኩራቷ ከፍ ያለ፣ ሰላምና ፀጥታ የሰፈነባት፣ ፈጣን የወጪ እና ገቢ የንግድ እንቅስቃሴ ያላት እና ስትራቴጂካዊ ላእላዊነቷን ያረጋገጠች እንደምትሆን ገልጸው በተቃራኒው የባህር በር የሌላት ሀገር ደግሞ እንኝህን ጥቅሞች እንደምታጣ ሰፊ ማብራሪያ አቅርበዋል።

በነገው ዕለትም ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት አጋጣሚ፣ የባህር በር ባለቤትነትን ለመመለስ የተደረጉ ጥረቶች እና ቀጣይ ሂደቶች ላይ አተኩሮ ስልጠናው ይቀጥላል።
በወቅታዊ ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

ዲዩ ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ በወቅታዊ ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ ላለፉት ስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ተጠናቀቀ።

ክቡር ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳደሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውና መጪውን አቅጣጫ ማስቀመጥ መቻላቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንትና ማኔጅመንት በዘርፉ ከፍተኛ እውቀትና ልምድ ያላቸውን አቶ ዛዲግን በመጋበዝ በወቅታዊ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ ጉዳዮች ስልጠና እንዲሰጥ በማድረጋቸው በጌዲኦ ዞን አስተዳደርና በዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ዶክተር ዝናቡ አያይዘውም፣ እኛ ኢትዮጵያን የምንገባበትና የምንወጣበት በር ተቆልፎብን እንድንኖር ሰብአዊ መብታችን ስለማይፈቅድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን የባህር በር እንድናገኝ የበኩላቸውን ሚና መውጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ በበኩላቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዋና ተልዕኳቸው ከመማር ማስተማር ፣ከምርምር እና ከማሕበረሰብ አገልግሎት በተጨማሪ ወቅታዊ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ ውይይቶች ፣ስልጠናዎችና ዓውደ ጥናቶች ማካሄዳቸው አስፈላጊ መሆኑን አውስተው ዲላ ዩኒቨርሲቲም ክቡር አቶ ዛዲግን በመጋበዝ በወቅታዊ ሀገራዊና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለተከታታይ ስድስት ቀናት ሰፊና ጥልቅ ስልጠና መስጠቱን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ ክቡር አቶ ዛዲግ ዩኒቨርስቲው ባቀረበላቸው ጥያቄ ከፍተኛ የስራ መደራረብ ቢኖራቸውም ቅድሚያ በመስጠት የዳበረ እውቀትና ልምዳቸውን ተጠቅመው በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች በትጋትና በቅንነት ለሰጡት ስልጠና ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

ክቡር አቶ ዛዲግ በዛሬው የስልጠና ውሎ ትምህርትና መፃኢ ዕጣ ፈንታ ፣ከፍተኛ ትምህርትና መፃኢ ዕጣፈንታ፣ ትምህርትና የመምህራን ሚና፣ የልዕለ ሃያልነት ጂኦፖለቲካና መፃኢ የዓለም ዕጣ ፈንታ እንዲሁም ለልዕለ ሃያልነት የሚያበቁ ሁኔታዎች በሚል ርእሰ ጉዳይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት የተያዘው የስልጠና መርሐግብር በስኬት ተጠናቋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ ሰልጣኛች መካከል መምህር አሸናፊ አስራት በሰጡን አስተያየት ስልጠናው በወቅታዊ ሁኔታዎች በተለይም በቴክኖሎጂ ዕድገት፣ በትምህርት መፃኢ እድልና የባህር በርን በተመለከተ ጥሩ ግንዛቤ የተገኘበት መድረክ እንደነበር ተናግረዋል።

ስልጠናው የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ካውንስል አባላት፣ አንጋፋ መምህራንና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም የተከበሩ አቶ ዛዲግ አብረሃ ባለፉት ስድስት ቀናት በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች በሰጡት ስልጠና እና ገለጻ ባበረከቱት አስተዋጽኦ የባህል አልባሳት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ሰራተኞች በአፍሌክስ ስልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው።

ሚያዝያ 28/2017 (አፍሌክስ) -
ለ300 አዲስ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ሰራተኞች በተለያዩ ሀገራዊና ተቋማዊ ርዕሰ ጉዳዮች በአፍሪካ አመራር ልሕቀት አካዳሚ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው።

ስልጠናው ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 2/2017 ዓ.ም ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

የአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ም/ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ስለተቋሙ ገለጻ አድርገዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሰላማዊት ዳዊት በመክፈቻው ላይ የስራ መመሪያ ሲሰጡ፣ ተቋማችን ከያዘው ግብ አንዱ ለማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የሀገር ደህንነት ማስጠበቅ ነው ብለዋል። ይህም ወደ አገር የሚገባውና ከአገር የሚወጣው ሰው ትክክለኛነትን በማረጋገጥ፣ አገርን ከመጠበቅ አኳያ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልፀዋል።

ዳይሬክተሯ አክለውም ተቋምን መገንባት የመንግስት ስርዓት ግንባታ አካል በመሆኑ ሰልጣኞች በ’እንችላለን’ መንፈስ መስራት ይኖርባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የተቋሙ የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ እና የዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ፣ በየዘርፋቸው ያሉትን ተግባራትና ተጨማሪ የስራ መመሪያ ለሰልጣኞች ሰጥተዋል፡፡
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በአመራር ስልጠና ለሀገር ጉልበት ሆነናል- የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ(አፍሌክስ) ምክትል ፕሬዝዳንት መሰረት ደስታ @EthiopianNewsAgency
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ለመሪዎቹ ''የመሪነት ጥበብ'' ሥልጠና እየሰጠ ነው።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሥልጠናው ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ ይህን ስልጠና ያዘጋጀነው ሚዲያው እና መሪዎቹ ሕዝብ እና መንግሥት የሰጣቸውን ኀላፊነት በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ አርበኞች ሀገራቸውን ከወራሪዎች የተከላከሉበትን ጀግንነት እና ጽናት አንስተዋል። በዚህም ኢትዮጵያን ማስከበራቸውን ጠቅሰው ዘመኑ የሚጠይቀው አርበኝነት ደግሞ ሁሉም በተሰማራበት ዘርፍ ኀላፊነቱን መወጣት እንደኾነ ገልጸዋል።

የዘመኑ ጠላታችን ድህነት እና ልመና ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን እንደ ቀደምት አርበኞች ሁሉ በአሸናፊነት ለመወጣት ጠንክሮ መታገል እንደሚገባ ነው የተናገሩት። የሚዲያ ሠራተኞችም በዚሁ ቅኝት እንዲሠሩ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭት ተፈትቶ ክልሉ ወደ ቀደመ ሰላሙ እንዲመለስ ሚዲያው ለሠራው ሥራ እውቅና ሰጥተው በቀጣይም ድህነትን ለማሸነፍ ለሚደረገው ጥረት የሚዲያውን አቅም የመጠቀምን አስፈላጊነት አንስተዋል።

ዶክተር ዘሪሁን የሕዝብ ዐይን እና ጆሮ የኾነውን አሚኮን በመጠቀም ልማትን በማፋጠን ድህነትን ለማሸነፍ እንሠራለንም ነው ያሉት።