African Leadership Excellence Academy
2.13K subscribers
2.38K photos
89 videos
6 files
104 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
‘የመጋቢት 24 ትሩፋቶችን ከኢትዮጵያ ትንሳኤና ከህዝባችን ህልምና መሻት ጋር አስተሳስሮ መመልከት አስፈላጊ ነው’ ወ/ሮ መሰረት ደስታ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2017 ዓ.ም (አፍሌክስ)፡- ‘የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች’ በሚል መሪ ቃል የለውጡ መንግስት በሰባት ዓመታት ውስጥ ያከናወናቸውን አኩሪ እና እመርታዊ ድሎችን የተመለከተ ውይይት ተካሄደ። ውይይቱ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በአፍሌክስ ዋናው ቢሮ ተከናውኗል።

በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአስተዳደር እና ቢዝነስ ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወንድዬ ለገሰ (ዶ/ር) በውይይቱ መክፈቻ ላይ ተገንተው ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ሰባት አመታት የተካሄደው ፖለቲካዊ ለውጥ ፤ በኢኮኖሚ ላይ የተደረገ ማሻሻያ ፤ በሀገራችን ያለውን የለውጡን ቀጣይነት ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ሪፎርምን ማእከል ያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።

በአፍሌክስ የአመራር ልማት ዘርፍ ምክትል ርዕሰ አካዳሚ ወ/ሮ መሰረት ደስታ የመጋቢታውያን የለውጥ ፍሬዎችና የነገ ተስፋዎች በሚል ርዕስ ባቀረቡት የጽሁፍ ገለጻ ላይ መጋቢት 24 በሀገራችን ታሪክ ሁለት ታላላቅ ሁነቶች የተስተናገዱበት ቀን መሆኑ ጠቅሰው፤ ይኸውም መላው የሀገራችን ህዝቦች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ፖለቲካዊ ለውጥ የተደረገበት እና የለውጡ መሪ ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀገራችንን ለማስተዳደር ቃለ መሃላ የፈጸሙበት መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ መሰረት ባቀረቡት ጽሁፉ ላይ እንደገለጹት አስተሳሳሪ እና የወል ትርክት ለዘላቂ አንድነት እና አብሮነት የሚኖረውን አዎንታዊ በረከት ጠቅሰው፣ ሀገራችንን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር የተሰሩ ስራዎችን በስፋት ተናግረዋል።

አምራች ኢንዱስትሪን በማስፋፋት የኢትዮጵያን ምርታማነት ማሳደግ ላይም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል እየተሰሩ ያሉ ሰፋፊ ስራዎችን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት መግለፅ ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያበረክተውን ጉልህ ሚና የጠቀሱት ወ/ሮ መሰረት የሀገራችንን ጸጋ ለሀገራችን ብልጽግና የመጠቀም መሻት የደረሰበትን ደረጃ አንስተው፤ የማዕድን ዘርፍ ዕድሎች፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጥረቶችና ትሩፋቶቹ ላይም የመንግስትን የአፈጻጸም ውጤቶች አብራርተዋል።

የሀገራችንን ከተሞች የማዘመን ትልምና የኮሪደር ልማት ፍሬዎች በሚሉ ርዕሶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የመጋቢት 24 ትሩፋቶችን ከኢትዮጵያ ትንሳኤና ከህዝባችን ህልምና መሻት ጋር አስተሳስሮ መመልከት አስፈላጊ እንደሆነ ወ/ሮ መሰረት ደስታ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

ከአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶችም መልስ እና ማብራሪያ ከመድረኩ ተሰጥቶባቸው የውይይቱ ፍጻሜ ሆኗል።
Ⓒⓞⓜⓘⓝⓖ ⓢⓞⓞⓝ
የሀሳብ ኃይል እና ዕጣ ፈንታችን -ከግለሰብ እስከ ሀገር -
አቶ ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
Ⓒⓞⓜⓘⓝⓖ ⓢⓞⓞⓝ
የተስፋ፤ የፍራቻና የተስፋ መቁረጥ ስሜቶችን ታግሎ በማስወገድ ነገሮችን ከሰረ መሰረታቸው የመቀየር ሚስጥር

አቶ ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
Ⓒⓞⓜⓘⓝⓖ ⓢⓞⓞⓝ
ለውጥ-ከሀይሉ እስከ መሰረታውያኑ
(The Power and the Fundamentals of Change)

አቶ ዛዲግ አብርሃ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
በቅርብ ቀን ይጠብቁ!
የአፍሌክስ ፕሬዚደንት አቶ ዛዲግ አብርሃ #የትልቁ_ሥዕል_ሀይልና_የምንገኝበት_አውድ - ከግለሰብ እስከ ሀገር-
በሚል ርዕስ የሰጡትን ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የዩቱዩብ ቻናል ለመከታተል ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
#የትልቁ_ሥዕል_ሀይልና_የምንገኝበት_አውድ - ከግለሰብ እስከ ሀገር- በአቶ ዛዲግ አብርሃ የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#ትልቁ_ሥዕል ትንሹን አይስተውም:: ትንሹ ግን #ትልቁን ሊስተው ይችላል::
#ትልቁ _ሥዕል_የዓላማ_ማቀጣጠያ_ነዳጅ_ነው::
#ትልቁን_ሥዕል የሚመለከት ሰው #ዓላማንና_ርዕይን ይጋራል: #ትብብርና_ፉክክርን #በሚዛን_ይመለከታል::
#ትልቁን_ሥዕል እያየ የሚሰራ አመራር እና ሰራተኛ አሻራውን እያኖረ እንደሆነ ያውቃል::
#በትልቁ_ሥዕል ላይ ግንዛቤ ያለው አመራር እና ሰራተኛ የዓላማ ግልፅነት ይኖረዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=DMKMQ0bjXkQ
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለአካላዊ ጥንካሬ፣ ለአዕምሯዊ ንቃትና ለጤንነት ጉልህ ፋይዳ አለው።

ዛሬ ማለዳ "ልህቀት በሰው ተኮር አገልግሎት" በሚል መሪ ሀሳብ ስልጠና እየወሰዱ ከሚገኙ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ኳስ ጨዋታ አድርገናል።

እንደዚህ ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በአማራሩ መካከል ያለውን ግንኙነትን በማጠናከር የተሻለ አንድነትን ይፈጥራሉ፦

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #Ethiopia