African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና በመከታተል ላይ ለሚገኙት ዲፕሎማቶች ባቢሎን በሳሎን ቲያትርን ተጋብዘው እየተመለከቱ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ ለምናከናውነው የአመራር አቅም ግንባታ ስራ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
በዛብህ ገ/የስ
የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
‹‹አካዳሚውን ከጠበኩት በላይ ነው ያገኘሁት፤ ሁሉም ነገር የተሟላ ነው፡፡በሌሎች ሀገሮች የምናያቸውን አይነት ትልልቅ ተቋማት በሀገራችን ማየት ትልቅ ኩራት ነው›› ደጀኔ በቀለ
በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአስተዳደርና ፋይናንስ ዳይሬክተር
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰልጣኞችን ተቀብሎ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠቱ ምስጋና እና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ሽልማቱን ሲያበረክቱ እንደተናገሩት ለተደረገላቸው መልካም አቀባበልና መስተንግዶ በተቋማቸውና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ለአካዳሚው የተሰጠውን ሽልማትም የተቋሙ ፕሬዚደንት አቶ አወሉ አብዲ ተቀብለዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ውስጥ ስልጠና መውሰድ ጀምረዋል፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አፈወርቅ ካሱ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት አካደሚው የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አድንቀው የልህቀት ማዕከል በሆነ ተቋም ውስጥ ስለ ትምህርት ጥራት መወያየት ልዩ ስሜትን የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና ከወሰዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰልጣኞች መካከል ስለ አካዳሚው ጠይቀናቸው ይህን ብለውናል፡-
‹‹ወደ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከመጣን ጊዜ ጀምሮ ጥሩ አቀባበል ተደርጎልናል፤ የጊቢው ንፅህና፣ ሁሉም አገልግሎት ስታንዳርዱን የጠበቀና ስልጠናችንን በአግባቡ እንድንከታተል ምቹ ሁኔታን ፈጥሮልናል ለዚህም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡ እኛም ሃላፊነታችንን ተወጥተን የሁላችን የሆነውን ንብረት መጠበቅና መንከባከብ አለብን፡፡››
የትናየት ከተማ
ከሚሲዮን ተመላሽ ዲፕሎማት
‹‹አካዳሚው የተሟላ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተገንዝብያለሁ፤ ስልመናው የሚሰጥበት አዳራሽና የመኝታ አገልግሎቱ የተሟላ ነው፡፡››
ቦል
በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማት /በፕሮቶኮል ዘርፍ/
የአፍሪካ አመርር ልህቀት አካዳሚ ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (Korean International Cooperation Agency /KOICA) ጋር በመተባበር የእውቀት ሽግግር ሴሚናር እያካሄደ ነው፡፡
ሴሚናሩን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚው የስልጠና ዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ስዩም መኮንን አካዳሚው በ2013 ዓ.ም የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን ማከናወኑን በማስታወስ ይህ ሴሚናር ብቃትን መሠረት ያደረገ የአመራር ስልጠናና ምዘና ስርዓትን በሃገራችን ለመትከል ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ተሞክሮ የሚቀሰምበት ከመሆኑም በተጨማሪ ከተቋሙ ጋር ግንኙነት በማጠናከር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታን ለመፍጠር የሚረዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኮይካን በመወከል በሴሚናሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ሊ ሱንጆ ተቋሙ ወደ አፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ መቀየሩን አድንቀው የኮሪያ ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ስልጠና የአካዳሚውን የለውጥ ጉዞ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ይህ ሴሚናር የእውቀት ሽግግርን በማስፋት የተሳካ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡›› ሲሉም አክለዋል፡፡
በሴሚናሩ ላይ በአቶ ጥላሁን አረጋና በእሸቴ አበበ (ዶ/ር) ሁለት ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡት ላይ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ክቡር አቶ አወሉ አብዲ የአካዳሚያችን ፕሬዚደንት ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያቶች ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ቀጣይ የስራ ዘመንዎም የስኬት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻ መርሃ ግብርን አከናወኑ፡፡
አሸባሪው የህወሀት ቡድን በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ለአሜሪካ መንግስትና ለመላው አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማድረስ ያለመውን ዘመቻ የአካዳሚው አመራርና ሰራተኞች የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት ” መርሀ ግብርን አከናውነዋል፡፡
የአሜሪካ መንግስት በሃገራችን ላይ እያደረገ ያለውን ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻ መርሃ ግብርን ሲያከናውኑ እንደተገለፀው 128 የሚሆኑ የአካዳሚው አመራሮችና ሰራተኞች “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት” ዘመቻን ተቀላቅለው ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአሜሪካ መንግሰት በአሸባሪው ህወሃት ቡድን የተጋረጠብንን አደጋ ለመመከት የሚደረገውን ትግል ለማደናቀፍና በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ለመግባት የሚያደርገውን ሙከራ እንዲያቆም ተጠይቋል። የተፈረመው ፖስታም ለአሜሪካ መንግሰት ተልኳል፡፡