African Leadership Excellence Academy
2.3K subscribers
2.49K photos
96 videos
6 files
116 links
የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ሁለንተናዊ ሰላም ዲሞክራሲና ልማት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና ካላቸው ወሳኝ አካላት አንዱ አሰተማማኝ አቅም ያለው አመራር መኖር በመሆኑ፤ ተከታታይና ሁሉን አቀፍ የአመራር ልማት በሁለም ደረጃ ማካሄድ አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በንድፈ-ኃ
Download Telegram
ክቡር አቶ ስዩም መኮንን የአካዳሚያችን የስልጠና ዘርፍ ምክትል ፕሬዚደንት ሆነው በቆዩባቸው ጊዜያቶች ላደረጉልን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡ ቀጣይ የስራ ዘመንዎም የስኬት እንዲሆን እንመኛለን፡፡
ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚን በሚመለከት ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ሃሳቦች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሚከተለውን ሃሳብ ሰጥተዋል፡፡
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ከዚህ ቀደም እንደነበረው አይነት ሳይሆን ተቋሙን የሚመጥኑ ብቃት ያላቸውንና ከፓርቲያችን ወጣ ብለን የተሻለ ብቃት ያላቸውን ሰዎች አምጥተን እያደራጀነው ነው፡፡
ዶ/ር ምህረት ደበበ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል
በየአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የሚሰጡ ስልጠናዎች ውጤታማ እንዲሆኑና የታሰበውን ግብ እንዲያሳኩ የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነዉ::
የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የ 2013/14 ዓ.ም የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን የመመረቂያ ጽሁፎች ግምገማ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንትና ፈታኞች በተገኙበት መጀመሩን ከአካዳሚክ ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአዲሱ መንግስት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው
በአዲሱ መንግስት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በዚህ ስልጠና መክፈቻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ገለጻ÷ አመራሩ በንፁህ እጅና በቅንነት ሀገሩን ማገልገል አለበት ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው ኢትዮጵያ ያሏትን ሃብቶች በአግባቡ በማልማት፣ በትጋት በመስራትና በንፁህ እጅና በቅንነት መሆኑን ተናግረዋል።

አመራሮች ከስለጠናው በኋላም የዓላማ ጽናት በቡድን የመስራት መንፈስና በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርባቸዋል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።