#StockMarket
ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ የ ' ስቶክ ማርኬት ' ስራ እንደሚጀመር ተገለፀ።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚጀምረውን የ ' ስቶክ ማርኬት ' ለመደገፍ ከወዲሁ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ስቶክ ማርኬት በከፍተኛ ደረጃ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ይደግፋል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " በጣም ብዙ ሰው ሃሳብ አለው ገንዘብ የለውም፤ ጥቂት ሰዎች ደግሞ ገንዘብ አላቸው ሃሳብ የላቸውም ፤ ጥቂቶች ደግሞ ገንዘብ አላቸው ሃሳብም ገብቷቸዋል ተቋም የላቸውም ፤ ስቶክ ማርኬት ማለት ገንዘብ ያለውን ሃሳብ ያለውንና ተቋምን የሚያገናኝ ምርጥ ሀሳብ ማለት ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
" ለአብነት ፦
- በአረብ ሀገራት ያሉ እህቶች ' ስቶክ ማርኬት ' ውስጥ ሼር ገዝተው እዛ እየሰሩ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚችሉ ፤
- አርሶ አደሮችም ከስቶክ ማርኬት ሼር ገዝተው እያረሱ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ ፤
- ዲያስፖራዎችም ወደ ሀገር ሲመለሱ ምንም የሌላቸው እንዳይሆኑ ከወዲሁ ዋና ዋና ኩባንያዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ " ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ዐቢይ ፤ ቴሌኮሚኒኬሽን በቅርቡ የተወሰነ ፐርሰንት ለህዝቡ እንደሚሸጥ አሳውቀዋል።
በሂደት ቴሌን፣ አየር መንገድን የህዝብ ተቋማት የማድረግ ስራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።
" እኛ ሂልተንንም፣ ጊዮንንም፣ አየር መንገድንም፣ ቴሌኮምን ይዘን አንዘልቀውም " ያሉ ሲሆን እነዚህ ኩባንያዎች ላይ ብዙዎች ኢንቨስት እንዲያደርጉበት ካደረግን የተሻለ እድገት ሊያመጡ ይችላሉ፤ ለኢትዮጵያ እድገትም እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት ምክር ቤቱ ከወዲሁ ድጋፍ ለማድረግ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።
#etstocks

በቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እየተነቀሳቀሰ ነው
ቴሌ ብር ለኢትዮጵያ ዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እንዳሉት÷ቴሌ ብር በደንበኞች ቁጥር ብዛትም ሆነ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ከፍተኛ እድገት እያስመዘገበ ነው፡፡
እንደ ኤፍ ኤም ሲ ዘገባ አሁን ላይ በቴሌ ብር በቀን 7 ቢሊየን ብር እንደሚንቀሳቀስ ገልጸው ይህም ለዲጂታል ኦኮኖሚ ግንባታ ሚናው ጉልህ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ቴሌ ብር አዳዲስ መተግበሪያዎችን እና አሰራሮችን በመፍጠር ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቴሌ ብር ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እንዲሰጥም ከሳይበር ደህንነት ጋር በተያያዘ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን ነው የገለጹት፡፡
#Etstocks