ET Securities
655 subscribers
578 photos
7 videos
28 files
290 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
#ECMA
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ባለስልጣን ሃና ተኸልኩን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሾመ!

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያን ባለስልጣን ሃና ተኸልኩን ዋና ዳይሬክተር አድርጎ ሲሾም በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ብሩክ ታዬን (ዶ/ር) ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ ተቀብሏል

ላለፉት ሁለት ዓመታት የካፒታል ገበያ ባለስልጣንን ከማቋቋም ጀምሮ በዋና ዳይሬክተርነት ሲመሩ በነበሩት ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) ምትክ በህግ እና በኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች ላይ ሰፊ ልምድ ያላቸውን ሃና ተኸልኩን አዲሱ ዳይሬክተር አድርጎ መቀበሉን አስታዉቋል ።

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የመጀመሪያ እና የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ መሾማቸው ተሰምቷል።

ብሩክ ታዬ የኢትዮጵያ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 27 የሚደርሱ የመንግስት ኩባንያዎችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን ላለፉት ሁለት ዓመታት በስራ አስፈፃሚነት በመሩት አብዱረህማን ኢድ ጣሂር ምትክ መሾማቸው ለማወቅ ተችሏል ።

Please follow and like us:
Fb.me/etstocks
X.com/etstocks1
YouTube.com/@etstocks
Website:- condoaddis.com/category/etstocks