ET Securities
661 subscribers
588 photos
7 videos
28 files
298 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
ET Securities
Photo
#የሐሳብ_መድረክ

IMF ዓለማው ምንድነው ? ቢሊዮን ዶላሮች ደግፎ / አበድሮ ምን ይጠቀማል ?

(በኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ)

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ 190 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ ድርጅት ነው። ትልልቅ ሼር ያላቸው ሀገራት አሉ። የድርጅቱ ገንዘብ በነዚህ ሼር ካላቸው ሀገራት የሚገኝ ነው።
- አሜሪካ 17.43%
- ጃፓን 6.47%
- ቻይና 6.4%
- ጀርመን 5.59%
- ፈረንሳይ 4.23%
- እንግሊዝ 4.23% ...አላቸው። ሌሎችም ሁሉም ገንዘብ አላቸው በድርጅቱ።

ኢትዮጵያም የIMF አባል ናት።

IMF የተቋቋመው በዓለም ላይ የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓትን ለመገንባት ነው። ለዚህም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ድጋፍ ለማድረግ ነው የተመሰረተው።

በዚህ ምክንያት በየሀገሩ ሪፎርም እያዘጋጀ ይቀርባል ' ይሄን ይሄን አድርጉ ' እያለ ወይም የቀረበለትን እየገመገመ ' ይሄን አድርጉ ይህ እንዲሆን ' ይላል። ትክክል ሲመስለው ያጸድቃል ካልሆነ ውድቅ ያደርጋል።

ኢትዮጵያም ወደ IMF የሪፎርም አጀንዳ ሰንድ ይዛ ቀርባለች። 3 ዓመታት ያህል ሰነዱን ሲገመግም ቆይቶ አሁን አጽድቋል። ሲያጸድቅ ግን የራሱንም መስፈርቶች አስቀምጦ ነው ወደ ተግባር የገባው።

የIMF ስም ከ ' floating exchange rate ' ጋር የሚነሳውም ለዚህ ነው።

እውነት ግን IMF ለሀገራት ስለሚያስብ ነው ? ወይስ በእጅ አዙር ሌላ አላማ አለው ? ይህ ነው ትልቁ መከራረከሪያ ነጥብ።

ይህ መከራከሪያ ጉዳይ ዓለም አቀፋዊ ነው።

IMF ስለ እራሱ የሚለው ምንድነው ? ስራዎቹን በመልካም ጎኑ የሚያዩት አካላት የሚሉት ምንድነው ?

- ዓለም ላይ ባሉ ሀገራት ተወዳዳሪነት ያለበት የኢኮኖሚ ስርዓት እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- የዓለም ኢንቨስትመንት ያለምንም እንቅፋት እንዲንቀሳቀስ ነው የምፈልገው።
- ገንዘብ በመላው ዓለም በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ እፈልጋለሁ። ... ይላል።

በዚህም ፤ " ምቹ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያለበትን ሀገር መፍጠር ነው የምፈልገው በየሀገራችሁ ይህን ፈጥርላችኋለሁ " ነው የሚለው።

ስለዚህ መንግሥት ፦
ቁጥጥር ይቀንስ
የገበያው ቁጥጥር ይቀንስ
ጣልቃ እየገባ መቆጣጠሩን ያቁም
የግል ሴክተሩን መቆጣጠር ያቁም
ኢምፖርት ላይ የሚወጣው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ይቀንስ
ኤክስፖርት ላይ ያለ ቁጥጥር ይቀንስ
ታሪፍ፣ ኮታ አጠቃላይ ቁጥጥር ስርዓት ይቀንስ
አሳሪ ህጎችን አላሉ
ንግድን ፣ ኢንቨስትመንትን የማያበረታታ ህጎችን አላሉ
ፉክክር የማያበረታት ህግ አላሉ
ፕራቬታይዤሽን እንዲኖር አድርጉ
መንግሥት ቁጥጥር ስር ያሉ ተቋማት ወደ ግል ይዙሩ
ሊበራይዜሽን ይጠናከር / በሞኖፖል የተያዙትን ዘርፎች ክፍት አድርጉ (ለምሳሌ ፦ ቴሌ ሊሆን ይችላል)
ማንም ከውጭ አይገባም የሚለውን ቀንሱ ፤ ፉክክር ይኑር
የችርቻሮ ገበያ ይከፈት ፣ የውጭ ባለሃብቶች ይግቡ ፣ ይፎካከሩ
ዋጋ መተመን ገበያ ውስጥ እየገባ እራሱ መሸጥ ሚናዎችን መቀነስ አለበት
ገበያው ለገበያው ይሰጥ
የዋጋ ንረት መቆጠር አለባችሁ
የበጀት ጉድለት አስተካክሉ
መልካም አስተዳደር እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ተቋማት ይገንባ

IMF የጠበቀ የቁጥጥር ስርዓት ቀላል የሆነ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ስለሚያደርግ የኢኮኖሚ እድገት አይፈጥርም ባይ ነው።

ስለዚህ ለናተው ሲባል " በኢኮኖሚ እንድታድጉ፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራችሁ " ነው ይህን ማድረግ ያለባችሁ የሚለው።

በኢኮኖሚ መርህ ተመሩና ሀገራችሁ እዲያድግ እፈልጋለሁ ነው የሚለው።

የሀገራት የእድገት አቅጣጫ እንዲስተካከል ይፈልጋል።

በዚህም ከድህነት የወጣ ሀገር ይመሰረታል ፣ ሁሌ የማይበደር ሀገር ይፈጠራል፣ ኢንቨስትመንት ጤነኛ የሆነበት፣ ምቹ ሀገር መፍጠር ይቻላል የሚል ሐሳብ አለው።

በመሆኑም የማክሮ ኢኮኖሚያ የመምራት አቅማችሁ ደካማ ከሆነ የምትመሩበትን ሁኔታ ይዤ መጣለሁ፣ የገንዘብ ፖሊሲው ጤነኛ ካልሆነ እኔ አግዛለሁ፦
• በቴክኒክ
• ፈንድ በማድረግ
• ብድር በመስጠት
• ብድር በማራዘም አግዛለሁ ይላል።

ስለዚህ " ራሳችሁን ችላችሁ ትቆማላችሁ ፣ ከመለመን ትወጣላችሁ ፣ ሁሌ አትበደሩም ፣ ዓለም አቀፍ እዳችሁ ይቀንስላችኋል፣ ለንግድ ለኢንቨስትመንት የምትመቹ ሀገር ትሆናላችሁ ያን ማድረግ ነው የምፈልገው ነው " የሚለው።

ሙስና እንዲቀንስ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲኖር ይፈልጋል።

IMF ይሄን ያደርጋል ብሎ የሚከራከሩለት አሉ።

IMF የሪፎርም ሰነዶቹን ለተለያዩ ሀገራት ነው የሚያቀርበው።

                                   ---

"IMF በእጅ አዙር ሌላ ዓላማ ነው ያለው" የሚሉ አካላት ምን ይላሉ ?

IMF ያደጉ ሀገራት ያሉበት ሼር ነው። ስለዚህ ያደጉ ሀገራት ድሃ ሀገራት ላይ ፍላጎታቸውን መጫን ይፈልጋሉ።

ብዙ ብድር በመስጠት የሚፈልጓትን ሀገር ተቆጣጥረው መያዝ ይፈልጋሉ።

እዳ ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ መያዝ። በብድር ሰብሰብ መያዝ።

ብድር እና ድጋፍ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ይፈልጋል።

በየሀገሩ እየሄደ " ልርዳችሁ " የሚለው በብድር ሰበብ ረጅም አመት በእዳ መያዝ ይፈልጋል።

ለአንድ ሀገር ብዙ ብድር ያውም ከእፎታ ዘመን ጋር ፣ ከዛም ምንም ወለድ የሌለበት ብድር ሲሰጥ ረጅም ዓመት ሀገሪቱ በእዳ ውስጥ እንድትቆይና በዛ ሀገር የፈለገውን ነገር ለመጫን እድል እንዲሰጠው ነው።

በእዳ የሚይዘው ያደጉት ሀገራት የድሃ ሀገራትን ማዕድን፣ ገበያውን ለምዕራባውያን መስጠት ስለሚፈልግ ነው።

ፊት ለፊት ከሚያደርጉት ስምምነት በተጨማሪ ከጀርባ የሚያደርጉት ስምምነት አለ። ያደጉ ሀገራት ድርጅቶቻቸው ያላደጉ ሀገራት ሄደው፦
° ማዕድን እንዲያገኙ
° ገበያ በቀላሉ እንዲያገኙ እድል እና ጫና የመፍጠር አዝማሚያ አለው።

እዳ ውስጥ የተዘፈቀ ሀገር በፖለቲካ በኩል የሚመጣለትን ፦
° ተጽኖ
° ጫና
° መከራከሪያ ሁሉ እንዲቀበል የማድረግ መሳሪያ ነው። አንዳንድ ሀገራት ግጭት ውስጥ ሲገቡ (ህልውናቸውን ለማስጠበቅም ቢሆን እንኳ)፣ ሰላምና መረጋጋት ሲርቃቸው እርዳታ እና ብድር ይይዛል። አይሰጣቸውም።

ዓላማው እድገት ብቻ አይደለም።

ተመሳሳይ ሪፎርም ለበርካታ ሀገራት ይሰጣል። ይህ የሀገራቱን ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ለግብጽም፣ ለናይጄሪያም፣ ለኢትዮጵያም የሚመክረው ተመሳሳይ ነው። ብዙ ድሃ ላለበት ሀገር እና ትንሽ ድሃ ላለበት ሀገር ተመሳሳይ ምክር ይሰጣል።

ምሳሌ ፦ ድጎማ #እንዲቀንስ_ያበረታታል። በደካማ ኢኮኖሚ ያለው ሀገር ሳይቀር መንግስት ከድጎማ ወጥቶ ገበያው በራሱ እንዲንቀሳቀስ ይመክራል። ይሄ ደግሞ በርካታ ሰዎች ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውጭ ይሆናሉ።

ነጻ ገበያ እያለ ያውጃል ግን ያላደጉ ሀገራት እሱን ሲሞክሩ ብዙ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ የሚገቡ ማህበረሰቦች ይፈጠራሉ።

የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመጠበቅ እንኳን መንገድ እንዳይኖር ልቀቁት ይላል። በዚህም ትንንሽ አማራቾች ከውጭ በሚመጣ ምርት እና አምራች ጋር መፎካከር አቅቷቸው ከንግድ ውጭ ይሆናሉ።

ምክሮቹ ድህነትን የሚያበረታቱ የመሆን እድል አላቸው።

በሚል የሚከራከሩ አሉ።

IMF ግን አንዳንድ ሪፎርሞች ሁሉ ወዲያው ለውጥ እንደማያመጡ በማመን የራሱ መከራከሪያዎች አሉት።

ያንብቡ: https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-04

@tikvahethiopia