ET Securities
643 subscribers
560 photos
6 videos
26 files
283 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
#Vacancy

If you are passionate in regulatory compliance, market oversight, or financial supervision, and want to contribute to building a strong, transparent capital market in Ethiopia—this is your opportunity!

Apply now using the below link.
https://ethiojobs.net/job/fV61CpAz5Q-market-supervision-officer
#ለመረጃ፦ ከሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ ተለውጧል! ቤንዚን ከ112.67 ወደ 122.53 ብር አድጓል!
ኢትዮ ቴሌኮም ለንግድ ድርጅቶች እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሰጭዎች የአጋርነት ጥሪ አቀረበ

ግዙፉ መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢ የሆነዉ ኢትዮ ቴሌኮም በትላንትናው ዕለት ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም. "ዘመን ገበያ" የተሰኘ ሀገር አቀፍ የዲጂታል የገበያ ቦታን በይፋ ካስጀመረ በኋላ፣ ከዚህ ፕላትፎርም ጋር ለመተባበር ፍላጎት ላላቸው የንግድ ድርጅቶች እና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ሰጭዎች ጥሪ አቅርቧል ።

ኩባንያው ከዘመን ገበያ ጋር ለመስራት ባቀረበው ጥሪ መሰረት፣ ከ42 በላይ የተለያዩ የንግድ ድርጅቶች እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ሰጭዎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ።

"ዘመን ገበያ" የኢኮኖሚ እድገትን በማፋጠን፣ የስራ እድል በመፍጠር፣ ዲጂታል አካታችነትን በማስፋፋትና የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል።

ተቋሙ እንዳስታወቀው በቀጣይም የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሳደግ ከሚፈልጉ አካላት ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

ይህ የዲጂታል መድረክ ለአምራቾችና ለአገልግሎት አቅራቢዎች ሰፊ የገበያ ተደራሽነትን እንደሚያረጋግጥ፣ የሥራ ማስኬጃ ወጪን እንደሚቀንስ፣ ከደንበኞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለመገንባት እንደሚያግዝ እንዲሁም የዲጂታል ክፍያ መፍትሄዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጥቅሞችን ይሰጣል ተብሏል።

ለሸማቾች በበኩሉ ሰፋ ያሉ የምርትና የአገልግሎት አማራጮችን፣ ምቹና ተደራሽ ግብይትን እንዲሁም ተወዳዳሪ ዋጋዎችን ያቀርባል። ለሎጂስቲክስ ኩባንያዎች ደግሞ ሰፊ ገበያ እንዲያገኙና በአገልግሎት አፈጻጸማቸው ላይ መሻሻል እንዲያመጡ ያግዛል ሲል ኢትዮቴሌኮም ገልጿል።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
ወጋገን ካፒታል ቀዳሚ ያደረገውን የመጀመሪያው የግብይት አባልነት ሰርትፊኬት ከየኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለንዋይ ገበያ ተቀብሏል።

ይህም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተቀበለውን ፍቃድ የተከተለ ነው።
የባንኩ ሰው ለይኩን ብርሃኑ  ( ከ1937 - 2017 )

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በተለያዩ አገራዊ ባንኮች ከገዥነት እስከ ፕሬዚዳንትነት ያገለገሉት የአቶ ለይኩን ብርሃኑ ከአባታቸው ከአቶ ብርሃኑ ገምታ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጉደቱ አንበቻ  ሰኔ 4 ቀን 1937 ዓ.ም በቀድሞ ወለጋ ክፍለ ሀገር በጊምቢ አውራጃ ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በጊምቢ ደጅአዝማች ገ/እግዚአብሔር አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በቀድሞ አጠራር ነቀምቴ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ከዚያም በመቀጠል የከፍተኛ ትምህርታቸውን በቀድሞ አጠራር ኃይለስላሴ ዩኒቨርሲቲ የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሐምሌ ወር 1961 ዓ.ም. በከፍተኛ ውጤት አጠናቀው በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ተቀብለዋል።

የአቶ ለይኩን ብርሃኑ የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያሳየው በሕይወት ዘመናቸው በተለያዩ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ለ47 ዓመታት በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች አገልግለዋል፡፡

ከጥር 1968 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 1971 ዓ.ም. የቀድሞ የአዲስ ባንክ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ከጥቅምት 1971 ዓ.ም. እስከ 1972 ዓ.ም. ደግሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ወቅት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም ለባንኪንግ ኢንዱስትሪው እድገት ላደረጉት በጐ ተጽእኖ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ማኔጅመንት ሚያዝያ 7 ቀን 2011ዓ.ም. በስማቸው ‘’ለይኩን ብርሃኑ’’ ቅርንጫፍ ከፍቶ ለአገልግሎት አብቅቷል፡፡

አቶ ለይኩን ብርሃኑ ከጥቅምት 1972 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 1975 ዓ.ም. የእርሻ ሰብል ገበያ ድርጅት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከመጋቢት 1978 ዓ.ም. እስከ መስከረም 1981 ዓ.ም. የትራንስፖርትና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ዋና ኃላፊ እንዲሁም ከጥቅምት 1982 እስከ ጥቅምት 1984 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር  በመሆን ኃላፊነታቸውን በብቃት ተወጥተዋል፡፡

አቶ ለይኩን ብርሃኑ በ1983 ዓ.ም. የደርግ መንግሥትን መውደቅ ተከትሎ አገራችን ኢትዮጵያ የተከተለችውን የኢኮኖሚክ ሪፎርም ኘሮግራም ከህዳር 1984 ዓ.ም. እስከ መስከረም 1987 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን በአስተባባሪነትና በአስፈጻሚነት ጉልህ ድርሻ አበርክተዋል፡፡ 

በተለይም በደርግ ዘመነ መንግሥት ለ17 ዓመታት ለግሉ ዘርፍ ዝግ ሆኖ የቆየውን የባንክና የኢንሹራንስ ዘርፍ ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ክፍት ለማድረግ አዳዲስ ባንኮችና ኢንሹራንሶች እንዲቋቋሙ የባንክና ኢንሹራንስ ሥራ ፈቃድ አዋጆችን በማውጣት በአሁኑ ጊዜ 30 የግል ባንኮች እና 17 የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች  እንዲቋቋሙ መንገድ የከፈቱና የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጡ መሪ ነበሩ፡፡

አቶ ለይኩን ብርሃኑ በመጨረሻው የሥራ ዘመናቸው ከመጋቢት 1988 ዓ.ም. እስከ ታህሣስ 2003 ዓ.ም. የአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር ኘሬዚዳንት በመሆን ባንኩን ከ14 ዓመታት በላይ በኘሬዚዳንትነት አገልግለዋል፡፡ አቶ ለይኩን ብርሃኑ በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም አርፈዋል  ።

የቅዳሜገበያ
@Etstocks
ኢትዮጵያ በይፋ የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽንን ተቀላቀለች!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  አዋጅ
ቁጥር 1379/2017ን
በማፅደቅ ሀገሪቷ ወደ አፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ለመቀላቀል የሚያስችላትን ውሣኔ አሳልፏል።

ማንበብ ይቀጥሉ
https://www.2merkato.com/news/alerts/8436-ethiopian-parliament-ratifies-proclamation-to-join-african-finance-corporation
የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2025 በአዲስ አበባ የሥነ ጥበብ እና ሳይንስ ሙዚየም ዛሬ በይፋ የተከፈተ ሲሆን፥ ከ150 በላይ የፋይናንስ ተቋማትን፣ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከ12 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከማዕከላዊ ባንክ የሚበደረው ብድር ወደ ዜሮ መውረዱን አስታወቁ።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው የውይይት መድረክ በፊንቴክ፣ በመንግስት እና በግል አጋርነት እና በአካባቢያዊ ውህደት ላይ ባሉ ክፍለ ጊዜዎች ቀጥሏል።
ባለፉት 10 ዓመታት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ (Gross Domestic Product per capital) ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገቡ 10 ምርጥ የአፍሪካ ሀገራት

የነፍስ ወከፍ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት ብዙውን ጊዜ ከግለሰብ ገቢ እና ፍጆታ መጨመር ጋር ይዛመዳል። ይህ የሚያሳየው በአማካይ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሰዎች ካለፈው አመት በተሻለ ሁኔታ ላይ መገኘታቸውን ነው።

ሌላው የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ ገፅታ ደግሞ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ የግዢ ሃይል እኩልነት(Purchasing power parity) ሲሆን ይህም በእያንዳንዱ ሰው አማካይ የኢኮኖሚ ውጤትን የሚያመለክት እና በአገሮች ያለውን የኑሮ ውድነት ታሳቢ ያደረገ ነው።

መረጃ ምንጭ - World Economics
አሜሪካ በሬሚታንስ ላይ ታክስ የመጣል ዕቅድ እንዳላት ተገለፀ።

በዚህ ሳምንት ታክስን በተመለከተ በቀረበው ዕቅድ ላይ በአሜሪካ ከሚኖሩ ሰዎች ወደ ሌላ ሃገር የሚደረጉ ክፍያዎች (ሬሚታንስ) ላይ የ5 በመቶ ተብሎ ታክስ ለመጣል ታቅዷል ተብሏል።

በታክሱ አብዛኞቹ በአሜሪካ ዜጎች የሚፈፀሙ ዝውውሮች ባይካተቱም በሌሎች ሀገር ዜጎች እና አንዳንድ በአሜሪካ ዜጎች የሚላኩ ገንዘቦች ግን ታክሱ ይፈፀምባቸዋል።

በ2023 ብቻ በአሜሪካ የሚኖሩ ሰዎች ከ93 ቢሊየን ዶላር በላይ ሬሚታንስ ወደ ሀገሮቻቸው የላኩ ስለመሆኑ የዓለም ባንክ ሪፖርት ያሳያል።

እንደ ኬንያ፣ ጋና እና ናይጄሪያ ያሉ ብዙ ሬሚታንስ ተቀባይ የሆኑ አፍሪካውያንም በጉዳዩ ስጋት ገብቷቸዋል።

በእነዚህ ሀገራት ሬሚታንስ ከሀገር ውስጥ ጥቅል ምርት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ሲሆን ከሬሚታንስ የሚገኘው ገንዘብ አንዳንዴ በእርዳታ እና ኢንቨስትመንት መልኩ ከሚያገኙት ገንዘብ ጭምር እንደሚበልጥም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ በ2023/24 ከሬሚታንስ 6 ቢሊየን ዶላር ያገኘች ሲሆን ታክሱ ተግባራዊ ከሆነ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታት ይሆናል።

Source: tikvahethmagazine
@Etstocks
Ethiopian Securities Exchange (ESX) and IFC - International Finance Corporation ) have made an agreement and officially launched the Ethiopia Money Market Capacity Building Project. The initiative is expected to play a pivotal role in shaping the future of Ethiopia’s capital markets by investing in critical human capital and institutional development.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ የወሰዳቸው የለውጥ እርምጃዎች ……

1. ለአስመጪዎች የቅድመ ክፍያ (አድቫንስ ፐይመንት) መጠንን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ተደርጓል።

2. ለውጭ ሀገር ተጓዦች የሚፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሆኗል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከሂሳባቸው ላይ በካርድ መጠቀም የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ10 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ እንዲል ሆኗል፡፡

3. የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ክፍያዎችን ሥርዓት ለማስያዝ በማሰብ ባንኮች ከገቢ ንግድ፣ ከአገልግሎት ክፍያ ወይም ከጥሬ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎት የሚያስከፍሏቸው ማናቸውም አስተዳደራዊ ወጪዎችና ክፍያዎች ከግንቦት 18፣ 2017 ጀምሮ ከ4 በመቶ እንዳይበልጡ ተወስኗል፡፡
ብሔራዊ ባንክ ሸቀጦችን ከውጭ ለማስገባት የሚከፈለው የቅድመ ክፍያ መጠን ወደ 50 ሺህ ዶላር ከፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያ ሥርዓትን ለማሻሻል ያለመ አዲስ የለውጥ እርምጃዎችን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።

ይህን ተከትሎ ከተወሰዱ እርምጃዎች ዉስጥ ከውጭ ለማስገባት ሊከፈል የሚችለው የቅድመ ክፍያ መጠን ከ5 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወደ 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ  እንዲል ማድረጉን አስታውቋል።

ባለፈው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም. ስራ ላይ የዋለው አዲሱ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓት በውጭ ምንዛሪ ገበያ እና በሀገሪቱ የውጭ ክፍያ ሚዛን ላይ ከፍተኛ መሻሻል ማምጣቱን ባንኩ አስታዉሷል።

የውጭ ምንዛሪ ገበያ ማሻሻያዎች በተመለከተ ብሔራዊ ባንክ ባወጣዉ መግለጫ ላይ ለግል ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ወደ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሲጨምር፣ ለንግድ ስራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ደርሷል።

በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከሂሳባቸው በካርድ መጠቀም የሚችሉት የውጭ ምንዛሪ መጠን ከ10 በመቶ ወደ 20 በመቶ ከፍ ብሏል።
ብሔራዊ ባንክ ስድስተኛውን የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ በ50 ሚሊዮን ዶላር ሊያካሂድ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና የውጭ መረጋጋትን ለመቆጣጠር ያለመ 50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ዛሬ ሐሙስ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ይህ ጨረታ ለንግድ ባንኮች የቀረበ ሲሆን፣ ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው ተከታታይ ጨረታዎች ስድስተኛው ነው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው አምስተኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የመገበያያ ዋጋ 132.96 ብር ሆኖ ተመዝግቦ ነበር። በዚያ ጨረታ ላይ ባንኩ 60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያቀረበ ሲሆን፣ በጠቅላላው 16 የንግድ ባንኮች የጠየቁትን የውጭ ምንዛሪ ድልድል ማግኘት ችለው እንደነበር ይታወቃል።

Source: capitalethiopia
@Etsrocks