ET Securities
662 subscribers
584 photos
7 videos
28 files
297 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
Highest Dollar offer DBE

@etstocks
ብሔራዊ ባንክ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን ገለፀ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የዉጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አዉጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

የዉጪ ምንዛሪ ገበያ ዉስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ እንደተናገሩት " የዉጪ ምንዛሪ ዚሮዉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይተዋል ያላቸዉን ሰዎች መቀበሉን " የገለፁ ሲሆን ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለዉ ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል ሲሉ ተደምጠዋል ።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ "ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩ የዉጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል " ይህም በድፍረት የተደረገ ነዉ ማለት ይቻላል ሲሉም እርጃዉን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ በ 100 ዶላር የዉጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።
#Capital
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 8.6 ቢሊዮን ብር የአርቦን ገቢ ማስመዝገብ መቻሉን እና የእቅዱን 92.4 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታወቀ

ብቸናዉ መንግስታዊ የኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነዉ ተቋሙ ካስመዘገበዉ የአረቦን መጠን ዉስጥ 8.3 ቢሊዮን ያህሉ ከመድን ዘርፍ የተመዘገበ ካለፈው በጀት ቀሪዉ 306.5 ሚሊዮን የሚሆነዉ ከረጅም ጊዜ መድን ዘርፍ የተመዘገበ መሆኑን በዓመታዊ ሪፖርቱ ገልጿል።

በበጀት አመቱ ከተመዘገበው አረቦን ውስጥ 85 በመቶውን ለመሰብሰብ እቀድ የተያዘ ቢሆንም የተሰበሰበው የአረቦን መጠን 89.7 በመቶውን ነው፡፡ ይህም ከተቀመጠው እቅድ አንጻር ሲገመገም አፈጻጸሙ 105.5 በመቶ መሆኑን ያስታወቀዉ ድርጅቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ግን አፈጻጸሙ የ9.3 በመቶ ብልጫ አለዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንዳስታወቀው በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት ከታክስ በፊት ከ 1.66 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን እና ይህም ከተያዘው እቅድ ጋር ሲነፃፀር 7.5 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ሲል በሪፖርቱ ገልጿል ።

Source: ENA
Source _ Banks Ethiopia

@etstocks
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ!

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ባሳለፍነው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡

ብር 232 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን

አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለ8250 ደንበኞች አቅርቧል፤ የተሰጡ ብድሮች ለግል ፍጆታ ብድር፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለግብርና ብድር፣ ለቤት መስሪያና ማደሻ እና ለተሽከርካሪ ግዥ ብድር ለማኅበረሰባችን ተደራሽ አድጓል፡፡

የተከፈለ ካፒታል ብር 136 ሚሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ የተቋሙ ሃብት ብር 1.9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡
Wegagen Bank overtakes DBE offering the highest rate for buying of USD
Ethiopia and China strike a historic currency swap deal to boost trade.

At the China-Africa summit, FDRE Minister of Finance H.E. Ahmed Shide, anounced a significant financial agreement between Ethiopia and China. The two nations have entered in to a currency swap deal, allowing them to conduct trade using their own local currencies.
ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የዉጪ ምንዛሪ ግኝትን ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል

👉 በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሐዋላ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ለሚከፍቱ ከሳምንታት በኃላ ፍቃድ መስጠት እንደሚጀመር ባንኩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የዉጪ ምንዛሪ ግኝት ከፍ ማድረጉን አስታዉቋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ደቦ የተሰኘ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን የሚያሻሽል ፕሮግራም ባንኩ ይፋ አድርጓል ።

የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት በህጋዊ መንገድ የሃዋላ የውጭ ምንዛሬ ቢሮ ለሚከፍቱ ግለሰቦች ( ተቋማት) ከሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በኋላ ፈቃድ መስጠት ይጀምራል ብለዋል።

መንግስት በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገዉ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ያበረታታ እና ዜጎችን ወደ ሕጋዊ መንገድ ያመጣ እንደሆነም ተነግሯል ።

በ2023 ከሬሚታንስ ከ653 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘት መቻሉን የገለፀዉ ብሔራዊ ባንክ ይሄንን ግኝት ከፍ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ የውጭ ምንዛሪ አሥተዳደር መመሪያ መዘጋጀቱን አስታዉቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሃዋላ የውጭ ምንዛሬ ሊያሳድግና የተሻሻለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ተግባራዊነት ሊያረጋግጥ እንደሚችል የገለፀዉን የስድስት ወር ንቅናቄ ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

Source: capitalethiopia
@Etstocks
ሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችል መመርያ ተዘጋጀ

ለአዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎች የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ መዘጋጀቱ ተገልጿል
ለካፒታል ገበያ ወደ ሥራ መግባት ትክክለኛና አስፈላጊ ነው የተባለ የሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችል መመርያ ዝግጅት መጠናቀቁን፣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አስታወቀ።

የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አዳዲስ የሥራ ፈጣሪዎች በሥራ ላይ ያሉትን የቁጥጥር ደንቦችና መመርያዎችን መከተል ሳይጠበቅባቸው፣ አገልግሎቶቻቸውን ለካፒታል ገበያ ማቅረብ የሚያስችል የቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ አድርጓል።

የካፒታል ገበያን ወደ ሥራ ለማስገባት ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ የሕግ ማዕቀፎች ሲዘጋጁ መቆየታቸውን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሀና ተኸልኩ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

የካፒታል ገበያን ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ለማስገባትና የኩባንያዎችን መዋዕለ ንዋይ ለሕዝብ ማቅረብ እንዲቻል፣ ባለሥልጣኑ ሲያዘጋጀው የቆየው መመርያ መጠናቀቁን የገለጹት ወ/ሪት ሀና፣ ተግባራዊ ለማድረግም በፍትሕ ሚኒስቴር ማስመዝገብ ብቻ ነው የቀረው ብለዋል፡፡ ‹‹በዚህ መሀል ሰነደ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ሰነዶቻቸውን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ እየሠራን ነው፤›› ሲሉም ጠቁመዋል።

የውጭ ባለሀብቶች ወደ አገር ውስጥ በመግባት የካፒታል ገበያው ውስጥ አክሲዮን መግዛት እንዲችሉ በቅርቡ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ እንደሚፈቅድ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሰነድ መዋዕለ ንዋይን ለሕዝብ ለማቅረብ የሚያስችለው መመርያ ፀድቆ ወደ ሥራ ያልገባ በመሆኑ፣ የውጭ ባለሀብቶች ገብተው አክሲዮን እንዳልገዙ አስታውቀዋል። መመርያው ፀድቆ የካቲፓል ገበያው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ፣ የውጭ ባለህብቶች ወደ አገር ውስጥ ገብተው ሼር የመግዛትም ሆነ የመሸጥ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

‹‹በካፒታል ገበያ ሰዎች ከተሻሻጡ በኋላ አክሲዮኑን ከአንድ ሰው ገንዘቡን ደግሞ ከሌላ ሰው የሚያቀያይር ሥርዓት (Central Securities Depository) ያስፈልጋል፤›› ያሉ ዋና ዳይሬክተሯ፣ ይህንንም በብሔራዊ ባንክ ግዥ መካሄዱንና የሙከራ ሒደት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የልማት ድርጅት አዳዲስ የፋይናንስ ሙከራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሪት ዳግማዊት ሽፈራው በበኩላቸው፣ ባንኮች የሚሰጧቸው እንደ ብድር፣ ገንዘብ ማስቀመጥና ኢንሹራንስ ያሉ አገልግሎቶች ለሚሰጡ ባንኮች፣ ብሔራዊ ባንክ በሚያወጣቸው ሕጎችና መመርያዎች የሚተዳደሩ መሆናቸውን፣ በካፒታል ገበያ ውስጥ ያለ አገልግሎት ከሆነ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሚያወጣቸው ሕጎች እንደሚተዳደሩ ገልጸዋል።

ሆኖም ኢንቨስትመንት ባንክ ሆነው በተለየ መንገድ የሚሠሩ ከሆነና አሁን ባለው የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አሰጣጥ የማይቻል ከሆነ ደግሞ፣ ባለሥልጣኑ ይፋ ባደረገው የካፒታል ገበያ ቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፍ እንደሚታይ አስታውቀዋል።

በቁጥጥር ማጣሪያ ማዕቀፉ የሚቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ አገልግሎቱ የፈጠራ ይዘቱ እንደሚመረመር፣ እንዲሁም ለምን ዓይነት ገበያና ተጠቃሚዎች ይቀርባል የሚለው እንደሚጣራ ወ/ሪት ሀና ገልጸዋል። ይህን ሒደት ያለፈ አገልግሎትም ተግባራዊ ሲደረግ የሚፈጠረውን ሁኔታ ለመገንዘብ የሙከራ ጊዜ እንደሚዘጋጅ አመላክተዋል።

ፈጠራን ማበረታታት አንዱ የማዕቀፉ ዓላማ መሆኑና አዳዲስ የፋይናንስ የፈጠራ አገልግሎቶችና ምርቶች ሲመጡ፣ ባለሥልጣኑ እንዴት መቆጣጠር እንደሚችል የሚማርበትና የቁጥጥር አቋም የሚገነባበት እንደሆነም ገልጸዋል።

ሪፖርተር
@etstocks
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሀንስ አያሌው (ዶክተር) ስራቸውን ለቀዋል። በተጠባባቂነት/በጊዚያዊነት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ጌታቸው ዋቄ  ሀለፊነቱን ተረክበዋል።

Source: theethiopianeconomistview
@Etstocks
Source:- Banks Ethiopia
@etstocks
ህብረት ኢንሹራንስ አዲስ ያሰራውን መለያም ይፋ አደረገ

ፕሬዝዳንቷ የ2024 የአፍሪካ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ምርጥ ዋና ስራ አስፈፃሚነትን አሸናፊ ሆነዋል።

ከቀዳሚዎቹ የመድን ሰጪ ተቋማት መካከል የሆነው ህብረት ኢንሹራንስ ኩባንያው ላለፉት 30 አመታት ሲገለገልበት የነበረውን መለያ (ብራንድ) ዘመኑን በዋጀ እና አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መለያ መቀየሩን አስታውቋል፡፡

Read More

Source: capitalethiopia
@Etstocks
የአማራ ባንክን በተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጫንያሌዉ ደምሴ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ::

ላለፉት 9 ወራት የአማራ ባንክ በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ጫንያሌዉ ደምሴ ሰኞ ዕለት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የካፒታል ምንጮች ተናግረዋል ።

አቶ ጫንያሌዉ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡበት በተጠባባቂነት የነበሩበትን የስራ አስፈፃሚው ቦታ አዲስ አመራር እንደሚመጣ ከተነገረ በኃላ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀውልናል።

በባንኩ የቦርድ አመራር ዐርብ ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዋና አቶ ኄኖክ ከበደ ታደሰና የኮርፖሬት አገልግሎት ዋና መኰንኑን አቶ ክንዴ አበበን፣ በአፈጻጸም ድክመት ከሓላፊነታቸው እንዳነሳ የሚታወስ ነው። ከሓላፊነታቸው በተነሡት አቶ ሄኖክ አበበ ቦታ፣ የባንኪንግ አገልግሎቶች ከፍተኛ መኰንን አቶ ጫንያለው ደምሴ ከኅዳር 29 ቀን ጀምሮ በጊዜዊነት የዋና ሥራ አስፈጻሚነቱን ደርበው እንዲይዙ እንደመደባቸው ይታወቃል ።
መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ባንኩ በ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘቡ 25 ነጥብ 1 ቢሊየን መድረሱን እና በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 377 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል ።

ባንኩ በቅርብ በሰጠዉ መግለጫ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች 311 ቅንጫፎችን መክፈቱንና 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ገልጿል።

Source Capital
@Etstocks
DBE boasts a capital base of 39.7 billion Br, second only to the Commercial Bank of Ethiopia (CBE). The turnaround began when the Council of Ministers approved a crucial capital injection of 28.5 billion Br, followed by the National Bank of Ethiopia’s (NBE) directive, which required commercial banks to purchase DBE bonds worth one percent of their annual loans. These bond sales generated 39.04 billion Br over the past three years, significantly bolstering DBE’s financial position.

Read More

Source: addisfortune
@Etstockd
የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በፕሬዝደንትነት ሲመሩ የነበሩት ዮሐንስ አያሌዉ (ዶ/ር) የአማራ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነዉ ተሾሙ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክን ላለፉት 4 ዓመታት ሲመሩ የቆዩት ዮሐንስ ( ዶ/ር) በአደሱ ዓመት ከመስከረም 02 ፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ የአማራ ባንክን በስራ አስፈፃሚነት ቦታ እንደተሾሙ ተገልጿል።

ዮሐንስ (ደ/ር) በይፋ ስራዉን ከጀመረ 2 ዓመት ተኩል ያስቆጠረዉ አማራ ባንክን በተጠባባቂ ዋና ስራ አስፈፃሚነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ጫንያሌዉ ደምሴን የሚተኩ አንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።

የግዙፉ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት የነበሩት ዮሐንስ (ዶ/ር) ከቀናት በፊት  በፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ የአማራ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ብሩን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ  መሾሙን በዛሬዉ ዕለት አስታዉቋል።

በአመራር የኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል ልምድ ያላቸዉ ዮሐንስ አማራ ባንክ በፕሬዝዳንትን የሚመሩ ሁለተኛው ሰዉ ያደርጋቸዋል ።

Source: capitalethiopia
@Etstocks