ET Securities
673 subscribers
592 photos
7 videos
30 files
300 links
At ET Securities, our goal is to provide services in the financial sector, with a special focus on capital markets and financial markets.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
Kenya’s KCB Group Limited is set to become the first foreign bank to enter Ethiopia’s financial sector following the country’s banking liberalization policy. The National Bank of Ethiopia (NBE) is currently in discussions with KCB executives regarding entry requirements, and the bank is expected to begin laying the groundwork for its expansion soon.

The Banking Business Proclamation, amended in November 2024, allows foreign banks to enter Ethiopia through four methods:
1. Incorporating a subsidiary in Ethiopia.
2. Buying stakes in a domestic bank.
3. Establishing a local branch office.
4. Opening a representative or liaison office.

The law caps foreign investment in a bank at 40% ownership, while domestic banks cannot sell more than 49% of their authorized shares to foreign investors. KCB Group CEO Paul Russo has expressed optimism about Ethiopia’s large, financially underserved population, despite the ownership restrictions.
የኢትዮጵያ ሰነደ መዋለ ንዋዮች ገበያ (ESX) የገበያ መተዳደሪያ ደንብ በአማርኛ ቋንቋ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

ደንቡን ለማግኘት ከታች ይመልከቱ
👇👇
ለባንኮች ብስራት

ከህዳር 2015 ዓም አንስቶ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባንኮች ከሚለቁት ብድር የ20 በመቶ እኩሌታ የግምጃ ቤት ቦንድ እንዲገዙ በአስገዳጅነት ጥሎት የነበረው አሰራር በዚህ ባለንበት የሰኔ ወር ያበቃል።

የሰሜኑ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ መንግስት ከአጋሮቹ ያገኝ የነበረው የበጀት ድጋፍ በመቋረጡ  ማእከላዊ ባንኩ የመንግስትን ወጪ በተለያየ መሳሪያ ለመደገፍ ሲሞክር የቆየ መሆኑ ይታወቃል።

ከዚህም መካከል የቀጥታ ብድር እና የ20 በመቶ የግምጃ ቤት/treasury ቦንድ የሚጠቀሱ ናቸው።

ከጦርነቱ ማብቃት በኋላም የቦንድ ግዥው አልተቋረጠም።

ይህም በተለይ መንግስት የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር በተጨማሪ መሳሪያነት ሳይጠቀምበት እንዳልቀረ ነው በባለሞያዎች የሚጠቀሰው።

ሆኖም አስገዳጅ የቦንድ ግዥው የባንኮችን የገንዘብ ይዞታ/ liqudity እንዳሳሳባቸው በምሬት ሲገልፁ ቆይተዋል።

ሆኖም መንግስት ከአውጭ አጋሮች ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት የቦንድ ግዥው በዚህ ወር የሚያበቃ ነው የሚሆነው።

ባንኮች ላይ ተጥሎ የቆየው የብድር አቅርቦት ገደብም በቀጣዩ መስከረም እንደሚነሳ ከሁለት ወራት በፊት መገለፁ ይታወሳል።
የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድን በኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ (ESC)በኩል ሊሸጥ ነው !

የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድን ከሐምሌ ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ማሻሻጥ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ሙዓለ ነዋይ ገበያ አስታውቋል 

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጥላሁን ካሳሁን (ዶ/ር) እንዳስታወቁት ዳያስፖራው የግምጃ ቤት ሰነድ  በመግዛት በዚህ የኢንቨስትመንት መሰማራት አለበት ፡፡


በዚህ ኢንቨስትመንት መንግሥት በገንዘብ ሚኒስቴር አማካይነት ለአንድ ዓመት ከሚበደረው ገንዘብ በአማካይ ከ16.5 በመቶ በላይ ወለድ እንደሚያስገኝ አስታውቀዋል ፡፡

ዳያስፖራዎች ባሉበት አገር ሆነው በከፈቱት አካውንት ኢንቨስት አድርገው ያገኙትን ዋና ገንዘብና ወለድ ወደፈለጉበት የባንክ አካውንት እንደሚዛወርላቸውም መናገራቸውን የዘገበው ሪፖርተር ነው  ፡፡


በዩቲዩብ   www.youtube.com/@etstocks
📢 Vacancy Announcement
Wegagen Capital Investment Bank

We’re hiring! Join Ethiopia’s pioneering investment bank and help us unlock capital market opportunities.

🔹 Position: Head of Marketing
🔹 Location: Head Office
🔹 Salary: Based on scale
🔹 Deadline: June 24, 2025

Job Summary:
Lead the marketing & communication strategy of the bank. Enhance our brand presence and drive impactful campaigns.

Requirements:
🎓 Bachelor's in Marketing, Communications, or related field (MBA preferred)
📈 8 years' experience (3 in a supervisory role)

📩 Send your Application Letter and CV to: info@wegagencapital.com.et
📌 Use the position title as your email subject.
Certified Intermediaries for T-Bill Trading in Ethiopia 

The Ethiopian Securities Exchange (ESX) has officially certified key intermediaries for Treasury Bill (T-Bill) trading, ensuring secure and regulated access for investors. These intermediaries facilitate transactions for both retail and institutional investors, following Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) guidelines. 

Certified Intermediaries: 
- CBE Capital Investment Bank S.C. – A subsidiary of the Commercial Bank of Ethiopia, offering brokerage and advisory services. 
- Wegagen Capital Investment Bank S.C. – The first licensed investment bank and ESX trading member, specializing in securities transactions. 
- Ethio-Fidelity Securities S.C. – An independent securities dealer focused exclusively on capital market services. 

Investors must open accounts with these intermediaries to participate in T-Bill auctions and secondary market trading. For more details, visit the [National Bank of Ethiopia]
በራሺያ ሴንትፒተርስበርግ አለምአቀፍ የኢኮኖሚ መድረክ ላይ ለእይታ የበቃው የብሪክስ የ200 የገንዘብ ኖት።

በገንዘቡ ላይ የኢትዮጵያ ጨምሮ የብሪክስ አገራት ባንዲራም ይገኛል።
👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMSaQwxfx/
| በስምንተኛው ዙር የዉጪ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ 136 ብር ደረሰ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሄደው 8ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት መሰረት፣ የአንድ የአሜሪካ ዶላር የምንዛሪ ዋጋ 136.6286 ብር መሆኑን አስታወቀ።

50 ሚሊዮን ዶላር በቀረበበበት ጨረታ ላይ 11 ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ድልድል አግኝተዋል።

ይህ አሁን ይፋ የተደረገው የምንዛሪ ተመን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው 7ኛው ዙር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ከተመዘገበው 134.95 ብር የአሜሪካ ዶላር አማካይ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር፣ የብር የመግዛት አቅም በ1.6786 ብር መቀነሱን ያሳያል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎችን የሚያካሂደው በሀገሪቱ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ለማቃለል እና የባንኮችን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማሟላት መሆኑ መግለፁ ይታወቃል። 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@et_securities/video/7517667465489353990
Ethiopia will begin trading under the African Continental Free Trade Area (AfCFTA) on July 1, six years after ratifying the agreement. The announcement was made by Trade and Regional Integration Minister Kassahun Gofe during a session of Parliament this week.
- - - - - - - - - - - - - - - - - - - - - -
ስምምነቱን ካፀደቀች ከስድስት ዓመታት በኋላ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) የንግድ ልውውጥ በመጪው ሐምሌ ወር የመጀመሪያ ሳምንት ትጀምራለች።

የንግድና ክልል ኢኮኖሚ ውህደት ሚኒስትሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ ይህን የገለፁት በዚህ ሳምንት በተደረገው የፓርላማው ስብሰባ ላይ ነው።

Read more
Etsecurities.com
የቴሌግራም መስራች ሀብቱን ለ100 ልጆቹ ለማውረስ ማቀዱን ገለጸ።

የቴሌግራም መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓቨል ዱሮቭ ያለውን ሃብት ለ106 ልጆቹ በእኩል እንደሚያከፋፍል አስታውቋል።

ቢሊየነሩ ዱሮቭ ከተለያዩ ሶስት ሴቶች 6 ልጆችን የወለደ ሲሆን በዘር ፈሳሽ ልገሳ ደግሞ በ12 የተለያዩ ሃገራት የተወለዱ 100 ልጆች እንዳሉት ይፋ አድርጓል።

ዱሮቭ ከቴሌግራም ጋር በተያያዘ ብዙ ጊዜ ጥያቄ የሚነሳበት እንደሆነ ሲታወስ በቅርቡ በዚሁ ምክንያት በፈረንሳይ መታሰሩም ይታወሳል።

እንደ ፎርብስ ከሆነ ዱሮቭ አጠቃላይ ሃብቱ 17.1 ቢሊየን ዶላር ሲሆን ይህንን ሃብቱን ለልጆቹ በእኩል እንደሚያከፋፍል ለፈረንሳዩ የፖለቲካ መጽሔት ለ ፖይንት ተናግሯል።

ልጆቹ እንደ ማንኛውም ሰው እንዲያድጉ እፈልጋለሁ ያለው ዱሮቭ ልጆቹ የተሰጣችውን ሃብት የሚወስዱት በፈረንጆቹ ከሰኔ 19,2055 በኋላ ወይም የዛሬ 30 አመት መሆኑንም ገልጿል።

የ40 ዓመቱ ወጣት አሁን ኑዛዜውን ማሰፈር ያስፈለገበት ምክንያት ከስራው ጋር በተያያዘ ያለውን አደጋ በመገንዘብ እንደሆነ ያስረዳል። "ነጻነትን መደገፍ ኃያላን መንግሥታትን ጨምሮ በርካታ ጠላቶችን ያተርፍልሃል" ይላል።

ቴሌግራም አሁን ላይ ከአንድ ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች አሉት።

Source: tikvahethmagazine
@Etstocks
Forwarded from Kelemat Ads Hub
ቤትዎን እና የስራ ቦታዎን ከሼይን እና አሊኤክስፕረስ በሚገኙ ውብ እቃዎች ማራኪ እና ውብ ያድርጉ።

Decorate your home and working places with classy items from Shein and AliExpress.

ቻናላችንን በመቀላቀል ያሉንን እቃዎች ይመልከቱ | Join our channel

👇

https://t.me/Medamart
https://t.me/Medamart
https://t.me/Medamart
ሰበር፡ የገዳ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ (ESX) ላይ ተዘረዘረ!

ገዳ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደመዋለንዋይ ገበያ  (ESX) ላይ በይፋ የተዘረዘረ ሁለተኛው ባንክ ሆኗል። ባንኩ 1.23 ሚሊዮን የ አክሲዮኖችን በገበያው ላይ በማቅረብ፣ ለኢትዮጵያ አዲስ ለሆነው የካፒታል ገበያ ባንኮች ያላቸውን እምነት አሳይቷል።

ይህ ዝርዝር አዲስ ገንዘብ ለማሰባሰብ ያለመ ሳይሆን፣ ነባር ባለአክሲዮኖች የአክሲዮናቸውን ፈሳሽነት (liquidity) እንዲያገኙ እና የገበያውን ታይነት ከፍ እንዲል ለማድረግ ነው።

የ ESX ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ካሳሁን “ይህ የገበያው ውጤታማነት ማሳያ ነው፤ እምነት እየገነባን ነው” ብለዋል።

ገዳ ባንክ በ2021 ተመስርቶ በ2022 ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2023/24 የ115 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ አግኝቷል። አጠቃላይ ንብረቱም ከ6.1 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወልዴ ቡልቶ ይህንን ዝርዝር “ለባንኩ ብቻ ሳይሆን ለመላው የፋይናንስ ሥርዓት ትልቅ ምዕራፍ ነው” ሲሉ ገልፀውታል።

የቦርድ ሰብሳቢው አቶ ሀሰን ሁሴን በበኩላቸው “እያደግን ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ግልፅና ተጠያቂ እየሆንን ነው” ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመጪው መጋቢት ወር የአለም ንግድ ድርጅት አባል ልትሆን ትችላለች ተባለ


ኢትዮጵያ በመጪው ዓመት መጋቢት ወር ላይ የዓለም ንግድ ድርጅት (WTO) አባል ልትሆን እንደምትችል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ። በርካታ የድርድር ጉዳዮች በስምምነት መጠናቀቃቸውን ተከትሎ፣ በካሜሩን በሚካሄደው የድርጅቱ ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ አባልነቷ እንደሚረጋገጥ ይጠበቃል።


ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው በ2003 ዓ.ም. እንደነበር ይታወቃል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የድርጅቱን ጥብቅ መስፈርቶች ለማሟላት የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች እንደተሻሻሉ መንግሥት አስታውቋል።


በ2020 ዓ.ም. ከአራተኛ ዙር ድርድር በኋላ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሌሎች ምክንያቶች ድርድሩ ተስተጓጉሎ ቢቆይም፣ አሁን በብዙ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ፍላቴ ተናግረዋል።


አቶ ወንድሙ በመጪው መጋቢት ወር በካሜሮን በሚካሄደው የድርጅቱ 14ኛው የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ አባል እንደምትሆን ተስፋ አድርገዋል።


የዓለም ንግድ ድርጅት ኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዲያገኝ የቴሌኮም እና የባንክ አገልግሎት ዘርፎቿን ለውጭ ባለሀብቶች እንድትከፍት በተደጋጋሚ ሲጠይቅ መቆየቱ ይታወቃል። አሁን የእነዚህ ዘርፎች ለውጭ ባለሀብቶች መከፈት መጀመራቸው የኢትዮጵያ የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝ እንደሚያግዝ ተገምቷል።


ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ከሆንች፣ ምርቶቿን በአባል አገራት ያለ ቀረጥ የመሸጥ መብት ታገኛለች። በተለይም እንደ ቡና ያሉ ምርቶቿን ያለ ክልከላ አቅሟ በፈቀደ መጠን የገበያ ፍላጎት ባለበት ሁሉ እንድትሸጥ ዕድል እንደሚሰጣት ተገልጿል።
Forwarded from Kelemat Ads Hub
ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና ባንኮችን በተመለከተ አዳዲስ እና የተብራሩ ዜናዎችን በየቀኑ ይፈልጋሉ?

ይህንን ቻናል Subscriber በማድረግ ራስዎን ያዘምኑ፡፡
👇

https://t.me/girum_x_links
https://t.me/girum_x_links
ሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ካፒታሉን ወደ 300 ሚሊዮን ብር ሊያሳድግ ነው

በኢትዮጵያ ፈቃድ አግኝተው በቅርቡ ወደ ሥራ ከገቡ ሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው ሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ፣ የካፒታል መጠኑን ወደ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያሳድግ ተገለጸ፡፡ የኢንቨስትመንት አካውንቶችን መክፈት ሊጀምር ነው፡፡

ሪፖርተር ያነጋገራቸው የሲቢኢ ካፒታል አክሲዮን ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ ኢንቨስትመንት ባንኩ በገበያ ውስጥ ያለውን አገልግሎት ለማስፋት በቀጣዩ በጀት ዓመት ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር ካፒታል በመጨመር አጠቃላይ ካፒታሉን ወደ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያሳድግ ገልጸዋል፡፡

ባንኩ ወደ ሥራ ሲገባ 100 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዘመዴነህ፣ ከዚህ ውስጥም 70 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻ ሲሆን፣ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ ዳሉል ካፒታል በተባለ የግል ኩባንያ የተያዘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://Etsecurities.com