ET Securities
645 subscribers
572 photos
7 videos
26 files
287 links
At Et securities our aim is in creating condusive space concerning capital markets and financial markets so as to enable learning and awareness creation to the society.

Support us https://t.me/boost/Etstocks

https://www.youtube.com/@etstocks
Download Telegram
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነድ ማስረከቢያ ጊዜን አራዘመ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በህዝብ የተያዙ ኩባንያዎች አስፈላጊ ሰነዶችን እና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ የተሰጠውን ቀነ-ገደብ ለአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ኩባንያዎቹ እስከ መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዶችንና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ አሳስቦ ነበር። ነገር ግን፣ ከኩባንያዎቹ የቀረቡትን ጥያቄዎች እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለመቀበል እንዲቻል የጊዜ ገደቡ እስከ ሚያዚያ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ተራዝሟል።

ይህ ማራዘሚያ አስፈላጊውን መረጃ እስካሁን ላላቀረቡ ኩባንያናት የመጨረሻ እድል እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ባለስልጣኑ ኩባንያናቱ የተራዘመውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም አስፈላጊ ሰነዶችንና መረጃዎችን እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ማራዘሚያው ከ50 በላይ የአክሲዮን ባለቤቶች ያሏቸው እና በአሁኑ ወቅት አክሲዮኖችን ለህዝብ ሽያጭ በማቅረብ ላይ ያሉ ኩባንያዎችን ይመለከታል።
#ሰበር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወጋገን ባንክ የመጀመርያ የሆኑትን ሁለት የኢንቨስትመንት ባንኮች በማቋቋም ወደ ስራ ለመግባት ፈቃድ አገኙ።

ባንኮቹ በኢትዮጵያ አክሲዮን ገበያ ላይ የማሻሻጥ ስራ ይጀመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን አምስት አዳዲስ አገልግሎት ሰጪዎችን ፈቃድ ሰጠ፤ የኢንቨስትመንት ባንኮች ለመጀመሪያ ጊዜ ፈቃድ ተሰቷቸዋል!!

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ለአምስት አዳዲስ የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ ሰጠ።

የፈቃድ አሰጣጡ ሥነ-ሥርዓት ዓርብ መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል።

ይህ አዲስ ፈቃድ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ባንኮች ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲጀመር ያስችላል።

በእነዚህ አዳዲስ ፈቃዶችም፣ በአጠቃላይ ፈቃድ ያላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ቁጥር ከአራት ወደ ዘጠኝ ከፍ ብሏል።

ፈቃድ የተሰጣቸው አዳዲስ ድርጅቶችና የፈቃድ ምድባቸው የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ሲቢኢ ካፒታል አ.ማ - የኢንቨስትመንት ባንክ

2. ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ - የኢንቨስትመንት ባንክ

3. ኢትዮ-ፊደሊቲ ሴኩሪቲስ አ.ማ - የሰነድ ም/ዋይ (ሴኩሪቲስ) አከናዋኝ

4. ኤች ኤስ ቲ ኢንቨስትመንት አድቫይዘሪ ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማ - የሰነድ ም/ዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ

5. ኢኩዥን የሰነድ ም/ዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ ኃ.የተ.የግ.ማ - የሰነድ ም/ዋይ ኢንቨስትመንት አማካሪ

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ አራት ፈቃድ ባላቸው አገልግሎት ሰጪዎች ብቻ የተወሰነ ሲሆን ሁሉም የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ነበሩ።

ሲቢኢ ካፒታል አ.ማ እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ ፈቃድ ማግኘታቸው ትኩረት የሚስብ ነው፣ ምክንያቱም እነዚህ ተቋማት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ሲቢኢ) እና በወጋገን ባንክ በባለቤትነት የተያዙ ናቸው።

ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/92/2024 ባንኮች በካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እስከ 100% ድረስ የአክሲዮን ድርሻ እንዲኖራቸው የሚፈቅደው ውጤት ነው።
#Vacancy_Announcements
Wegagen Capital-Investment Bank S.C. invites competent and qualified candidates for the following positions.

1. CHIEF, RESEARCH DEPARTMENT
2. CHIEF, RISK AND COMPLIANCE
3. CHIEF ADVISORY OFFICER
4. SR. ADVISORY OFFICER
5. . . . . .
6. . . . . .

Please visit the below link to the website for the details:

https://capitalethiopia.com/.../17/vacancy-announcement-6/
Deadline: Wednesday April 02, 2025
ET Securities pinned «https://www.youtube.com/watch?v=eqxaPShlwog»
Banking Business Proclamation No.1360_2025.pdf
11.8 MB
አዲሱ የባንክ ስራ አዋጅ
#ለመረጃ፦ ቤንዚን 112.67 ብር ገብቷል!

ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሚከተለዉ መሰረት ስራ ላይ እንዲዉል በመንግስት ተወስኗል።

በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ:-

ቤንዚን 112.67
ኬሮሲን 107.93
ነጭ ናፍጣ 107.93
ቀላል ጥቁር ናፍጣ 109.22
ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106.75 ብር በሊትር የሚሸጥ ይሆናል።
Zemedeneh Negatu, a seasoned Ethiopian-American investment advisor, has been appointed the founding Chief Executive Officer of CBE Capital SC , following the company’s receipt of an investment banking license from the Ethiopian Capital Market Authority on March 21.

The license makes CBE Capital one of the country’s first officially recognized investment Banks.
"ኢትዮጰያን በ2026 የአለም የንግድ ድርጅት ሙሉ አባል ለማድረግ እየሰራን ነው” - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ 5ኛውን የአለም የንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በበቂ ዝግጅት ተሳትፋ በስኬት ማጠናቀቋን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ ትላንት መጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በመግለጫቸውም በቅርቡ ጄነቭ በተካሄደው 5ኛው የሀገራችን የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁንና በቀጣይ በሚካሄደው 6ኛው የአለም ንግድ ድርጅት የስራ ቡድን ስብሰባ ኢትዮጵያን ሙሉ አባል ሆና ድርጅቱን መቀላቀል የሚያስችላትን ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል፡፡

Read More

Source: addisstandardamharic
ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መግለጫ ተሰጥቷል።

ማዕከላዊ ባንኩ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ሁለተኛ ስብሰባውን መጋቢት 16 ቀን 2017 አካሂዷል፡፡የደረሰበትን ውሳኔ ነው ይፋ ያደረገው።ዝርዝሩ በ3 ገፅ ከላይ ተያይዟል።
𝐌𝐨𝐧𝐞𝐭𝐚𝐫𝐲 𝐏𝐨𝐥𝐢𝐜𝐲 𝐂𝐨𝐦𝐦𝐢𝐭𝐭𝐞𝐞 𝐈𝐝𝐞𝐧𝐭𝐢𝐟𝐢𝐞𝐬 𝐂𝐚𝐬𝐡 𝐂𝐫𝐮𝐧𝐜𝐡 𝐢𝐧 𝐄𝐭𝐡𝐢𝐨𝐩𝐢𝐚𝐧 𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐫𝐜𝐢𝐚𝐥 𝐁𝐚𝐧𝐤𝐬

The Monetary Policy Committee under the National Bank of Ethiopia (NBE) identified pinching liquidity hurdles across some local banks with high levels of loan-to-deposit ratios.

Read More

Source: shegamedia
𝗖𝗕𝗘 𝗜𝗻𝘁𝗿𝗼𝗱𝘂𝗰𝗲𝘀 𝗜𝗻𝘁𝗲𝗿𝗻𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻𝗮𝗹 𝗠𝗮𝘀𝘁𝗲𝗿𝗖𝗮𝗿𝗱 𝗣𝗿𝗲𝗽𝗮𝗶𝗱 𝗖𝗮𝗿𝗱𝘀

March 27, 2025 (EBR_News)

The Commercial Bank of Ethiopia (CBE), in collaboration with global payment leader Mastercard, has introduced both plastic and virtual international prepaid cards, a move set to enhance digital payment accessibility in Ethiopia.