Ethio Job Vacancy
46K subscribers
23.2K photos
63 videos
157 files
19.5K links
አዳዲስ እና ወቅታዊ የሥራ ቅጥር ማስታወቂያዎችን ከተለያዩ ጋዜጦችና ድረ ገጾች ለሥራ ፈላጊዎች መረጃ መስጠት ነው።
Post New Job vacancies to Who are looking jobs.
Group discussion https://t.me/+uGe3tVg5jF4yZjk0
Download Telegram
#የትርጉም #መናፍስት
እንደ ሰው ስጠይቅ በብሔር አታዳምጡኝ
የራስ አስቀምጣችሁ የዘር ጆሮ አትስጡኝ
የዘር መልስ አትስጡኝ

እንደ ሰው ሲያወራ በጎጥ ጆሮ ሰምተን
"#መገዳደፍ" ጀመርን "#መደጋገፍ" ትተን
* * *
#እንግዳ #ሲመጣ
ትልቅ ሀገር ሽጠን መንደር ስለገዛን
"#ማሳቁን" ትተነው "#ማሳቀቅ" አበዛን
ሰውነትን ጥሎ ዘረኝነት ሲያልፈው
"#ተቀባይ" "#ተበቃይ" ሆነውና አረፈው
ዜግነት ሞቶ ብሄር ጀገነ
"#መቀበል" ማለት "#መበቀል" ሆነ
* * *
#አዲስ #ሞያ #ሆኖ
አፍ በጆሮ ማረድ ንግግር መበለት
"#እንቆረጥ" ሆኗል "#እንቆጠር" ማለት
#አትራፊ #ተብሎ
ፍቺ ሊቸረቸር ከሱቅ የወጣ ‘ለት
"#እንዝጋ" ይልሀል "#እንግዛ" ለማለት
* * *
ተርጓሚ ሲበዛ በየጥጋጥጉ
"#መተራረድ" ሆነ "#መረዳዳት" ወጉ

"#የማብላት" ትርጉሙ "#መብላት" የሆነ ‘ለት
"#መገናነዝ" ሆኗል "#መዘጋገን" ማለት

"#ሊቁን" ጠፍንገን "#ቂሉን" ስንፈታ
"#ወንጀል" ገነነ "#በወንጌል" ፋንታ
ትርጉም አለቀ ፍቺ ተዛባ
"#ልጅ" ስንጣራ "#ጅል" ዘሎ ገባ
========||=======
ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 2012 #አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች #የምዝገባ_ቦታን ስለማሳወቅ:

1.#ዋና_ግቢ (ፔዳ)
#ማህበራዊ_ሳይንስ(Social Science) እና
ማህበራዊ ሳይንስ #ቲችንግ(Social Science teaching)

2.#ግሽ_አባይ_ግቢ (ይባብ ካምፓስ)
#ተፈጥሮ_ሳይንስ(Natural Science) ከአልፋቤት A እስከ
M የሆናችሁ

3.#ዘንዘልማ_ግቢ
ተፈጥሮ ሳይንስ(Natural Science) ከአልፋቤት N እስከ
Z የሆናችሁ እና
ተፈጥሮ ሳይንስ #ቲችንግ (Natural Science
teaching)ሁሉም
መሆኑን አውቃችሁ በየተመደባችሁበት ቦታ እነድትገኙ እናሳውቃለን፡፡

ሬጅስትራርና አሉሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#ETA

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

ይፋ በተደረገው መረጃ የማስተካከያ ጥቆማ የሚኖራቸው ተቋማት በህጋዊ ተወካዮቻቸው በኩል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share