#አፋር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ፤
Afar Mass Media-ጥቅምት 26/2013
የህወኃት የባንዳ ቡድን የራሱን የስልጣን ፍላጐት እና ክብር ለማስጠበቅ የውጭ ተልዕኮን በመቀበል የአገራችንን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና እያለ በሚገኘው ልዩ ልዩ የሰሜን ዕዝ መከላከያ ሠራዊት ካምፖች ላይ አስነዋሪ ጥቃት ፈፅሟል፡፡
የአፋር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ይህንን በሉዓላዊነታችን ላይ የተቃጣ ድርጊት የሚኮንን መሆኑን ይገልፃል፡፡
ህወኋት በአሁኑ ወቅት እየፈፀመ ያለው ድርጊት የአንድን ቡድን ፍላጐት ለማሳካት የሚደረግ ሴራና ተልዕኮ እንጅ መላው የትግራይ ክልል ህዝብን የማይወክል አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡
ይህ ቡድን ባለፉት 27 ዓመታትም ትክክለኛ ያልሆነ የፌደራሊዝም ስርዓት በመዘርጋት በእጅ አዙር የክልላችንን ብሎም የአገራችንን ሀብት መዝብሯል፡፡ በእነዚህ አመታት በአፋር ክልል ህዝብ ላይ የተለያዩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመጣስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡
ህወኋት ከለውጡ በኋላ ከፈፀማቸው ስህተቶች ትምህርት ወስዶ ለአገራችን አንድነትና ብልፅግና የበኩሉን ድርሻ መወጣት ሲገባው የተፈጠረበት፣ ያደገበትና የኖረበት የፖለቲካ ሴራ አልላቀው ብሎ በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ብሄርንና ሀይማኖትን መሠረት ያደረገ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር በማድረግ ለበርካታ ንፁሀን ዜጐች ሞትና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል፡፡ በርካታ የንብረት ውድመት እንዲደርስም አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት በአገራችን መከላከያ ሰራዊታችን ላይ በፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት ለማስቆም የአገራችን ህዝቦች በአንድነት በመቆምና የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በዚህ ቡድን ላይ በሚወስደው የማያዳግም እርምጃ ከሰራዊቱ ጐን በመሰለፍ የሚሰራ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በመሆኑም የአፋር ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች፣ አባላት፣ ደጋፊዎች እና መላው የክልላችን ህዝብ አጥፊው የህወኋት ቡድን እየፈፀመ ያለውን አገር የማፍረስ ድርጊት ለማስወገድ በሚወሰደው እርምጃ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ጐን በመሆን ሁሉንም የክልላችን አካባቢዎች በንቃት በመጠበቅ ፤ የተለየ እንቅስቃሴ ምልክት ሲታይ መረጃ መስጠትና ከየአካባቢው የፀጥታ ሀይል ጋር በመሆን በማክሸፍ የክልላችንን ሰላም በማስቀጠል ለአገራችን አንድነት እንድትሰሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
#Prosperity Party, Afar Branch

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የፓርቲውን ፕሬዝደንት ምርጫ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ፣ እጅግ ዘመናዊ በሆነና ግልፅነት ባለው መንገድ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
#prosperity
#prosperity
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው የከሰዓት በኋላ ውሎው የፓርቲውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ጉባኤው በጠዋቱ ክፍለ ጊዜው ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) የፓርቲው ፕሬዚዳንት እንዲሁም አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች አድርጎ መምረጡ ይታወሳል።