Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የትግራይ ክልል የአየር መሥመር ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ሂደትን ተከትሎ ተዘግቶ የነበረው የአየር ክልል ከዛሬ ታህሣሥ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ክፍት መሆናቸውን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰሜን የኢትዮጵያ የአየር ክልል ውስጥ የሚያቋርጡ የዓለም አቀፍ እና የሃገር ውስጥ የበረራ መስመሮች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልጿል።

አገልግሎት መሥጠት የሚችሉ ኤርፖርቶች በረራ ማስተናገድ የሚችሉ መሆኑንም ኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል።


#EBC
#የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ አቀረበ::

ሰመራ-ሰኔ 21, 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ አቀረበ::

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊነትን መሰረት ባደረገና ተጨማሪ ጉዳት በማያስከትል መልኩ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳስታወቁት፤ ክረምት እየገባ በመሆኑ የትግራይ አርሶ አደር ተረጋግቶ የእርሻ ስራውን እንዲያከናውን፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ለተረጂዎች ያለምንም ችግር እንዲደርስ እና ወቅቱን የሚመጥን ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት የፌዴራል መንግስት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያደርግ ተጠይቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለፈው ሳምንት በይፋ ጥያቄውን ያቀረበው የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች፣ ከቢሮና የዞኖች አመራር አባላት፣ በተለያየ ቦታ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች፣ ከትግራይ ምሁራን፣ ከባለሀብቶችና ከሃይማኖት አባቶች ጋር ተከታታይ ምክክር ካደረገ በኋላ ነው።

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በክልሉም ሆነ በአገሪቷ ላይ የፈጠረው ውስብስብ ችግር ወታደራዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መሆኑን ያወሱት አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፤ ለዚህም እስከ አሁን በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ መፍትሄዎች ሲወሰዱ መቆየቱን አብራርተዋል።

እስከአሁን ህግ የማስከበር እርምጃ ከመውሰድ ባሻገር በህግ የሚታዩ ጉዳዮችን በህግ መፍትሄ ለመስጠት ከጥፋት ሃይሉ ወንጀለኛ የሆነውን ለይቶ ወደ ህግ የመቅረብ ስራ ሲከናወን መቆየቱን ተናግረዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩም ሆነ በፌዴራል መንግስት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎቸን አስታውሰው፤ በቀጣይም ፖለቲካዊ አማራጮችን ታሳቢ ማድረግና የመፍትሄ እርምጃዎችን የመውሰድ አስፈላጊነት ላይ እምነት መኖሩን ጠቁመዋል።

የክልሉ አርሶአደር በዚህ ክረምት ወደ እርሻ ካልገባ የዘር ወቅት ስለሚያልፍ፣ በቀጣይ ገበሬው ለዓመታት ተረጂ ሆኖ የመኖር እድል እንደሚገጥመው ነው ያወሱት።

በዚህም አሸባሪው ቡድን የዚህ ዓይነቱን ቀውስ እየፈጠረ እንደሚሄድ ጠቅሰው፤ “የኢትዮጵያ መንግስትና የመከላከያ ሰራዊት እዳውን እንዲሸከምለት ያደርጋል” ብለዋል።

እንደርሳቸው ገለጻ፤ መንግስትና የእርዳታ ድርጅቶች እርዳታ እንዳያደርሱ፣ ለገበሬው ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ እንዳያቀርቡ እያሰናከለ፣ ህዝብ ተራበ ብሎ ራሱ ይጮሃል፤ ምክንያቱም ህወሃት መኖር የሚችለው የትግራይ ህዝብ ሲሞትና መከራ ሲያገኝ ብቻ ነው ብለዋል።

እንዲህም ሆኖ የኢትዮጵያ መንግሰት ባለፉት ወራት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ለእርዳታ፣ ለመንግስት አገልግሎት ማስቀጠልና ለመሰረተ ልማት ግንባታ አውሏል ነው ያሉት።

ይህም በአገሪቷ አጠቃላይ ኢኮኖሚ በተለይ በሌሎች ክልሎች የሚያደርሰው ጫና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ክልሎች ከበጀታቸው ቀንሰው የትግራይ ክልልን ለማቋቋም ድጋፍ ማድረጋቸውን ለአብነት አንስተዋል።

እርዳታ እንሰጣለን ለሚሉ አካላትም ከሚፈለገው በላይ ተሂዶ ምቹ ሁኔታዎች ተፈጥሯል ብለዋል።

በቀጣይ ደግሞ ሰብዓዊ እርዳታው ወደ ሚፈለገው ቦታ ለማድረስ፣ እርሻ ሥራ እንዳያመልጥ ለማድረግ፣ የተፈናቀለውንም ተረጋግቶ ወደ የቤቱ እንዲመለስ ተጨማሪ የፖለቲካ አማራጭ በማስፈለጉ በተደጋጋሚ ከመንግስት ጋር ንግግር መደረጉን ነው አብርሃም በላይ (ዶ/ር) የገለጹት።

ይህን መነሻ በማድረግ ለፌዴራል መንግስት ባለዘጠኝ ነጥብ ጥያቄ አቅርበናል ብለዋል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ገበሬው ተረጋግቶ እንዲያርስ፣ ለችግረኞች የሰብዓዊ ድጋፍና የእርዳታ ቁሳቁስ ለማድረስ፣ የተፈናቃዮችን ቤት ጠግኖ ወደ ቦታቸው ለመመለስ እንደሚያስችል አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅት በረሃ ካለው ሃይል መካከል የሰላም መንገድ የሚፈልግ መኖሩን አመላክተው፤ ለዚህ ሃይል እድል መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚናገሩት፤ አጥፊው የህወሃት ሃይል የተበተነ ቢሆንም ለብዙ ዘመናት በክልሉ በዘረጋው የፍርሃት መዋቅር በኩል ዜጎች ያስፈራራል፣ ያስገድላል፤ ይገላል።

“ለዜጎች የእርዳታ እህል እንዳይደርስ ያደናቅፋል፤ የእርዳታ ሰራተኞች ይገድላል፤ ዜጎች እርዳታ እንዳይቀበሉ ያስፈራራል፤ ከተቀበሉ በኋላ እንዲያካፍሉት ያስገድዳል” ብለዋል።

“የአጥፊው የህወሃት ቡድን ዋና አላማ ህዘቡን የጦርነት ጋሻ ማድረግ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ ነገር ግን የህዝብን ጥቅም በማስቀደም የተኩስ አቁም ማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው አብራርተዋል።

ችግሮቹን ለመፍታት የፖለቲካ መፍትሄ መውሰድ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ለትግራይ ህዝብ ፖለቲካዊ መፍትሄ መፈለግ ያለበት መንግስት እንጂ ለህዝቡ ግድ የሌለው የህወሃት ጥፋት ሃይል ሊሆን አይችልም” ያሉት አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ፤ በመሆኑም መንግስት ይበልጥ ሆደ ሰፊ ሆኖ ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን መስጠት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።

ለፌዴራል መንግስት የቀረበው የተኩስ አቁም ስምምነት ጥያቄ የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑንም አብርሃም በላይ (ዶ/ር) አብራርተዋል።

#EBC