Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ሊዘዋወር የነበሩ 53 ጩቤ እና ሌሎች ሕገወጥ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር ዋሉ::

ሰመራ-ነሃሴ 25, 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ሊዘዋወር የነበሩ 53 ጩቤ እና ሌሎች ሕገወጥ ቁሳቁስ በቁጥጥር ስር ዋሉ::

ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ሊዘዋወሩ የነበሩ ጩቤ፣ የጥይት መያዣ ካርታ እና ሌሎች ሕገወጥ ቁሳቁስ በዛሬው እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 አካባቢው 53 ሕገወጥ ጩቤ፣ 30 የጥይት መያዣ ካርታ፣ 30 እንግብ፣ 30 የትጥቅ መያዣ ቀበቶ እንዲሁም 3 ኪሎ የሚመዝን አደገኛ እጽ መሰል ነገር ከከሚሴ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሊዘዋወር ሲል በፖሊስ እና በማህበረሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ሕገወጥ ቁሳቁሱን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ከሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#EBC