Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ጁንታው በጋሊኮማ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሶስት ቀን ሀዘን ታውጇል።

#ሰመራ-ነሀሴ 05/2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አሸባሪው የህወሀት ጁንታ በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ በጋሊኮማ ጊዚያዊ መጠለያ ተጠልለው የነበሩ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሀዘን ቀን እንዲሆን የአፋር ክልል መንግስት አውጇል።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሴኮ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ጁንታው በጋሊኮማ በንፁሀን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ እጅግ ዘግናኝ እንደነበር ገልፀው የክልሉ መንግስትም ይህን ጥልቅ ሀዘን አስመልክቶ የሶስት ቀናት ሀዘን ማወጁን ገልፀዋል።

ታሪክ የማይረሳው 107 ህፃናትን, 89 ሴቶችን እና 44 አዛውንቶችን ህይወት የቀጠፈውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ያካሄደው የህወሀት ጁንታ ድንገት በከፈተው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት ንፁሃን አርብቶ አደሮች መገደላቸውና መቁሰላቸው እንዲሁም በመጋዝን የነበረ የአስቸኳይ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ይታወሳል።

ጁንታው ገና ቀድሞ በረሀ እያለ የነበረውን የአፋርን መሬቱ ወደ ራሱ የማካለል ቅዠትን በግርግር መፈፀም የሚያስችለው መስሎት በፈፀመው ወረራ አርብቶ አደሩን ማህበረሰብ የጥቃት ሰለባ አድርጎታል።

በተለይም በጋሊኮማ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ጥቃት ፈፅሟል አሽባሪው ህወሀት። ይህንንም ዘግናኝ ጭፍጨፋ አስመልክቲ በአፋር ክልል ውስጥ ከዛሬ ነሀሴ 05 /2012 እስከ ነሀሴ 07/2013 ድረስ የሀዘን ቀን እንዲሆንና የአፋር ክልል ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ የክልሉ መንግስት ወስኗል።

ይህን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ውድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በያሉበት ሆነው እንዲቃወሙና እንዲያወግዙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

t.me/AfarMassMediaAgency

#አፍ/ብ/ክ/መ/ካ/ጽ/ቤት