#ሰኔ 14 ድምፅ የመስጠት ሂደት የማይካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢዎች አሉ፦ ምርጫ ቦርድ
***************
ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች ድምፅ የመስጠት ሂደት የማይካሄድባቸው የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢዎች እንደሚኖሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
እነዚህ የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢዎች በፀጥታ ችግሮች ምክንያት የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው ቦታዎች፣ የመራጮች ምዝገባ ተጀምሮ የተቋረጠባቸው ቦታዎች እና የመራጮች ምዝገባ ላይ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው ወይም ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ ጉልህ የአሠራር ችግር በማየቱ ማጣራት የወሰነባቸው ቦታዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ድምፅ መስጠት ሂደቱ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ተግባራዊ ሊሆን የማይችልባቸው የምርጫ ክልሎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል (4 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመባቸው ቦታዎች፦ 1. መተከል ምርጫ ክልል፣ 2. ሺናሻ ልዩ ምርጫ ክልል 3. ካማሽ ምርጫ ክልል እና 4. ዳለቲ ምርጫ ክልል ናቸው።
ሶማሌ ክልል (14 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ የቀረበባቸው እና የማጣራት ሂደቱ ላይ የሚወሰኑ፦ 1. አራቢ የምርጫ ክልል፣ 2. ደግሃመዶ ምርጫ ክልል፣ 3. ጎዴ የምርጫ ክልል 4. ጂግጂጋ 1 የምርጫ ክልል፣ 5. ጂግጂጋ 2 የምርጫ ክልል፣ 6. ቀብሪደሃር ምርጫ ክልል፣ 7. ቀላፎ ምርጫ ክልል፣ 8. ዋርዴር ምርጫ ክልል፣ 9. ፊቅ ምርጫ ክልል፣ 10. ገላዲን ምርጫ ክልል እና 11. ደገሃቡር ምርጫ ክልል ሲሆኑ
የመራጮች ምዝገባ ሂደት በክልሉ መስተዳድር የተቋረጠባቸው፦ 1. አይሻ ምርጫ ክልል፣ 2. ኤረር ምርጫ ክልል፣ 3. ሽንሌ ምርጫ ክልል ናቸው።
ኦሮሚያ ክልል (7 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)፦ 1. ቤጊ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ፣ 2. ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል - ምእራብ ወለጋ፣ 3. አያና ምርጫ ክልል - ምስራቅ ወለጋ፣ 4. ገሊላ ምርጫ - ምስራቅ ወለጋ፣ 5. አሊቦ ምርጫ ክልል -ሆሮ ጉድሩ፣ 6. ጊዳም ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ እና 7. ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል- ሆሮ ጉድሩ ናቸው።
አማራ ክልል (8 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)፦ 1. ማጀቴ (ማኮይ) ምርጫ ክልል፣ 2. አርጎባ ልዩ ምርጫ ክልል፣ 3. ሸዋሮቢት ምርጫ ክልል፣ 4. ኤፌሶን ምርጫ ክልል፣ 5. ጭልጋ 1 ምርጫ ክልል፣ 6. ጭልጋ 2 ምርጫ ክልል፣ 7. ላይ አርማጭሆ ምርጫ ክልል እና 8. ድልይብዛ ምርጫ ክልል ናቸው።
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል (4 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ያልተጀመረባቸው (በጸጥታ ችግር)፦ 1. ዘልማም ምርጫ ክልል፣ 2. ሱርማ ልዩ ምርጫ ክልል፣ 3. ዲዚ ልዩ ምርጫ ክልል እና 4. ሙርሲ ልዩ ምርጫ ክልል ናቸው።
ሐረሪ ክልል (3 ምርጫ ክልል) - የመራጮች ምዝገባ ከፍተኛ የተዛባ አሰራር የታየባቸው እንዲሁም በህግ የተያዘ ጉዳይ፦ 1. ጀጎል ልዩ ምርጫ ክልል 2. ጀጎል መደበኛ ምርጫ ክልል እና 3. ጀጎል ዙሪያ እና ሁንደኔ ምርጫ ክልል መሆናቸውን ቦርዱ አስታውቋል።
በሌላ በኩል በጋምቤላ ክልል ዲማ ምርጫ ክልል እና አኮቦ ምርጫ ክልል የመሠረተ ልማት እና የመጓጓዥ ችግር ከፍተኛ በመሆኑ በልዩ ሁኔታ የክልል እና የፌደራል መንግሥትን ከፍተኛ እገዛ ይጠይቃል ብሏል።
#EBC