Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ዛሬ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፣፣

ሰመራ-የካቲት 14, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ምክር ቤቱ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ዛሬ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፣፣

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ በሚገኘው ልዩ ስብሰባው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮችን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ኤፍቢሲ ዘገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ከዚህ በፊት ዝርዝራቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

የተገኘውን ግብዓት ምክር ቤቱ ከተመለከተ በኋላም መስፈርቱን በከፍተኛ ደረጃ አሟልተዋል ያላቸውን እጩ ኮሚሽነሮች በመምረጥ እንዲሾሙ ለምክር ቤቱ አቅርቧል።

በዚህ መሰረትም፦

1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ
3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ
4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ
5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን
6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ
7. አቶ ዘገየ አስፋው
8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር
10. አቶ ሙሉጌታ አጎ እና
11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ እጩ ኮሚሽነር ሆነው ቀርበዋል።

ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደው በሚገኘው ልዩ ስብሰባ በእነዚህ እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከተወያየ በኋላ ይሾማቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

#EBC