Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፣፣

ሰመራ-ሰኔ 28፣ 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ሚኒስቴሩ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ አደረገ፣፣

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
ቤንዚን - 47 ነጥብ 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ - 49 ነጥብ 02 በሊትር
ኬሮሲን - 49 ነጥብ 02 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ - 53 ነጥብ 10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ - 52 ነጥብ 37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ - 98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አስታውቋል፡፡

#Walta