Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፣፣

ሰመራ- ሚያዝያ 01, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ገንዘብ ሚኒስቴር መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ በቀጥታ እንዲገቡ ወሰነ፣፣

ሚያዝያ 1/2014 (ዋልታ) መሰረታዊ የምግብ ሽቀጦች የሆኑት ዘይት፣ ስንዴ፣ ስኳር፣ የህጻናት ወተት እና ሩዝ ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፍቃድ (በፍራንኮ ቫሉታ) በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል በቀጥታ እንዲገቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ወሰነ።

መንግሥት በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እንዲቻል እና በርካታ የውጭ ሀገር የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሚና መጫወት እንዲችሉ የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄ እያቀረቡ በመሆኑ ነው ብሏል።

ቀረጥና ታክሱ በሚመለከት በገንዘብ ሚኒስቴር በ22/3/2013 ዓ.ም በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት እንዲፈጸምና አፈጻጸሙም ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በኩል ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግበት መወሰኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Walta