Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ፣፣

ሰመራ-አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት- ታህሳስ 04/2013

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በመቀሌ ከከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር ተወያዩ፣፣

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሕግ ማስከበር ሂደቱን ከመሩ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ጋር መቀሌ ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በአካባቢው ለሕዝቡ እየተደረገ ያለው ሠብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

መቀሌ ላይ በተካሄደው ውይይት ሌተና ጄኔራል አበባው ታደሰና ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

በጁንታው ላይ የተገኘው ድል የሚያኩራራ ሳይሆን 'የምንማርበትና የኢትዮጵያን ቀጣይነት የምናረጋግጥበት ነው' ማለታቸውን ኢዜአ ከስፍራው ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይን ክልል መልሶ ለማቋቋም መንግስት በሙሉ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በአካባቢው ለሕዝቡ የተጀመረው ሠብዓዊ ድጋፍ እንደሚቀጥልና መንግስት በሕግ ማስከበሩ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን እንደሚደግፍ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር አባላት ጋር በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

በተለይም ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚሰሩ ስራዎች ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


#ኢ.ቢ.ሲ
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ፣፣

ሰመራ-መጋቢት 27,2013 (አፍ.ብ.መ.ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

ከመጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች፡

- መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር,

- ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር,

- ግዛው ተስፋዬ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾመዋል።


ምንጭ: OBN
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው ለሥራ ጉብኝት ቱርክ አንካራ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቆይታቸው ፕሬዚደንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶጋንን አግኝተው በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ የትኩረት በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#EBC
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ፣፣

ሰመራ-መስከረም 27, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሠጡ፣፣

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስቴር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡

1. አቶ አደም ፋራህ - በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ

2. አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ - በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
3. ዶ/ር ስለሺ በቀለ - በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
4. ዶ/ር ለገሰ ቱሉ - በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ

በተጨማሪም፡
- ዶ/ር ምህረት ደበበ - የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት፤
- አቶ ፍሰሃ ይታገሱ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
- እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ - የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡


#EBC
#ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ:

ሰመራ-መስከረም 29, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በትናንትናው እለት ለ22ቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታዎችን እንዲሁም ለሌሎች ሁለት ተቋማት ኮሚሽነሮችን ሾመዋል፡፡

ከተሿሚዎቹ መካከል የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር አካላት የተካተቱ ሲሆን ከእናት ፓርቲ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ከነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ወ/ሮ ነብያ መሃመድ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል፡፡

ተ.ቁ
የመስሪያ ቤቱ ስም
የተሿሚው ስም
የተሾሙበት የሃላፊነት ቦታ


1.
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

2.
ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አምባሳደር ብርቱካን አያና
የኃብት ማኔጅመንትና አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

3.
ገንዘብ ሚኒስቴር
ዶ/ር እዮብ ተካልኝ
የፊሲካል ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

4.
ገንዘብ ሚኒስቴር
ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰዉ
የኢኮኖሚ ትብብር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

5.
መከላከያ ሚኒስቴር
ዶ/ር አህመድን መሐመድ
የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

6.
መከላከያ ሚኒስቴር
ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ
የፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

7.
ግብርና ሚኒስቴር
ዶ/ር መለሰ መኮንን
የእርሻና ሆልቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

8.
ግብርና ሚኒስቴር
ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ
የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

9.
ግብርና ሚኒስቴር
ፕሮፈሰር እያሱ ኤልያስ
የተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

10.
ግብርና ሚኒስቴር
ዶ/ር ሶፊያ ካሳ
የግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

11.
ሠላም ሚኒስቴር
አቶ ታዬ ደንደአ
ሚኒስትር ዴኤታ

12.
ሠላም ሚኒስቴር
ዶ/ር ስዩም መስፍን
ሚኒስትር ዴኤታ

13.
ፍትህ ሚኒስቴር
አቶ አለምአንተ አግደዉ
የመንግስት ህግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

14.
በፍትህ ሚኒስቴር
አቶ ፍቃዱ ፀጋ
የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

15.
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አቶ ዳንጌ ቦሩ
የንግድ ትስስርና ውጪ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

16.
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አቶ ሐሰን መሀመድ ሙአሊን
የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

17.
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አቶ እንዳለዉ መኮንን
የጥራት መሠረተ ልማትና ማረጋገጫ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

18.
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
አቶ ሽሰማ ገ/ስላሴ
የመሠረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

19.
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
አቶ ታረቀኝ ቡልቡልታ
የዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

20.
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

21.
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
ወ/ሮ ሁሪያ አሊ
የአይሲቲና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

22.
ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ዶ/ር አብረሃ አዱኛ
የዉሃ ሃብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

23.
ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋቅሻዉ
የመጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

24.
ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር
ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ
የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

25.
ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
አቶ ፈንታ ደጀን
የከተማ አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

26.
ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
አቶ ሄኖስ ወርቁ
የቤቶችና ከተማ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

27.
ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር
አቶ ካሊድ አብዱራሂማን
የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

28.
ማዕድን ሚኒስቴር
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ
የማዕድን ነዳጅ ልማትና ቁጥጥር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

29.
ማዕድን ሚኒስቴር
አቶ ቶማስ ቱት
የጂኦ ሳይንስና ምርምር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

30.
ጤና ሚኒስቴር
ዶ/ር ደረጄ ድጉማ
የአገልግሎትና ፕሮግራም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

31.
ጤና ሚኒስቴር
ወ/ሮ ሰሀርላ አብዱላሂ
የኃብትና ግብአት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

32.
ጤና ሚኒስቴር
ዶ/ር አየለ ተሾመ
የሥርዓት አቅም ግንባታ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

33.
ትምህርት ሚኒስቴር
ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ
የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

34.
ትምህርት ሚኒስቴር
ዶ/ር ፈንታ ማንደፍሮ
የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

35.
ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
አቶ ካሳሁን ጎፌ
የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

36.
በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር
አቶ በረኦ ሐሰን በረኦ
የአገልግሎትና ቁጥጥር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

37.
ቱሪዝም ሚኒስቴር
አቶ ስለሺ ግርማ
የቱሪዝም መዳረሻና መሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

38.
ቱሪዝም ሚኒስቴር
ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት
የቱሪዝም ፕሮሞሽንና ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

39.
ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ወ/ሮ አየለች እሸቴ
የማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

40.
ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ
የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

41.
ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
ወ/ሮ ሙና አሕመድ
የወጣቶች ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

42.
ገቢዎች ሚኒስቴር
አቶ ተስፋዬ ቱሉ
የታክስ ሥርዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

43.
ገቢዎች ሚኒስቴር
ወ/ሮ መሰረት መስቀሌ
የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

44.
ፕላንና ልማት ሚኒስቴር
ወ/ሮ ጥሩማር አባተ አያሌዉ
የክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

45.
ፕላንና ልማት ሚኒስቴር
ዶ/ር ነመራ ማሞ
የፕላን ስታቲስቲክስ እና ፖሊሲ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

46.
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ዶ/ር በከር ሻሌ
የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

47.
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
አቶ አሰግድ ጌታቸዉ​
የሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

48.
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
አቶ ንጉሱ ጥላሁን
የሥራና የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

49.
ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ወ/ሮ ነብያ መሀመድ
አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ

50.
መስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር
ዶ/ር እንድሪያስ ጌታ
የቆላማ አከባቢ ምርምርና ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

51.
መስኖና ቆላማ አከባቢ ሚኒስቴር
ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ
የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

52.
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ
የባሕልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

53.
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
ወ/ሮ ነፊሳ አልማሂዲ​
የኪነጥበብና ስነጥበብ የፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

54.
ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር
አምባሳደር መስፍን ቸርነት
የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

55.
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አቶ ተስፋዬ ዳባ
የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

56.
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳዉሎስ
የአገልግሎቶችና መልካም አስተዳደር ክትትል ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

57.
ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አቶ ወርቁ ጓንጉል
የሀገራዊ ፕሮጀክቶች ክትትል ሚኒስትር ዴኤታ

58.
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አቶ ከበደ ደሲሣ
ሚኒስትር ዴኤታ
#ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጠላት ኃይል እጁን እንዲሰጥ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው ሕወሓት ታጣቂዎች እጃቸውን እየሰጡ ነው መሆኑ ተገለጸ።

ሰመራ-ህዳር 25, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)-

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ግንባር አምርተው የወገንን ጦር መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ግንባር ድል እየተመዘገበና የጠላት ሀይል እየተበታተነ መሆኑ ተመላክቷል።

'በዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት' የወገን ጦር ድል በድል እየደራረበ ሲገሰግስ በአንፃሩ የጠላት ኃይል በየጦር ግንባሩ ሽንፈትን እየደረሰበትና እየተደመሰሰ ይገኛል።

ለአብነትም በጋሸና፣ በሸዋ፣ በወረኢሉ፣ በጭፍራ እና በሌሎች ግንባሮች የወገን ጥምር ጦር ባደረገው ተጋድሎ በርካታ ከተሞችን ከወራሪው ኃይል ነፃ ማድረግ ችሏል፣ የወራሪው ቡድንም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት በመፈርጠጥ ላይ ይገኛል።

ከመደምሰስ የተረፈው የወራሪና ዘራፊ ቡድኑ ኃይልም እየተበታተነ ሲሆን የወገን ጦር በየግንባሩ የተበታተነውን የጠላት ኃይል የመልቀም ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ራዕይና ግቡ በማይታወቅ ጦርነት በዕውር ድንብር ጁንታው ያሰለፋቸው የትግራይ ወጣቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ መሆኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።

በዚህም ወጣቶች በማያውቁት አካባቢና ራዕይ በሌለለው ጦርነት ገብተው እንዳያልቁ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊትና ለክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የትግራይ እናቶችም ልጆቻቸው ራዕይ በሌለው ጦርነት እንዳያልቁ "ልጆቻችን የት ደረሱ" ብለው መጠየቅ እንዳለባቸው መግለፃቸው አይዘነጋም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎም በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ለውጊያ ያሰለፋቸው ታጣቂዎች እጃቸውን ለወገን ኃይል እየሰጡ ነው።
እጃቸውን የሰጡት ምርኮኞቹም ባለማወቅና በመገደድ ወደ ውጊያ መሰለፋቸውን ገልፀው፤ ቡድኑ በደረሰበት ሽንፈት እጅ ለመስጠት መገደዳቸውን ገልፀዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በቤተሰብ ልጅ አምጡ እየተባሉ በአሸባሪው ተገደው ቢሰለፉም በእስካሁኑ ድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ ጠይቀዋል።

አሸባሪው ቡድን የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን አሸባሪ ቡድኑ ተሸንፏል ብለዋል።

በርካታ ጓደኞቻቸው በከንቱ ሕይወታቸውን የሚናገሩት ምርኮኞቹ፤ እነርሱ ግን እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠታቸው እድለኞች ነን ብለዋል።

እጅ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በህብረተሰቡ ለተደረገላቸው እንክብካቤ አመስግነዋል።
ሌሎች የትግራይ ወጣቶችም በአሸባሪው ቡድን እያሸነፍን ነው በሚል በሚዲያ በሚነዛው ሀሰተኛ መረጃ እየተደናገሩ ለውጊያ እንይሰለፉ፣ ውጊያ ላይ የተሰለፉትም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የትግራይ ወጣቶች በጁንታው ጦርነት ከመማገድ ይልቅ ለወገን ጦር እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸውን ማዳን እንዲችሉ የኃይማኖት አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።

በየግንባሩ ተሸንፎ የተበታተነው የጠላት ኃይል የዘረፈውን ሀብት ይዞ እንዳይሸሽ ህብረተሰቡ አካባቢውን ተደራጅቶ እንዲጠብቅ፣ ብሎም የወራሪው ኃይል አባላትን እየማረከ ለመከላከያ ሰራዊት እንዲያስረክብ መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

ምንጭ: ኢዜአ