Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#የደቡብ ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት እጩ የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ።

ሰመራ-መስከረም 22/2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

የደቡብ ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት እጩ የካቢኔ አባላት ሹመት አጸደቀ።

መስራች ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት በርዕሰ መስተዳድሩ የቀረበለትን የእጩ የካቢኔ አባላት ሹመት አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፦

1. አቶ ጥላሁን ከበደ-የመንግስት ዋና ተጠሪ

2. አቶ አቶ ተስፋዬ ይገዙ - ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ

3. ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ -በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ

4. አቶ ኡስማን ሱሩር - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሃላፊ

5. ዶክተር ባዩሽ አያሌ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የልማትና እቅድ ኮሚሽን ኮሚሽነር

6. ዶክተር አበባየሁ ታደሰ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

7. አቶ አለማየሁ ባውዱ -በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ

8. የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ- አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል

9. የክልሉ መንግስት ረዳት ተጠሪ- አቶ ይሁን አሰፋ

ከዚህ ውጭም፣

1. አቶ ተፈሪ አባተ - የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ

2. አቶ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ - አቶ ሶፎኔያስ ደስታ

3. አቶ ማሄ ቦዳ -የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ሃላፊ

5. ኢ/ር አክሊሉ አዳኝ - የውሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ

6. አቶ እንዳሻው ሽብሩ -የጤና ቢሮ ሃላፊ

7. አቶ አክሊሉ ለማ- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ሃላፊ

10. ወ/ሮ በይዴ ሙንዲኖ - የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ -

11. አቶ ሀልገዮ ጅሎ - ኢንቨስትመንትና ኢንደስትሪ ቢሮ ሃላፊ

12. ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም - የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

13. አቶ ሀይለማሪያም ተስፋዬ- የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

14. አቶ ዘይኔ ቢልካ- የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ

15. ዶክተር ኦንጋዮ ኦዳ -የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ

16. አቶ ገብሬ ጋጌ- የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ

17. ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን -የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ

21. አቶ ተስፋዬ ብላቱ- የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ

22. አቶ ቢረጋ ብርሃኑ - የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ሃላፊ

23. አቶ አንተነህ ፍቃዱ- የደንና አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ ሃላፊ

24. አቶ ከበደ ሳህሌ- የአርብቶ አደር ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ

25. አቶ ሎምባ ደምሴ- የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ቢሮ ሃላፊ

26. አቶ ተመስገን ፈይሳ- የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ተሰጥቷቸዋል።

ከእነዚህ የካቢኔ አባላት ዝርዝር ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ተወካዮች አለመካተታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አስታውቀዋል ።

ለዚህም ምክንያቱ በሪፈረንደሙ ውጤት መሰረት የራሳቸውን ክልል በቅርቡ የሚመሰርቱ በመሆኑ ነው ብለዋል አቶ እርስቱ።

#Walta
#ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በበዓለ ሲመታቸው ያደረጉት ንግግር

መስከረም 24/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በርከት ያሉ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ጥቂቶቹም፦

ሕዝባችን ጥቃት የሚያንገበግበውና ልዩነቱን ትቶ ለአገሩ የሚሰለፍ ነው፤ ይህም እንድኮራ ከሚያደርጉኝ መካከል ነው።

ኢትዮጵያ ድጋፍ በፈለገች ጊዜ ለደረሳችሁላት ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ።

ኢትዮጵያ በአቃፊነቷ በመርከብ ትመሰላለች።

ኢትዮጵያ ካዘመመችበት ቀና የምትልበት ጊዜው አሁን ነው ይህን ለማሳካት ኃላፊነት ተጥሎብናል።

ኢትዮጵያ አያሌ ውጣውረዶችን ተሻግራ እዚህ ደርሳለች።

6ኛው ምርጫ የምኞታችንን ያህል እንከን የሌሽና የተሳካ ነው ባይባልም የዘመናት የዴሞክራሲ መሻታችንን ለመጀመር መነሻ ሆኗል።

በምርጫው የተመዘገበው ድል የአንድ ፓርቲ ወይም መንግሥት ሳይሆን ኢትዮጵያ እንደአገርና ኢትዮጵያዊያን እንደ ሕዝብ በአንድነት ያሸነፍንበት ነው።

ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ አካታች ብሔራዊ የምክክር መድረክን እንፈጥራለን።

የሰሜኑ ጦርነት ጥቂት ግለሰቦች እኛ ያልመራናት አገር አታስፈልግም ብለው በግፍ የከፈቱት ነው፤ በዚህም ህፃናት ለጦርነት እያሰለፈና እንስሳትን ሳይቀር እየገደለ ይገኛል።

ፀባችን ከኢትዮጵያ ጠልኃይሎች ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ኢትዮጵያ ጠንካራ የደኅንነትና የፀጥታ ኃይል ትገነባለች።

ማንኛውም ወዳጅነት የኢትዮጵያን ክብርና ጥቅም የሚነካ አይሆንም ሊሆንም አይገባም።

ዓባይ ማለት የመነሳታችን ምሳሌ በራሳችን የመቆም ማሳያና መተሳሰሪያችን ነው፤ ግድቡም ይጠናቀቃል።

መንግሥት የኑሮ ውድነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል።

ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር አበክረን እንሰራለን።

ሌብነትን እንደ ትልቅ ፈተና ወስደን ለመሻገር እንሰራለን።

ለመጪው ትውልድ የተሻለ አገር ለማስረከብ ተደምረን ቀን ከሌት እንሰራለን።

እንደኅዳር አህያ ያለው ሁሉ ካልጫንኳችሁ እንዲለን ያደረገውን ድህነታችንን ለማሸነፍ እንተጋለን።

መጪዎቹ ዓመታት ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከአይበገሬነት ማሳያ ጋር የሚተሳሰርበት እንደሚሆንም እናምናለን።

ኢትዮጵያ ትናንት ነበረች ዛሬም አለች ነገ አቧራዋን አራግፋ ስትነሳ ደግሞ ከፊቷ የሚቆም ምድራዊ ኃይል አይኖርም።

#Walta