#ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፣፣
ሰመራ፣ መስከረም 23፣2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)
ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሠረታል፣፣
በኢፌዴሪ ሕገ መንግስት መሠረት ነገ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት ይመሰረታል።
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2፥ በሕዝብ ተመርጦ አዲስ የሚቋቋም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜውን መጀመር ያለበት በ“መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ነው” ብሎ በደነገገው መሠረት ነው ነገ በፌዴራል ደረጃ አዲስ መንግሥት የሚመሠረተው።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በቅርቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም፥ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ በተደረገው የሰኔ 14ቱ የምርጫ ውጤት መሰረት፤ መስከረም 24 ቀን 2014ዓ.ም አዲስ መንግሥት እንደሚመሰረትና ለዚህም ህጋዊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ነው ያስታወቁት።
የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 56 ላይ “ በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል፤ ይመራል” ብሎ በደነገገው መሠረት፥ ሰኔ 14 ቀን 2013 በተካሄደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ፓርቲ ነው አዲስ መንግስት የመመስረት የፖለቲካ ሥልጣን ያለው።
በመሆኑም በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ እንደተደረገው የምርጫ ውጤት፥ መንግስት የመመስረት የፖለቲካ ሥልጣን ያለው ድርጅት የብልጽግና ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል።
አዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በዚህ ታሪካዊ ጉባኤው የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሾም ሲሆን፥ ተሿሚው ጠቅላይ ሚኒስትርም በአዲስ መልክ በሚዋቀረው አደረጃጀት አግባብ ካቢኔያቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብ ያስፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ያደረገውና ሊመራኝ ይገባል ብሎ ላመነበት አካል ድምጹን የሰጠው ህዝብ፥ በሚቋቋመው አዲስ መንግስት የሥራ አፈጻጸም ላይ ግልጽ አስተያየት የሚሰጥበትና ጥያቄ የሚያቀርብበት የአሰራር ሥርዓት እንደሚዘረጋም አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገልጸዋል።
አዲስ የሚመሰረተው የሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት የሕዝብ ውክልና በተግባር የሚንጸባረቅበት ምክር ቤት ይሆናልም ነው ያሉት።
አደረጀጀቱም የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለማፋጠንና የህዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በሚያስችል አግባብ አንደሚዋቀር አፈ ጉባኤው ጠቁመዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፥ ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት፥ ወቅቱ የኢትዮጵያን በጎ ነገርና ብልጽግና ለማየት የማይሹ የውጭ ሃይሎችና የውስጥ ባንዳዎች በአገራችን ላይ አደጋ ለመፍጠር የሚረባረቡበት ጊዜ በመሆኑ፥ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት መላውን ህዝብና የፖለቲካ ሃይሎችን በማስተባበር ሀገራዊ ኃላፊነቱን በብቃት መወጣት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል፡፡
አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ እየተደረገ ያለው ዘመቻ በአጭር ጊዜ መቋጨት አለበት የሚሉት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ አዲስ የሚዋቀረው መንግስት ለሀገር ስጋት የሆኑ ኃይሎችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድና በአገራችን ሰላምን ማስፈን ይኖርበታል ብለዋል፡፡
#FBC