Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አዲሱ የሚመሰረተው መንግሰት ከነበረው በተሻለ ሙህራንን እና ሴቶችን ሊያካትት ይገባል ተባለ።
#አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃር ኢብራሂምን ከንቲባ አድርጎ ሾመ፣፣

ሰመራ-መስከረም 19, 2014 (አፋ.ብ.መ.ድ)

አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ ከድር ጁሃር ኢብራሂምን ከንቲባ አድርጎ ሾመ፣፣

በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድሬዳዋ ህዝብን ይሁንታ ያገኙ ተወካዮች ባካሄዱት የምስረታ ጉባዔ አሸናፊው ብልፅግና ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩ አመራሮች ተቀብሎ ሾሟል::

በዚህም አቶ ከድር ጁሃር የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ሆነው ተሾመዋል::

ለመጪዎቹ 5 ዓመታት ከተማዋን እንዲመሩም በምክር ቤቱ ይሁንታ አግኝተዋል::

አዲሱ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ከከንቲባው ሹመት በተጨማሪም ወ/ሮ ፈቲያ አደም ዑመርን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ እንዲሁም ወ/ሮ ከሪማ አሊን ምክትል አፈ ጉባዔ አድርጎ በሙሉ ድምፅ ሾሟል::

ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባልነት በተካሄደው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም 186 መቀመጫዎች ማሸነፉ ይታወሳል::

ቀሪ 3 የምክር ቤቱ መቀመጫዎችም መስከረም 24 በሚደረግ ምርጫ የሚሟሉ ይሆናል::

#AMN