Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች እየተከፋፈለ ነው፣፣

ሰመራ፣ ጳጉሜን 5፣ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ለክልሎች እየተከፋፈለ ነው፣፣

የዘመን መለዋጫ በዓልን አስመልክቶ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይከሰተ ከውጪ የገባው የምግብ ዘይት ወደ ክልሎች እየተከፋፈል መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት÷ መንግስት በሃገሪቱ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በርካታ ጫናዎች ቢኖሩበትም ጫናውን ተቋቁሞ ሃገር እንድትቀጥል ጥረቶች በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡


መንግስት የዘመን መለወጫ በዓል መምጣቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ የዘይት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው በማሰብ ያለውን ውስን የውጪ ምንዛሬ ተጠቅሞ ዘይት ከውጪ ሃገር ማስመጣቱን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ወቅት ከውጪ የገባው ዘይት በአንዳንድ ምክንያቶች በተፈለገው ጊዜ ባይደርስም÷ አሁን ግን ለክልሎች እየተሰራጨ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC