Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ፣፣

ሰመራ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (አፋ.ብ.መ.ድ)

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ፣፣

የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ወሳኝ በሆኑ ሸቀጦች ላይ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል።

በመግለጫቸውም ፖስታ እና ማካሮኒ የጉምሩክ ቀረጡ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደተነሳላቸውም ነው የተናገሩት።

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና የሩዝ ምርቶች ከውጭም ሆነ ከሃገር ውስጥ ግዥ ሲፈጸም ከማንኛውም ቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗልም ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ባለፈም በዶሮ እንቁላል ላይ የነበረው ተጨማሪ እሴት ታክስ ፍላጎት እና አቅርቦት እስከሚጣጣም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ ለገበያ እንዲቀርብ ተወስኗልም ነው ያሉት።

ይህም ከዛሬ ጀምሮ ለሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እና አስፈጻሚ አካላት መመሪያ መተላለፉን አንስተዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው በመግለጫቸው ያለ ውጪ ምንዛሬ ሸቀጦችን ከውጪ የማስገባት ፈቃድ (የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ) ለ6 ወራት በመራዘሙ ምርት ማስገባት የጀመሩ መቀጠል እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

#FBC