Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውጪ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን ተጠያቂ እናደርጋለን-ፖሊስ

ሰመራ-ሰኔ 16/2013 (አ.ብ.መ.ድ)

ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ውጪ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን በህግ ተጠያቂ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፤ በመዲናዋ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን እና ድምጽ የተሰጠባቸው የምርጫ ቁሳቁሶች ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ምርጫ ክልሎች መጓጓዛቸውን ገልፀዋል።

ምርጫው በከተማው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ብሎ የተደረገው ዝግጅት እገዛ ማድረጉን ገልፀው ፖሊሰ ገለልተኛ ሆኖ ለየትኛውም ቡድን ሳያዳላ አገልግሎቱን መስጠቱን ነው የተናገሩት።

በቅድመ፣ በምርጫው እለት እና በድህረ ምርጫ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን ቀድሞ በመተንተን የፀጥታ ሃይሉ ዝግጅት ማድረጉን አስረድተዋል።

በዚህም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስችሏል ብለዋል ኮሚሽነሩ።

በድህረ ምርጫም ሂደቱ ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ፖሊስ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በትብብር መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በዚሁ ሂደት የምርጫ ውጤት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ብቻ መገለጽ እንዳለበት በህግ የተደነገገ በመሆኑ ከዚህ ውጭ ውጤት ይፋ የሚያደርጉ አካላትን ፖሊስ በህግ ተጠያቂ ያደርጋል ብለዋል።

በአንዳንድ ህገ ወጥ የሚለቀቁ ያልተረጋገጡ ውጤቶች ፍፁም ህጋዊነት የሌላቸው እና በምርጫ ህጉ መሰረት ተጠያቂ የሚያደርጉ መሆኑንም ነው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለምርጫው ሰላማዊ ሂደት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከአገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፌዴራል ፖሊስ፣ ብሄራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር የነበረው ትብብር የላቀ እንደነበርም ጠቅሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ለፖሊስ ላደረገው የሎጀስቲክ ድጋፍም ኮሚሽነር ጌቱ አመስግነዋል።

#AMN