Afar Mass Media Agency (AFMMA)
1.09K subscribers
3.65K photos
161 videos
2 files
655 links
This channel is an official channel of Afar Mass Media Agency (AFMMA).
AFMMA is an autonomous government organization accountable to the regional Council of the Afar region.
Download Telegram
#ኤርትራ እና ሱዳን በኢትዮጵያ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ

አፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት-ህዳር 02, 2013

ኤርትራ እና ሱዳን በኢትዮጵያ ጉዳይ መወያየታቸው ተገለጸ::

የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አማካሪ የማነ ገብረ አብ የተካተቱበት የኤርትራ ልዑክ ዛሬ ካርቱም አቅንቶ ከሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ም/ቤት ፕሬዝዳንት አል-ቡርሃን እና ከጠ/ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር መወያየቱን የሱዳን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡
የኤርትራ ልዑክ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ የተላከ መልዕክት ለሱዳን መሪዎች ያደረሰ ሲሆን በቆይታቸው ከሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ካደረጉት ውይይት በተጨማሪ የሁለቱም ጎረቤት በሆነችው ኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ችግር መምከራቸውንም የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል በትዊተራቸው ገልጸዋል፡፡
ይሁን እንጂ ስለውይይታቸው የተባለ ዝርዝር ጉዳይ የለም፡፡

#Sudan_Eritrea #Ethiopia

#al-Ain News