Audio
✝ #በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
#SUBSCRIBE ማድረግዎን አይርሱ
#SHARE በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
#SUBSCRIBE ማድረግዎን አይርሱ
#SHARE በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
❤1
Forwarded from መሠረተ አሚን - Meserete Amin
💠መስቀል
❖✟✞✝✥❖💠💠
➕➕➕ ነደ እሳትን የተሸከመ የኪሩቤልም ባልንጀራ የሆነ እንደ ድንግል ማርያም ስም አራት ፊደል ያለው ነበልባላዊ የእሳት መንበር።
✣✣✣ አዳምን ከሞት ያወጣው የሕይወት ዛፍ።
✥✥✥ የኃጢአትን ቀላይ የገታ መርከብ።
❖❖❖ ባሕረ እሳትን ያሻገረ የድኅነት ትርክዛ።
✞✟✟ነፍሳት የሕይወት እንጀራን የጠገቡበት ማዕድ!
✟✟✟ክርስቶስና ቤተክረስተያን የተሞሸሩበት የሠርግ ቦታ።
✝✝✝ምእመናን የተጸነሱበት መካነ ክርስትና።
🔸🔸🔸 ቤተክርስቲያን የጸናችበት መሠረተ ሃይማኖት።
🔹🔹🔹የፍስሐ ኩሉዓለም ክርስቶስ ደም የፈለቀበት ሙሐዘ ትፍሥሕት!
🔶🔶🔶 ከሕይወት ውኃ ከክርስቶስ የተተከለ ሁል ጊዜ የሚያፈራ የሕይወት ዛፍ።
🔷🔷🔷 የንጉሥ ልጅ በአባቱ ኅልቀተ ወርቅ ማኅተም እንዲመካ፥ የንጉሠ ነገሥት ክርስቶስ ልጆች የምንለይበት የምንመካበት ትእምርተ ድኂን።
🔹✔ የጨለማውን አበጋዞችን ድቅድቅ የምንገፍበት
ጸዳለ ኩሉ ዓለም።
🔹🔹🔹✔ የሚወረወረውን ፍላጻ የምንሰብርበት ልብሰ ሃይማኖት ጥሩር።
✟✟✟✔ጦር ከነቀነቀ ጋሻ ከታጠቀ ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ የምንመክትበት ንዋየ ሐቅል።
🔷✅✅✅ ቢዋጉ ማሸነፊያ ቢሸሹ መጠጊያ ጸወነ ሥጋ ወነፍስ ወልታ ጽድቅ።
መስቀል መልዕልተ ለኩሉ ነገር

Forwarded from መሠረተ አሚን - Meserete Amin (Aba G.kidan)
❖❖❖❖ መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
አንተ ሰው እስኪ ልጠይቅህ? :ጌታ የተሰቀለ ዕለት ዕርጥብ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ ሲሄድ ብትኖር ኖሮ ታግዘው ነበርን ? ወይስ አብረህ ትገፋው ነበር ? ወይስ በርቀት ሆነህ ይገባዋል እያልክ ትደነፋ ነበር ? ወይስ አላውቀውም ብለህ ትክድ ነበር ? ወይስ ጥለኸው ትጠፋ ነበር ? ወይስ በልብህ አምነህ አብረህ ከጠላቶቹ ጋር ታመዋለህ ? ወይስ ራቅ ብለህ ትከተለው ይሆን ? እስኪ ዛሬ የደመራ ነጭ ልብስህን እንደለበስህ ይህንን አስብና ምን እንደምታደርግ እርግጡን ለልብህና ለራሱ ለመድኀኔዓለም ንገረው !
አይ ጌታዬ ተሸክሞ እየደከመማ አግዘዋለሁ እንጅ አልክደውም ትለኝ ይሆናል ። እኔም እንዲህ እልሃለሁ ።
አንተ ሰው ! አሕዛብ ቤቱን በማቃጠል ፥ ልጆቹን በማረድ እያሳደዱት በአንተ ዘንድ በልጅነት ያድር ዘንድ በመጣ ጊዜ ሰውነትህን በዝሙትና በበደል አርክሰህ በንስሐ ሳትታጠብ ከቆየኸው ማደሪያ እየነሣኸው አይደለምን ? አብረህ እየገፋኸው አይደለምን ? እርሱ ስለአንተ ርጥብ መስቀል ተሸክሞ አንተ የወንድም እኅቶችህን አመል የማትታገሥ ከሆነ ምኑን መስቀሉን አገዝኸው ? እርሱ ለጠላቶቹ መስቀል ከተሸከመ የእኅት ወንድሞቻችን ሸክም የማንሸከም እኛ ምን እዳ ይጠብቀን ይሆን ? ወዳጄ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን ሲል የተሸከመውን መስቀል አግዘዋለሁ ካልክ አንተ ለምን ለሚስትህ ብለህ ድካሟን አትሸከምም ? እጠቀም የማይል ጌታ የአይሁድን መስቀል ከተሸከመ መንግሥተ ሰማያት ትወርስ ዘንድ ለምን መከራ አትቀበልም ?
ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ! አንዳንዶቻችን በልብ አምነን በአፍ ዝም ያልን ነን ! አንዳንዶቻችን ገብቶንም ሳይገባንም መስቀሉን ከሚገፉ ጋር ተባባሪዎች ነን ! አንዳንዶቻችን ራቅ ብለን እሰይ ይበላቸው እያልን በአባቶቻችን ውርደት የምንሳለቅ ነን ! አንዳንዷቻችን ደግሞ ቀርቦ ከመቃጠል ራቅ ብሎ መጠቅለል እያልን ከባድ ነገር መስማትን የማንወድ ሲነሣ ንገሩኝ አይነት ሰዎች ነን ! አንዳንዶቻችን እንደ ቀንድ አውጣ ደስታ ሲሆን ብቅ መከራ ሲመጣ በኑሯችን ሸማ ጥልቅ የምንል ነን ! አንዳንዶቻችን ጭራሽ ምን እየሆነ እያለ እንኳ የማይገባን አመት በዓል ሲመጣ ለምግብ ብቻ አለሁ ባዮች ጥለን የጠፋን የበረከተ ኅብስትና የድግሥ ክርስቲያኖች እንጅ ቀራንዮ ላይ የለንም ! የመጥፋታችን ምልክቱማ የመስቀል ዕለት መዝፈናችን
አይደል !
መስቀሉን እሸከማለሁ የሚል የመድኃኔ ዓለም ወዳጅ ?????????????????????????
መልስ ፦ እኔ አለሁ የመድኃኔዓለም ወዳጅ ኃይል ባገኝ የቤተክርስቲያናችን ፈተናዎች ለማሳለፍ እተጋለሁ ። ባይቻለኝ ግን የራሴን ፦
1. የራሴን ሥጋዊ የፍትወት መከራ መስቀል እሸከማለሁ እንጅ የፈቃዴ ባርያ አልሆንም ።
2. ዘወትር የዕለት ዳዊትና ውዳሴ ማርያም በመጸለይ ያለ ማቋረጥ አምላኬን እመገባለሁ ።
3. በሠራኋቸው በደሎች ከነገ ጀምሮ ለንስሐ አባቴ እናዘዛለሁ ።
4. ጌታዬ በመስቀል የተሰቀለው ለእኔ ምግብ ሆኖ ሊፈተት ፥ መጠጥ ሆኖ ሊቀዳ ነውና ለእኔ ሲል መሞቱን ቅዱሥ ሥጋውን በመቀበል እመሠክራለሁ ።
5. ምንም ቢሆን ጌታዬ እኔን ፍለጋ ከሰማይ ወደ ምድር ወርዷልና እኔም እርሱን ፍለጋ ቤተክርስቲያን ኪዳን ሳላስደርስ አልውልም ።
6. እርሱ የእኔን ደዌ በመስቀል እንደተሸከመ እኔም የባልንጀራዬን ድካም ታግሼ ማንንም ሆነ ማንን ይቅር እላለሁ ።
8. በመከራዬም ሆነ በደስታየ ከመስቀሉ ሥር እገኛለሁ እንጅ ራበኝ ብየም አልጠፋም ጠገብሁ ብየም አልርቅም !
9. ቢቻለኝ የቤተክርስቲያንን ችግር እፈታለሁ መስቀሉን እሸከማለሁ እንጅ አባቶችን አልተችም ከገፊዎች ጋር አልቆምም ።
10. ጊዜየን በማይረባና ርብሐ ቢስ በሆነ አላባክንም ፤ በየጊዜው ና በየሰዓቱ ስለቤተክርስቲያን ባልናገር እንኳ ቢያን ጆሮየ ለቤተክርስቲያን የተከፈተ አደርጋለሁ ።
11. ሥጋውን ደሙን በለጋሥነት ሀሰጠኝ ጌታ ከጠፊ ገንዘቤ ከአሥር አንዱን በታማኝነት አወጣለሁ ።
12. ለተጠራሁበት የጸጋ ሥጦታ እታመናለሁ ። ድንግል የሆነ ለድንግልና ፣ ባለትዳር እንደሁ ለትዳር ፥ ዲያቆን እንደሁ ለዲቁና ፤ መነኩሴ እንደሁ ለምንኩስና ፣ ጳጳስ እንደሁ ለጵጵስና ፥ ሊቀ ጳጳስ እንደሁ ለሊቀጵጵስና ፥ ለመታመን በቆመበት ቁርጥ ሕሊና የሚከፈትበትን ሁለንተናዊ የአጋንንት ጦርነት የሚታገሥ እርሱ ጌታን በቀራንዮ ያገዘው የቀራንዮ ሰው ነው ! ወዳጄ ሆይ ባለህባት የመንፈሳዊነት ደረጃ የምትገጥምህ መሰናክል ያቺ ለአንተ መስቀልህ ። ከመልካምነትህ ያልተናወጽህ እንደሆነ በእውነት ግርማ አይሁድን ታግሠህ ከክርስቶስ ጋር የቆምክ የመስቀሉ ሰው ነህ !
አባ ገብረ ኪዳን
መስከረም ፲፮ -፳፻፲፫ ዓም

በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
✝️ ከመቅሰፍት የምንድነው በምን ነው ❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ክፍል ፪(2)
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ሊንክ👉
#SUBSCRIBE ያድርጉ ።
#SHARE ያድርጉ ።
https://youtu.be/mTuBsRJy6eA
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
✝️ ከመቅሰፍት የምንድነው በምን ነው ❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ክፍል ፪(2)
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ሊንክ👉
#SUBSCRIBE ያድርጉ ።
#SHARE ያድርጉ ።
https://youtu.be/mTuBsRJy6eA
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
YouTube
ቅዱስ ቁርባን መቼ ? የት ? እንዴት ? ለምን ? በማን ? ክፍል 2 በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ #Subscribe_Gubae_tezekro_G
በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
✝️ ከመቅሰፍት የምንድነው በምን ነው ❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
#SUBSCRIBE ያድርጉ ።
#SHARE ያድርጉ ።
✝️ ከመቅሰፍት የምንድነው በምን ነው ❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
#SUBSCRIBE ያድርጉ ።
#SHARE ያድርጉ ።
❤1
Audio
✝ #በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
✝ከመቅሰፍትየምንድነው በምንድነው❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ክፍል ፪(2)
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
👉የጉባኤ ተዘክሮን የዩቲዩብ ቻናል
https://youtu.be/mTuBsRJy6eA
✝ከመቅሰፍትየምንድነው በምንድነው❓
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ክፍል ፪(2)
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
👉የጉባኤ ተዘክሮን የዩቲዩብ ቻናል
https://youtu.be/mTuBsRJy6eA
Audio
✝ #የደናግል_መመኪያ
✝በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
✝🌻 መስከረም 21/2013
በዩቱብ ለመከታተል👉
https://youtu.be/TRsEcjnrisI
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
✝በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
✝🌻 መስከረም 21/2013
በዩቱብ ለመከታተል👉
https://youtu.be/TRsEcjnrisI
✝የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።✝
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
👉 ውድ የጉባኤ_ተዘክሮ አባላት በሙሉ በተማርነው ትምህርት እንዲሁም በእለት እለት ህይወታችን ጥያቄ የሆኑባችሁን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከታች በተጠቀሰው አድራሻችን ማድረስ ትችላላችሁ ጥያቄዎቻችሁን ለሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በማቅረብ መልስ እንዲሰጡበት ለማድረግ እንሞክራለን ።
ኢሜል አድራሻ :- samuelkifles75@gmail.com
የቴሌግራም አድራሻ :- @AbaGebrekidanGubaetezekro
ማድረስ ትችላላችሁ ።
የዩቲዩብ ቻናላችንን #ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ !
#ሼር በማድረግም ለሌሎች ያድርሱ ።
Please #Share and #Subscribe
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቲዩብ ሊንክ https://youtu.be/QukwBrTSqdY

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ።
ዘመን ማለት ወራት አመት የአመታት ውሕደት ማለት ነው።ጽጌ ማለትም አበባ ማለት ነው።
ማርያም ማለትም፦
ሀ)ፍጽምት ሲሆን በነፍስ በስጋዋ ምንም ነውር የሌለባት ሁለንተናዋ ያማረ አቻ የሌላት መልካም ማለት ነው።=ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ"እንዳለ።መኃ፩፥፲፭
ለ)ጸጋ ሀብት ስጦታ ማለት ነው።ቀድማ መካን ለነበሩ እናት አባቷ ተስጥታለች። በፍጻሜ ግን"በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው"ተብሎ እንደተጻፈ ከመስቀሉ ላይ ሆኖ የሠጠን ከመስቀሉ ስር የተቀበልናት የሁላችን ፍጽምት ጸጋችን ሀብታችን በረከታችን ናትና።ያዕ፩፥፲፯፣ዮሐ፲፱፥፳፮
ሐ)መንግስተ ሰማያት መርታ የምታገባ ማለት ነው።"ክርስቶስ በሥጋ መጣ "ተብሎ እንደጻፈ ሮሜ፱፥፭፤መጀመሪያ እግዚአብሔር ወደ ፍጥረት ሲመጣ የእርሷን ሥጋ ለብሶ ነው የተገለጠው።ወደፊት ወደልጇ እየመራች የምታደርሰን ዐይናችን እርሷ ናትና።
መ)ልዕልት ማለት ነው።ከፈጣሪ በታች እርሷን የሚመስል እንደርሷ ማንም የለም ።ኪሩቤል የጌታን ዙፋን ይሸከማሉ፤ሱራ ፌል ያጥናሉ መላእክት ሁሉ ያመሰግናሉ ፈቃዱን ይፈጽማሉ።ይህ ሁሉ ክብር ቢኖ ራቸውም ጌታን መውለድ የተሠጣት ግን እመቤታችን ማርያም ናት።
ሠ)የአማንያን አንድነት ሕብረት ማለት ነው።ሃይማኖት ያልነበራቸው አረማውያን ሃይማኖት ያላቸው እንዲሁም የሰማይ መላእክት አንድ መሆን የቻልነው እመቤታ ችን ጌታን በመውለዷ ነውና።ሉቃ፪ ፥፲፩
ረ) የእግዚአብሔርና የሰው መልእክተኛ ማለት ነው። ለእግዚአብሔር ከእርሷ የቀረበ ባለሟል የለውም።ምክንያቱም እርሷ በጌታ ፊት የእናትነት ስልጣን ነውና ያላት።"በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና"እንዳለ ቅዱስ ገብርኤል። ሉቃ፩፥፴ እኛም ከእርሷ በላይ ሌላ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን የለንም። የሰውን ጭንቀት ወደ ጌታ የጌታን በረከት ደግሞ ወደ ሰው የማውረድና የማሳረግ ኃይል ያለው ከእርሷ የቀረበ የለምና።
ሰ)የእስራኤል ቤትሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው።እስራኤል የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚል ትርጉም አለው።በዚሕ መሠረት ማርያም ማለት ክርስቲያኖች ደስ ይበላችሁ ማለት ነው።ለምን ብንል የሁላችን ደስታ ጌታን ወልዳልናችና።"በጌታ ደስ ይበላችሁ" እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ።ፊል፪፥፬
ቀ)የሁሉ ንግስት ወይም እመቤት ማለት ነው።እንዴት ብንል የዘለዓለማዊ ንጉሥ የእግዚአብሔር እናቱ መንበሩ ናትና። የሥላሴ መንበር ከመላእክት በላይ ነው። ድንግል ማርያም ደግሞ ጌታን ከመንበር ነት አልፎ ወልደዋለች አጥብተዋለች አሳድገዋለች አዝዘዋለች።ስለዚህ የመላእክትም የሰው ልጆችም ንግስት ናት።ራእ፬፥፪
በ)እናት ለጅዋን ወልዳ መግባ ጠብቃ ሲታመም አሳክማ ታሳድጋለች።ድንግል ማርያም ግን መንፈሳዊ እናታችን ናትና የልጅዋን ሥጋና ደም መግባ፤በእውነ
ተኛው እረኛ በልጇ ጠብቃ፤በነፍሳችን መድኀኒት በልጇ ፈውሳ ታሳድገናለች። ምድራዊ እናታችን መጨረሻ ላይ ምድራዊ ሀብት ታወርሰናለች።ሰማያዊት እናታችን ድንግል ማርያም ግን ሰማያዊ መንግስሥት ታወርሰናለች። "ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል"መባሉ ስለዚህ ነው።መዝ፹፮፥፭
ተ)ሠረገላ ጸሐይ ወይም የጸሐይ መመላለሻ ማለት ነው።ጸሐይ በሰሌዳዋ ላይ እንደምታበራ እውነተኛው የጽድቅ ጸሐይ ክርስቶስ በእርሷ ተገልጦ ለዓለሙ አብርቷልና።"ለዓለም ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሐን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር"ዮሐ፩፥፱ ይሕ የሕይወት ብርሐን መድኀኒታችን ክርስቶስ ነው።"እኔ የዓለም ብርሐን ነኝ"ብሏልና።ዮሐ፰፥፲፪ በድቅድቅ ጨለማ የሚኖረው ሕዝብ ያየውን የሕይ ወት ብርሐን ያወጣችልን የድኅነት ምስራቅ በራችን የሃይማኖት መለኮታዊት ሰሌዳ እመቤታችን ናትና እመ ብርሀን እንላታለን!እርሷን ተከትለን በብርሐን ሀገር ለመኖር ያብቃን!አሜን!
ቀጣዩን ክፍል እንደ ሥላሴ ፈቃድ በተከታታይ እናያቸዋለን ይቆየን።
👉 በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
👉 @mesereteamin

👍1
Audio
በመጋቤ_ብሉይ_ወሐዲስ_አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
✝ #ቅዱስ_ቁርባን
👉 #ክፍል ፫(3)
✝መቼ እንቁረብ❓
✝የት እንቁረብ❓
✝ እንዴት እንቁረብ❓
✝ ለምን እንቁረብ❓
✝በማን እንቁረብ❓
👉የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ቻናል
https://youtu.be/wavsurEsCmc
በቴሌግራም👉
✝የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት ጉባኤ ተዘክሮ ዘጎንደር✝
<<የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ::>>
https://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro

ሁላችሁም የቻናላችን እና የግሩፕ አባላት ሌሎች ሰዎችን በማስገባት የእግዚአብሔርን ቃል ታዳርሱ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ትጠየቃላችሁ ።
@AbaGebrekidangubaetezekro

✝ ወደ እኔ ብረሪ ✝
በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።
ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርር በደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።
ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን ያኀያላን ጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢችኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይን ያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።
የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።
ነውር የሌለብሽ መልካም ጸጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።
👉በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን
@mesereteamin