የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.48K subscribers
173 photos
7 videos
861 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
🛑የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት / የብሉይ ኪዳን ጉባኤ ተዘክሮ ማውጫ በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ

ክፍል ፩ (1)
👉 https://youtu.be/efDLWFXIYOE

ክፍል ፪ (2)
👉 https://youtu.be/scQ_bVF9oYw

ክፍል ፫ (3)
👉 https://youtu.be/KgR1QA7Wgw4

ክፍል ፬ (4)
👉 https://youtu.be/cnHMS-jbkQ4

ክፍል ፭ (5)
👉 https://youtu.be/YK5I56RCTlM

ክፍል ፮ (6)
👉 https://youtu.be/HiVB3RNas8k

ክፍል ፯ (7)
👉 https://youtu.be/nNU7GPQ2e88

ክፍል ፰ (8)
👉 https://youtu.be/3HYhNEMgzSM

ክፍል ፱ (9)
👉 https://youtu.be/_dRURfr_1xg

ክፍል ፲ (10)
👉https://youtu.be/M1DOVXOMt6M

ክፍል ፲፩ (11)
👉 https://youtu.be/rV1rk_E-FOs

ክፍል ፲፪ (12)
👉 https://youtu.be/L7-s2Q9h1UU

ክፍል ፲፫ (13)
👉 https://youtu.be/DS-72Aa-020

ክፍል ፲፬ (14)
👉 https://youtu.be/sNRH6GUKCZg

ክፍል ፲፭ (15)
👉 https://youtu.be/FazHjzw18Mo

ክፍል ፲፮ (16)
👉 https://youtu.be/NZQF6skQPMg

ክፍል ፲፯ (17)
👉 https://youtu.be/YYGRhNqxPGg

ክፍል ፲፰ (18)
👉 https://youtu.be/9nnhoSXLcUo

ክፍል ፲፱ (19)
👉 https://youtu.be/kTlz2FbD1ig

ክፍል ፳ (20)
👉 https://youtu.be/vlmVDevWgA8

ክፍል ፳፩ (21)
👉 https://youtu.be/fxiSgmzal2s

ክፍል ፳፪ (22)
👉 https://youtu.be/Mqy4q9XAGaI

ክፍል ፳፫ (23)
👉 https://youtu.be/6ebb1H0EKCw

ክፍል ፳፬ (24)
👉 https://youtu.be/-sdJoGNL6N8

ክፍል ፳፭ (25)
👉 https://youtu.be/x4XrM81qvvA

ክፍል ፳፮ (26)
👉 https://youtu.be/D1SKByX8ipg

ክፍል ፳፯ (27)
👉 https://youtu.be/QQhVLrV-gF4

ክፍል ፳፰ (28)
👉 https://youtu.be/DXqeBaOPxGI

ክፍል ፳፱ (29)
👉 https://youtu.be/ksdlTp8lp6k
እግዚአብሔር የረሳን ለምን ይመስለናል?
1. እኛ ስለምንረሳው
የመከራ ጽናት የዘመን ብዛት እግዚአብሔር ረስቶኛል ብቻ ሳይሆን (ሎቱ ስብሐት) እግዚአብሔር የለምም ያስብላል። የሰው ልጅ መከራው ጽኑ በሆነ ጊዜ፣ ዘመን በራቀበት ጊዜ፣ ለጥያቄው መልስ ባጣ ጊዜ በእነዚህ በሦስቱ በሃይማኖት እንቅፋት ይገጥመዋል። ስለዚህ እግዚአብሔር ረስቶኛል፣ አይወደኝም ይልና ቀቢጸ ተስፋ ላይ ሲደርስ ደግሞ እግዚአብሔር ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ ማለት ይጀምራል። በመጨረሻም የለም ብሎ ይክዳል።
ሰይጣን ሰውን ወደ ምንፍቅና ወደ ክህደት የሚወስድባቸው 3ቱን መንገዶች መጠንቀቅ ይገባል። ይህንን ይበልጥ ለመረዳትም የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ሀሳቦችን እንመልከት:-
👉ሀ. "ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም? ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተን አላወቅህም?" (ኢሳ58÷3)
እዚህ ላይ ጹመው ለጥያቄያቸው ምላሽ በማጣታቸው እግዚአብሔርን አልተመለከትከንም፣ አላወቅኸንም እስከማለት ደርሰው ነበር። "የእግዚአብሔር ዓይኖች ምን ሆነው አንመለከቱም?፣ አይወሰኑ ምሉዓን፣ አይሞቱ ሕያዋን፣ አያዳሉ ጻድቃን ናቸው። ታዲያ ለምን አልተመለከትከንም አሉ?" ብንል መልሱ "ጥያቄያቸው ባለመመለሱ እግዚአብሔር የተዋቸው የገፋቸው የረሳቸው መስሏቸዋል" የሚል ይሆናል።
የፈለጉትን በማጣታቸው በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት እግዚአብሔር የሌለ እየመሰላቸው ወዲያ ወዲህ የሚቅበዘበዙ ወገኖች በዚህ ዘመንም አይታጡም። ግን እግዚአብሔር አላይ ብሎ ሳይሆን እኛ አንታይም አትየን ብለነው ነው። "ገዳም ሄድኩ፣ ንስሐ ገባሁ፣ እጸልያለሁ፣ እጦማለሁ፣ በቅዱሳን አምናለሁ፣ እቆርባለሁ ነገር ግን እስከዛሬ ከነበርኩበት ነኝ ምን ይሻለኛል?" የሚሉ ብዙዎች ናቸው። መልሱን ለእነዚህ ጦመኞች የመለሰውን እንስማ!
"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትቾላለችን? አዎ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም" ይላል (ኢሳ 49÷15)። እናት 9 ወር ፀንሳ፣ ኸደምዋ ተከፍሎ፣ በምጥ በፃዕር በጭንቅ የወለደችውን፣ 3 ዓመት ያጠባችውን፣ ሁሉን ታግሳ በንጽሕና ያሳደገችውን ልጇን ትረሳለችን? አትረሳም። ዳሩ ግን ቢያንስ ሙቶ እንኳን አልቅሳ አልቅሳ ስታንቀላፋ በዕለቱም ቢሆን ትረሳለች። እግዚአብሔር ግን ይህ ሁሉ በባሕርዩ የለበትምና አይረሳም። "እንግዲያውስ ስለምን አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

ጥያቄ:- ስለምን ጦምን? አንተም አልተመለከትከንም ሰውነታችንንስ ስለምን አዋረድን? አንተም አላወቅኸንም?

መልስ.......
ይቀጥላል
ከጸያሔ ፍኖት (በአባ ገብረ ኪዳን) ከገጽ 68-69 የተወሰደ
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
" እግዚአብሔር እሺ በሉት ጋኔንን እምቢ በሉት" ያዕ 4፥7

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ/Aba Gebrekidan new sbket 2021

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉 https://youtu.be/h_m4qi53wp0

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
"ያዳነኝ ተሸከም ብሎኛል" 🛑እጅግ ወቅታዊ እና 🛑ድንቅ ትምህርት በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ/Aba Gebrekidan new sbket 2021

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉 https://youtu.be/bKYTyzksejo

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
በስልክ ንስሐ መግባት ይቻላልን?🛑"ቀኖና እና ሱታፌ ክርስቶስ" ወቅታዊ ትምህርት

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/ayPTHt4gYfs


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
"ልባቸውም ከንቱ ነው፥ጉሮሮአቸውም እንደተከፈተ መቃብር ነው" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት ክፍል 30

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/qjpBqj9LWdg


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
"አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ በመዓትህም አትገስጸኝ"
የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት #ክፍል_31

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/qGLtoBwFNbs


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
ወደ እኔ ብረሪ

በርግብ ክንፎችሽ ከአውሬው ስትሸሽ፣
በጸዳል እግሮችሽ ስትንከራተቺ
በበረሃዉ ጉያ ስትመላለሽ
ከአህያይቱ ጀርባ ጫማ ተሸክሜ
ምነው በነበርኩኝ እኔ እንደ ሰሎሜ።

ከሄሮድስ ዱላ ከሳለው ጋሻ ጦር
ፈጥነሽ እንደበረርሽ ልጅሽን ለመሰወር
እኔም እንድሰደድ ከኃጢአቴ መንደር
ለጽድቅ እንድፋጠን በሰማይ እንድበር
ደግፊኝ እመ አምላክ ክንፌ እንዳይሰበር።
የቀላያት ጌታ ውኃ እንደተጠማ
በነፋስ የሚበርር በደመናው ማማ
ውኃ ስትለምኚ ጫማ እንደተቀማ
እኔን ድርቅ ያርገኝ ከኃጢአት ልጠማ
ደረቄን እንዳልቀር ከፍሬው አውድማ።

ምድርንም ያጸና ሰማይን የታታ
ግሩም እምግሩማን የኀያላን ጌታ
ለሰው ፍቅር ብሎ ብዙ ሲንገላታ
በዉኃ እንዳጠብሽው ኃይሉ እንዲበረታ
በእንባሽ እጠቢኝ ኃጢአቴ በርትቶ የተረታሁ ለታ።
ጸሐይን ያዘልሽው ደመና መፍጠኒት
የወርቅ ሐመልማል ርግብየ ኅሪት
አክናፍኪ መስቀል የሕይወት መሠረት
ሄሮድስ ሳይውጠኝ ሳልቀሰፍ በሞት፤ ወደ እኔ ብረሪ አዝለሽልኝ ምሕረት።

የግብጽን በረሃ የጎበኘሻቸው
አድባረ አግአዚትን ዞረሽ ያየሻቸው
የሕይወትን ውኃ ያዘነብሽላቸው
ሐሩሩ ሕይወቴን ፍጹሙን በረሀ
ታስትይዮ ስቴ እሴፎ አሜሃ።

ነውር የሌለብሽ መልካም ጽጌረዳ
በመንከራተትሽ ውስተ ምድረበዳ
ሸክም ቀለለልን ከፈልሽልን እዳ
በምጽአቱ ጌዜ ፍቁርሽ እንግዳ
ቅርጫፍሽ ልሁን አይብላኝ አንጋዳ።

👉በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ

🛑የቴሌግራም ሊንክ @AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዩቲዩብ ሊንክ
https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑ለጓደኛዎ ያጋሩ/ ቻናላችንን ያስፋፉ
ሰላም ለሁላችን። ከዚህ በፊት በ #ዩቲዩብ እና በ #ቴሌግራም የምታውቁት የ "ዕንቈ ሥላሴ tube" አሁን ደግሞ በ #ዋትሳፕ መጥቶላችኋልና ለወዳጅ ዘመዶት ሊንኩን በማጋራት ትምህርተ ወንጌልን በማስፋፋት የነፍስን ምግብ ይመገቡ ይመግቡ !
🛑የዩቲዩብ ሊንክ 👉https://youtube.com/channel/UCUC5SLeTiPLbN8iA4E3bBgw
🛑የቴሌግራም ሊንክ 👉@AbaGebrekidangubaetezekro
🛑የዋትሳፕ ሊንክ 👉https://chat.whatsapp.com/G5sQlltWryQ2pPkU9RDeVt