የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.48K subscribers
173 photos
7 videos
861 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
"እኔ ግን በምህረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ትርጓሜ ክፍል 28 በመጋቤ ብሉይ…
👉ሰለ ሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ውግዘት የተነገረውን እንስማ ከምንወዛገብ!

<<"እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደቤትህ እገባለሁ::">>

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የብሉይ ኪዳን ጉባኤ ተዘክሮ::

የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት::


👉 ክፍል 28

👉በዩቱብ ለምትከታተሉ
https://youtu.be/DXqeBaOPxGI

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
ቅዱስ እግዚአብሔር

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ👉https://youtu.be/OhpMg9REPkA


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
🛑ቅዱስ ሲኖዶስ ሁልጊዜ ትክክል ነውን ? 🛑ስለ አለቃ አያሌው ውግዘት ! 🛑ምክረ አበው በታላላቅ…
<<"ቅዱስ ሲኖዶስ ሁል ጊዜ ትክክል ነው">>
ስለ ሊቁ አባት አለቃ አያሌው ውግዘት በተመለከተ

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


👉በዩቱብ ለምትከታተሉ
https://youtu.be/_i7doP3oc1w
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
🛑"ወደ ቅኔ አትሒዱ" እጅግ ድንቅ ስብከት በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረኪዳን ግርማ/🛑Must…
<< እንግዲህ ወደ ቅኔ አትሂዱ::>>

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


👉በዩቱብ ለምትከታተሉ
https://youtu.be/Dg73KBGY_yw



የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
💠💠💠💠ጾምሰ ሕገ ፍቅር ይእቲ💠💠

✟ጾም የፍቅር ሕግ ናት።

ጾም ማለት ሐይው ከመ መላእክት ፦ የመላእክት ኑሮ ናት። ቅዱሳን መላእክት ከዚህ ዓለም ምንም ምን የሚሹት ገር የላቸውም። ለምን ቢሉ ለልብሳቸው ብርሃኑን ለምግባቸው ምስጋናውን ገንዘብ አድርገው ይኖራሉና። ስለዚህም ከዚህ ዓለም አንዳች አያስፈልጋቸውሞ። አይርባቸውም ገጸ እግዚአብሔርን በማየት ይጠግባሉና። አይጠሙም ውኂዘ ስብሐቱን ያንቆረቁራሉና። አይራቡም ሕብስተ አኮቴቱን ይመገባሉና። አይራቆቱም በጽርየተ ክብር ሸልሟቸዋልና። አይጨልምባቸውም መብረቀ መለኮቱ ያበራላቸዋልና። አይደክሙም ኃይለ መዊዖቱን ታጥቀዋልና። አይሞቱም ሠራዊተ ሕያው እግዚአብሔር ናቸውና።

ይህን ሕይወት እኛ በክርስቶስ የተዋጀን ክርስቲያኖት በትንሣኤ ዘጉባኤ የምንቀላቀለው ሲሆን እስከዚያው ድረስ ግን በጾምና በቅዳሴ በምናኔ በንጽሕና በአረቦንነት እንለማመዳለን። "አስመ ሐይው ከመ መላእክት ይሬስዮ ለብእሲ ከመ ኢይፍቅድ ምንተኒ በዲበ ምድር - ሰው የመላእክትን ኑሮ ልኑር ባለ ጊዜ ከዓለም ምንም ምን አይሻም"። እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
ስለዚህ አዘወትሮ የሚበላ እንስሳዊት ኑሮን እየተለማመደ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን እየካደ ነው ማለት ነው። ለምን ቢሉ መብላት የእንስሳት ነውና፤ እንስሳትም የትንሣኤ ተስፋ የላቸውምና። ስለዚህ ወዳጄ መላክ መሆን ብትሻ ጹም እንስሳ መሆን ብትሻ ብላ! ተስፋ የለስሽ መሆን ከፈለግህ ብላ፤ ባለትስፋ መሆን ብትወድ ጹም።

ከቤተክርስቲያን አባቶች አንዱም ወግሪስ " በቀን ሦስት ጊዜ የሚበላ እንስሳ ነው፤ ሁለት ጊዜ የሚበላ ሰው ነው፣ አንድ ጊዜ የሚበላ ደግሞ መልአክ ነው" ብሏል።

ሁለተኛ ጾም ምንድን ናት ብትለኝ ሕገ የፍቅር ናት። አዳም በለስን የተከለከለው ከበለሷ ይልቅ እግዚአብሔርን መውደዱ እንዲታወቅ እንጅ ሌላ ምንድን ነው? በለሷን ሲበሏት ግን በፍቅረ እግዚአብሔርን አፈረሱ። ፍቅርን ሲያፈርሱም አካላቸው መፍረስ (ሞት) ተፈረደባቸው ይላል ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ።

ወዳጇቼ አስተዋላችሁን? በለሷን መብላት ፍቅርን ማፍረስ እንደሆነ ፥ ፍቅርን ማፍረስም ሞትን እንዳመጣ! እንዲሁ ጾምን ማፍረስ ለእግዚአብሔር ያለንን የፍቅር ማፍረስ ነው። ጾምን ማፍረስም የሞት ምንጭ ነው። ስለዚህ በሀገራችን ሞት እየነገሠ ያለው
ጾምንና ፍቅርን እያፈረስ እንደሆነ እናስተውል።

በጾም የፍቅር ሕግ ነው ማለትስ ምን ማለት ነው?

አንደኛው የፍቅር ሕግ እግዚአብሔር እኛን ወዶ ሁሉን ትቶ እንደወረደ ( ከክብር መንግሥቱ ሳይጎድል ዕብራውያን ፲፫፥፰) እኛም የምንወደውን ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ብለን ስንተው መሥዋዕት ፍቅር ይባላል። እግዚአብሔርን ለመውደድ የግድ ትልቅ መሆን አይጠበቅም። ባለንባት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ያለችንና የምንወዳትን ትንሽ ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ብለን ቆርጠን ስንተዋት ባለችን ምንንት ሀብት እግዚአብሔርን መውደዳችን የታወቀ ተረዳ ማለት ነው።

እግዚአብሔር ከእንቅልፋችሁ ቀንሳችሁ ጸሎዩ፥ ከምግባችሁ ተለይታችሁ ጹም፥ ከገንዘባችሁ ቀንሳችሁ ስጡ የሚለን በእኛ መሰቃየት ደስ ስለሚለው አይደለም። ይልቁንም ያችን ነገር መሥዋዕት አድርጎ ስለሚቀበልልንና ለእርሱ ያለንን የመታመንና የፍቅር ሕግ ስለምንገልጥ ነው እንጅ።

አያችሁ ወዳጆቼ ! ጾም እንቀንስ ባልን ጊዜ ለእግዚአብሔር ያለንን የፍቅር እንቀንስ ማለታችን ነው። ወይም ከእግዚአብሔር ፍቅር ይልቅ የመብል ፍቅር ይበልጥብናል ማለታችን ነዋ!

ሁልጊዜም ማድረግ ቢገባንም አብዝን በጾም ወቅት ግን፦ ጉሯችን በጽምዕ ፥ ከርሣችንን በረሃብ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሕዋሳታችን የሚወዱትን ኃጢአት እግዚአብሔርን ስለመውደድ መተው አለባቸው። የምንወደውን መብልና መጠጥ እግዚአብሔርን ስለመውደድ እንደተከለከልን የምንወዳቸውን ኃጣውእ የሠራናቸው በመናዘዝ ፥ ያልሠራናቸውን በመታቀብ ከተውናቸው በትክክል ጾማችን ሕገ ፍቅር ሆነችልን ማለት ነው።

ሁለተኛው ጾምን ሕገ ፍቅር ያሰኘው ምን ነው ቢሉ በአንድ ጊዜ ሁለት የድኅነት መሠረቶችን መፈጸም ነው። ስለ እግዚአብሔር ብለን ከምግምብ እንደተከለከልን ስለ በፍቅረ በጽ ደግሞ በመጾማችን ያልተመገብናቸውን ምግቻችን ለወንድሞቻችን ለእኅቶቻን መስጠት ነው። የጾሙን ሕግ ስናከብር ፍቅረ እግዚአብሔርን እንፈጽማለን። ከምንበላው ቆርሰን ስናጎርስ፤ ከምንለብሰው ቀደን ስናለብስ ደግሞ ፍቅረ ቢጽን ፈጸምን ማለት ነው። ስለዚህ የብሉያት የሐዲሳት ሕገጋት ምሰሶዎች የሚባሉትን ፍቅረ ቢጽና ፍቅረ እግዚአብሔርን በጾም ስለምንፈጽባት ጾም ሕገ ፍቅር ተባለች።
... ይቀጥላል.... ይቆየን!
ጹመን እንድንድን ምክንያት ሁና ጌታን የወለደችልንን እመቤታችንን መርጦ ከእርስዋ በሥጋ ተገልጦ ጹሞ ያዳነን ቡሩክ መድኃኔአለም ይመስገን!

አባ ገብረ ኪዳን ገብራ ለኪዳነ ምሕረት።
http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
"አቤቱ በጽድቅህ ምራኝ ስለጠላቶቼም መንገዴን በፊትህ አቅና" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት ክፍል 29…
<<" አቤቱ በጽድቅህ ምራኝ ሰለጠላቶቼም መንገዴን በፊትህ አቅና::">>

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

የብሉይ ኪዳን ጉባኤ ተዘክሮ::

የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ጥናት::


👉 ክፍል 29

👉በዩቱብ ለምትከታተሉ
https://youtu.be/ksdlTp8lp6k

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
የንስሐ እንቅፋቶች እና መፍትሔዎቻቸው

ትምህርተ ንሰሃ ክፍል ፲(10)


መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/uF-d6Jj43WE


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
🛑የቤተክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ "መመለስ ወይስ መደራጀት

ካልተመለሳችሁ ሰይፉን ይመዛል"
እጅግ ድንቅ ትምህርት

መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ
ገብረኪዳን

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/X_lOfMrMQxM


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
Audio
🛑 እጅግ ወቅታዊ እና ድንቅ ስብከት "ሻጮች እና ለዋጮች"ዮሐ 2፥14

በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ/Aba Gebrekidan new sbket 2021

በዩቱብ ለምትከታተሉ
👉https://youtu.be/g2lTRW4-9_8

የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro