የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket
6.47K subscribers
175 photos
7 videos
862 links
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ትምህርቶች
Download Telegram
"ብርሃን ያለባት የወርቅ መቅረዝ የታመነች የሕግ ታቦት ንጽሕት ብርህት የምትሆን ሰማያዊት ጽዮን እመቤታችን በዓሏን ለማክበር እየጮሁ እያደነቅሁ አመሰግናለሁ፡፡ ምድራውያን ጻድቃን ሰማያውያን መላእክት የመያመሰግኗት ከእግዘአብሔር ብቻ በቀር በክብር በገናንነት በደም ግባትና በማማር የሚተካከላት እንደ እሷ የሌለ እግረ ሕሊናዬ በአደባባይዋ በተመላለሰ ጊዜ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ እያልሁ አነባለሁ እተረጉማለሁ በማለት ደስ አለኝ፡፡"
(ድርሳነ ጽዮን ዘሰኑይ)

እንኳን አደረሰን!!!
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket pinned «Watch "መልእክት በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መላክ በባህርዳር ሀገረ ስብከት የአረቱ ጉባኤያት ምስክር ቤት መምህር" on YouTube https://youtu.be/l_Fbj0tia7M»
"እርሱ ከመላእክት ይበልጣል"የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች ማብራሪያ በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ…
#የሐዲስ_ኪዳን_ጉባኤ_ተዘክሮ

#የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች_ ትርጓሜ

#"እርሱ ከመላእክት ይበልጣል::"

👉 #ክፍል(12)


በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን

👉በዩቱብ ለምትከታተሉ!
https://youtu.be/CPKMi4MmsNU

https://youtu.be/V7xmIwb9Aes

👆
ይህ ቻናል ገዳማትን እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት የተከፈተ ስለሆነ ሁላችሁም "Youtube" ተጠቃሚዎች በሙሉ "Subscribe" እና "Share" ታደርጉት ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ትጠየቃላችሁ ።
#subscribe_ያድርጉን
#share_ያድርጉ
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ሊንክ
👉https://youtu.be/DS-72Aa-020

#SUBSCRIBE ማድረግዎን አይርሱ
#SHARE በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ
የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro
12 እርሱ ከመላእከት ይበልጣል
<unknown>
የሐዲስ ኪዳን ጉባኤ ተዘክሮ
ክፍል 12
የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ዕብራውያን ሰዎች ማብራሪያ


እርሱ ከመላእክት ይበልጣል
ዕብ 1÷4
1
Forwarded from መሠረተ አሚን - Meserete Amin
💠💠💠 ሰውና ዝንጀሮ ተዛዝነው በኖሩባት አገር ኢትዮጵያ ዛሬ
ሰው ሰውን የሚያርድባት ሆነች በቃ?!✟✟✟

ጻድቁ ብርሃነ ዓለም ተክለ ሃይማኖት በአካለ ሥጋ በህሉና መንፈስ ደብረ ሊባኖስ ሳሉ ደቀ መዛሙርታቸው ጥቂት ለቁመተ ሥጋ የሚሆኑ ጥራጥሬ ይዘሩ ነበር። በኋላ ዝንጀሮ እየመጣ እየበላ አስቸገራቸው። ሂደው ቢነግሯቸው "ልጆቼ ተዋቸው እኛ ወደ ጫካቸው መጣን እንጅ እኛ አልመጣንባቸው" ብለው ነበር የመለሱላቸው።

ዛሬ ይህንን ሳስብ ሥጋዊ ሆኜ እንባ እያጠረኝ ነው እንጅ አልቅስ አልቅስ ይለኛል። ምነው ለዝንጀሮ በተራራባት ሀገር ሰው በሰው ደም የሚታጠብ ሆነ!

በኋለኛውም በአስራ አራተኛው ክ/ዘመን የነበሩት የንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ ወንድም አቡነ ዮሴፍ ይህንን የምሕረት ሥራ አድርገውታል።

ዛሬ አጽማቸው ባለበት ላስታ በሚገኘው ገደል ውስጥ እጅግ ብዙ ዝንጀሮዎች አሉ። እኔም ባለፈው ዓመት አይቻቸዋለሁ። ከዕለታት ባንዳቸው አንድ ገበሬ ዘር ዘርቶ እያረሰ ሲያለቅስ አቡነ ዮሴፍ አገኙት። ምን ሆነህ ታለቅሳለህ ቢሉት እናቴ ሙታ ሂጄ እንዳልቀብር ዘሩን ዝንጀሮ ሊበላብኝ ሆነ መተኪያ ዘር ደግሞ የለኝም አላቸው። እርሳቸውም ሂድ እኔ እጠብቅልሃለሁ ብለውት ቀብሮ ተመለሰ።

ከዚህ በኋላ አቡነ ዮሴፍ የሀገሩን ሰዎችና ዝንጀሮዎችን ይዘው ሽምግልና ተቀመጡ። እንዲህም አሏቸው።
ገበሬዎችን፦ እናንተ ቀድሙን(ቃርሚያውን) ጨርሳችሁ አታጭዱባቸው ስታጭዱ ጥቂት ለዝንጀሮዎች ተውላቸው። እነርሱም እጅ ነስተው ተቀበሉ።
ዝንጀሮዎችን፦ እናንተም እሸቱንና ክምሩን አትንኩ ሲያጭዱ ከሚተርፍላችሁ በቀር አሏቸው። ዝንጅሮዎችም ለጥ ብለው ሰግደው ትእዛዛቸውን ተቀበሉ። ይኼው ዛሬ ድረስ በዚያ አካባቢ ዝንጀሮ ሳርና ከመከር የቀረውን ይበላል እንጅ ዘር ወይም እሸት፣ ክምር፣ ስጦ አይበላም።

ዛሬ አንዱን ከአንዱ ከመንቆርና ከማናቆር በቀር ሽማግሌም የለም። እንኳንስ ለእንስሳት በሰው ደም ምቾት ሊያመጣ ደም የጠማው ትውልድ በዝቷል። ጠባያቸው የማይገናኝ ዝንጀሮና ሰው በተስማሙባት ሀገር ቋንቋየን አትመስልምና ልቀቅልኝ እያለ ሰው እንደ ጥራጊ የሚደፋባት የስግብግቦች ምድር ሆነች።

አክሱም ያሉ እናቶች አሁን ድረስ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄዱ ለወፎች ጥሬ ይዘው ይሄዳሉ። አጉራ ዘላዩ ትውልድ ደግሞ ወንድሙን እኅቱን የዋሃን ሕጻናትን እያረደ በእነርሱ መቃብር ላይ ቤት ሰርቶ መዝናናት ያምረዋል።

ኢቶዮጵያ እኮ በድርቅ ዘመን ራሳቸውን አቁስለው ከቁስላቸው ትሎች ለወፎች የመገቡ ቅዱሳን የነበሩባት ናት።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንበሳና ነብር እየመገቡ የኖሩባት ቦታ ናት። ምድረ ከብድ።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ አረጋዊ ዘንዶን መሰላል ያደረጉባት ሀገር ናት። ደብረ ዳሞ።

ኢትዮጵያ እኮ እለ አቡነ ሳሙኤል አንበሳን መጓጓዣ ያደረጉባት ሀገር ናት። ዋልድባ።


ኢትዮጵያ እኮ እለ አባ አምደ ሥላሴ እሾህ የወጋውን አንበሳ የሚያወጡባት ሀገር ናት።

ኢትዮጵያ እኮ እለ እምነ ቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ለሰይጣን ምሕረት የለመኑባት ቤተ ሣሕል ናት!
ደብረ ምሕረት
በእውነት ሃይማኖት ይኑረውም አይኑረውም ምሕረት የሌለው ሰው ኢትዮጵያዊ ነኝ አይበል!

🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋
ለውሻ የራራሽ እመ ብርሃን ከውሻ ለከፋን ልጆችሽ ከመሐሪው ልጅሽ ለምኝልን። ለኢትዮጵያም የምሕረት ጠል አውርጅላት!
የምሕረት አሞላክ የሚራራ ልብ ይስጠን!እርሱም ይራራልን!
🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋
አባ ገብረ ኪዳን ነኝ ወልደ ምሕረታ ለቡርክት ማርያም!
ጥቅምት ፬ /፳፲፪ ዓም ስቶክሆልም!
ሁላችሁም የቻናላችን እና የግሩፕ አባላት ሌሎች ሰዎችን በማስገባት የእግዚአብሔርን ቃል ታዳርሱ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። ለጓደኞቻችሁ share አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFLc4S9Wpf2oI1Ji8A
የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ትምህርቶች የሚተላለፉበት Aba Gebrekidan sibket pinned «ሁላችሁም የቻናላችን እና የግሩፕ አባላት ሌሎች ሰዎችን በማስገባት የእግዚአብሔርን ቃል ታዳርሱ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ። ለጓደኞቻችሁ share አድርጉ ። https://t.me/joinchat/AAAAAFLc4S9Wpf2oI1Ji8A»
Forwarded from መሠረተ አሚን - Meserete Amin
"የትዕግስት ጽዋ"
የጦሩን አንደበት የእሳቱን ወላፈን
የመጋዙን ስለት የመንኮራኩሩን
እንዲያ ፋት እንዳልከው ፍጹም በመታመን፡
እኛም እንድንወደው አንተን ተከትለን
የትዕግስትን ጽዋ ለእኛም አቀብለን።

ባለቤቱ እንዳለ ይች ጽዋ ትለፍ
ብርሐኑን ገልጦ ጨለማን ለመግፈፍ
የተጋድሎን ማዕድ ከእርሱ ለመሳተፍ
ፍጹም ደስ እንዳለህ ብዙ ስትገረፍ
ጊዮርጊስ አስታጥቀኝ አብሬህ ልሰለፍ

በብረት ሊፈጩሕ ሊወጉህ በካራ
ወደ እሳት ሲወስዱሕ ደግሰው መከራ
እንደ ሸለሙት ሰው ሠርግ እንደተጠራ
ለምን ነው ደስ ያለህ እንኳን ልትፈራ
ስለምታይ ነዋ የሰማዩን ጌራ!

በጦር አልተወጋሁ ስለት አላገኘኝ
እሳት አልነደደ ሾተል አልጎሰመኝ
ኧረ እኔን ምኑ ነው የሚያነጫንጨኝ?
አክሊለ ሰማዕታት ትርጉሙ እንዲገባኝ
የሰማዩን ምስጢር ለእኔ ሹክ በለኝ።

የመበለቷን አምድ አንተ ስትጠጋው
ሥር እንደሰደደ እንዳለመለምከው
መሶቡን በኅብስት ቶሎ እንደ መላኸው
ደረቁን ሕይወቴን ለፍሬ ክብር አብቃው
ቀዝቃዛውን ልቤን ምውቅ ጽዋ ምላው።

ጽንዓ ሰማዕታትን ያድለን !በሰማዕትነት ዘመን ሰማዕት ከጠፋ የቤተክርስቲያን ሕመሟ ያን ጊዜ ነው።
"በረከትህ በህዝብህ ላይ ነው" የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ትርጓሜ በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን…
<unknown>
መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳን

#የብሉይ_ኪዳን_ጉባኤ_ተዘክሮ

#የቅዱስ_ዳዊት_መዝሙር_ጥናት

" በረከትህ በሕዝብህ ላይነው::"

👉
#ክፍል_18

👉
https://youtu.be/kTlz2FbD1ig በዩቱብ ለምትከታተሉ::

https://youtu.be/V7xmIwb9Aes

👆
ይህ ቻናል ገዳማትን እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት የተከፈተ
የጉባኤ ተዘክሮ የዩቱብ ሊንክ
👉
https://youtu.be/DS-72Aa-020


የብሉያት እና የሐዲሳትን መጻሕፍት ከምንጩ ይማሩ።

http://t.me/AbaGebrekidangubaetezekro