አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC 🇪🇹
262 subscribers
580 photos
23 videos
45 links
Download Telegram
* አዲስ ዙ ፓርክ/ 6 ኪሎ አንበሳ ግቢ/

  አዲስ ዙ ፓርክ ሁለት ሳይቶች ያሉት ሲሆን አንዱ ስድስት ኪሎ የሚገኙው በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ የሚጠራው  መዝናኛ ስፍራ ነው ፡፡
  አንበሳ ግቢ በ19 40 ዓ.ም በ1.2 ሄክታር ቦታ ላይ ለአንበሳ እና ለዱር እንስሳቶች መጠለያ ሆኖ ለህብረተሰቡ የመናፈሻነት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ግቢው በወቅቱ ከወለጋ፣ከኢሉአባቦራ(ጎሮ) እና ከሲዳሞ የመጡ ሁለት ጥንድ ማለትም ሁለት ወንድ ሁለት ሴት አንበሶች እንዲሁም ሶስት ደበሎች የነበሩት ሲሆን በሂደትም ሰዎች አንበሶችን መጎብኘት ሲጀምሩ ፓርክ ሆኖ ተመስርቷል፡፡በዚያን ዘመን በግቢው የነበሩት አንበሶች ንጉሱ ለአደንና ለተለያዩ ጉዳዮች ወደተለያዩ ስፍራዎች ሲዘዋወሩ የአካባቢው ሰዎች በስጦታ መልክ የሰጧዋቸው እና ንጉሱ ያመጧቸው እንደነበሩ ይነገራል፡፡

  በአሁኑ ወቅት አንበሳ ግቢ የተለያዩ አገልግሎቶች ተጨምረውበት የመዝናኛ እና የመናፈሸ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡በተለይ በግቢው ውስጥ በየጊዜው የሚዘጋጁ የቤተሰብ ፌስቲቫሎች፣ የህጻናት ዘመናዊ መጫዎቻ አገልግሎቶች፣ለእይታ የቀረቡ በርካታ ብርቅየ  የዱር እንስሳቶች፣ልዩ ልዩ ባህላዊ እና ዘመናዊ ቁሳቁስ መሸጫ ሱቆች፣ደረጃውን የጠበቀ የካፌና የመናፈሻ አቅርቦቱ …የጎብኝዎችን ቀልብ የሚስብ አድርጎታል፡፡

  6 ኪሎ አንበሳ ግቢን ከሌሎች መዝናኛ ስፍራዎች ለየት የሚያደርገው በርካታ ብርቀየ የዱር እንሳቶች በውስጡ የያዘ መሆኑ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ከ13 በላይ ዝርያ ያላቸው የዱር እንስሳቶች ይገኙበታለል።
YOU GO PARK